TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አልሃምዱሊላሂ ~ #ድምፃችን ተሰማ

* 28 ጊዜያዊ የዑለማዎች አገዥ ምክር ቤት ተቋቁሟዋል
* 7 ጊዜያዊ አጋዥ ቦርድ አባላት ተመርጠዋል

ምስጋና ለአላህ፣ ምስጋና ለኮሚቴዎቻችን፣ ምስጋና ለሙፍቴ ሸህ ዑመር፣ ምስጋና ለጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ይሁንና ዛሬ ሕገ ወጡ መጅሊስ ከሥልጣን ወረደ የአመታት ገፍላችን ተነሳ።

ዛሬ በሸራተን አዲስ ሆቴል ጠዋት ሦስት ሰዓት ተጀምሮ እስከ ምሽቱ አንድ ሰዓት ተኩል ድረስ በቀጠለው የውይይት ጉባዬ 28 ጊዜያዊ የዑለማዎች አገዥ ምክር ቤት ተቋቁሟዋል። እንዲሁም 7 ጊዜያዊ አጋዥ ቦርድ አባላት ተመርጠዋል።

ብዙ የመወያያ ሰንዶች፣ ሕጎችደ፣ መተዳዳሪያዎች ደንቦች ቀርበው ተወያይተውባቸው ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ከአዳራሽ ሲወጡ...

\\"አልሃምዱሊላሂ ~ #ድምፃችን ተሰማ\\" እያሉ ነበር\\

Via Getu Temesgen
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት ዴቪድ ማልፓስንና ልዑካቸው በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። በሚያዝያ ወር አጋማሽ የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት ዴቪድ ማልፓስ ሦስት የአፍሪካ ሀገራትን በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ። ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ ያደነቁት ፕሬዚዳንቱ የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ትብብር እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ወሳኝ የፋይናንስና ዕውቀት ምንጭ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፓዊ፣ ማንዱራና ግልገል በለስ አካባቢዎች ያለው የፀጥታ ሁኔታ አሳሳቢ እንደሆነ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ የኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና የፌዴራል ፖሊስ በአካባቢዎቹ ፀጥታ ለማስፈን ጥረት እያደረጉ ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ባሕር ዳርን #የሚወድ የከተማዋን ደኅንነት መጠበቅ አለበት::" የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ
.
.
በባሕር ዳር በሚዘጋጀው የጣና ፎረም ለመታደም ከሚያዚያ 24 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ እንግዶች መግባት ይጀምራሉ፡፡ ጉባኤው የውጭ ግንኙነት ያጠናክራል፤ የውጭ ባለሀብቶችን ለመሳብም አማራጭ ይኖሆናል፤ የባሕር ዳርን የቱሪዝም፣ የትምህርትና የኮንፍረንስ ከተማነት ያጠናክራል ያሉት የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሙሉቀን አየሁ ናቸው፡፡ ስለሆነም "በፎረሙ ወጣቱ የባሕር ዳርን ገፅታ ለመሸጥ ርብርብ ማድረግ ይገባዋል" ነው ያሉት፡፡ ነገር ግን ስጋቶች እንዳሉም አቶ ሙሉቀን ጠቁመዋል፡፡ "ጉባኤው እንቅፋት ቢያጋጥመው ሀብት ለማመንጨትም ሆነ ለማምጣት፣ ፋብሪካ ለመክፈት፣ የሥራ ዕድል ለመፍጠር፣ ቱሪዝሙን ለማሳደግ ፈተና ይጋርጣል" ሲሉ ጠቁመዋል፡፡

በከተማዋ ባሉ አካባቢዎች የሚካሄዱ የጦር መሣሪያ ተኩሶች መታረም እንዳለባቸው ያሳሰቡት ከንቲባው "ተኩስን የሚፀየፍ ማኅበረሰብ እንዲኖረን እንሻለን፡፡ ለሠርግና መሠል ዝግጅቶች ሲባል የሚተኮሱ ርችቶችም ሆኑ ሮኬቶች ጭምር ድጋጤን ይፈጥራሉ፡፡ ከዚህ ተግባርም መቆጠብ ተገቢ ነው" ብለዋል፡፡ ባሕር ዳርን የሚወድ የባሕር ዳር ደኅንነት መጠበቅ እንዳለበት ያመለከቱት ከንቲባው ነዋሪው እንግዶቹን ጨዋነትንና ትልቅነትን በተላበሰ መልኩ ማስተናገድ እንደሚኖርበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ እንግዳ ተቀባይነት ባሕሪው ጎልቶ መታየት እንዳለበት በመጥቀስ፡፡ በከተማ አስተዳደሩ በኩል ቅድመ ዝግጅቱ መጠናቀቁንም አስታውቀዋል፡፡

የጣና ከፍተኛ ሰላምና ደኅንነት ፎረም የአፍሪካና ሌሎች አህጉራት መሪዎች የሀገር መሪዎች፣ የቀድሞ መሪዎች፣ የዓለማቀፍ ድርጅቶች መሪዎች፣ ምሁራንና ባለሀብቶች ይሳተፉበታል። ለ8ኛ ጊዜ የሚካሄደው የጣና ፎረም የፊታችን ቅዳሜ ይከፈታ፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ''ሚዲያ እና ዴሞክራሲ'' በሚል መሪ ቃል በትላንትናው ዕለት በአዲስ አበባ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ እየተከበረ ነው። #WorldPressFreedomDay

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ህጋዊ_ሰነድ እና ማስረጃ ያቀረቡ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቁጥር 116 ደረሷል፦

ህጋዊ ሰነድና ማስረጃ ሙሉ ለሙሉ ያቀረቡ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቁጥር 116 መድረሱን የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ አሳወቀ።

እስከ ባለፈው ሳምንት ድረስ ህጋዊ ሰነድ እና ማስረጃዎችን ሙሉ ለሙሉ ያቀረቡ፣ ያላመሟሉ እና ሙሉ ለሙሉ ያቀረቡ በሚል የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ማሳወቁ ይታወሳል፤ ኤጀንሲው አያይዞም የተጠየቁትን ያላቀረቡ ተቋማትን በሚመለከት እስካላቀረቡ ድረስ የያዙትን ተማሪ ከማስጨረስ በቀር አዲስ ተማሪ መመዝገብ እንደማይችሉ ማሳሰቢያ አስተላልፏል።

እስከ ባለፈው ሳምንት ህጋዊ ሰነድ እና ማስረጃ ሳያመሟሉ እና ምንም ሳያቀርቡ ቀርተው የነበሩት የተቋማት ቁጥር 74 እንደነበሩ ይፋ የተደረገ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 18 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙሉ ለሙሉ የተጠየቁትን ህጋዊ ሰነድና ማስረጃ ማቅረባቸውን ኤጀንሲው ገልጿል። ይህም ሙሉ ለሙሉ ህጋዊ ሰነድና ማስረጃ ያቀረቡ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቁጥር ወደ 116 ደርሷል።

የቀሩት 58 ተቋማት ህጋዊ ሰነዶቹንና ማስረጃዎቹን እስቃላቀረቡ ድረስ አዲስ ተማሪ መመዝገብ እንደማይችሉ የተላለፈው ውሳን እንተጠበቀ መሆኑን እየገለጽን ያላቀረቡትን ለይተን ዝርዝራቸውን የምናሳውቅ ይሆናል።

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ህጋዊ ሰነድና ማስረጃ ያላቀረቡ ተቋማት አዲስ ተማሪ መመዝገብ አይችሉም፤ ነገር ግን በመማር ላይ ያሉ ህጋዊ ተማሪዎችን እንዲያስጨርሱ ይደረጋል” የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ

@tsegabwolde @tikvahethiopia