TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የሀዋሳን ሃይቅ ዳርቻ በማልማትና በማፅዳት ከተማዋን #በዓለም በማስተዋወቅና የጎብኝዎች መዳረሻ እና የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ እንደሚሰራ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሚሊዮን_ማቴዎስ ተናግረዋል። በጅግጅጋ በተካሄደው 8ኛው የከተሞች ፎረም ለ7ኛ ጊዜ ራስን በማስተዋወቅ ሀዋሳ ከተማ 1ኛ መውጣቷን ምክንያት በማድረግ ለከተማው ማህበረሰብና ባለሀብቶች እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል። በትላንትናው ዕለት በተካሄደው የሽልማትና እውቅና ስነ ስርዓት ላይ 25 ባለሀብቶች ሲሸለሙ ከተማዋ ራሷን በማስተዋወቅ ከፍተኛ ቦታ እንድታገኝ የሰሩ 244 ባለሙያዎችም እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሰሜን ሸዋ ዞን በአጣዬ ከተማ ተዘግተው የነበሩ ተቋማት ተከፍተዋል። በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ ሰሞኑን በደረሰው ጥቃት በአጣዬ ከተማ ተዘግተው ነበሩ የንግድ ባንክና የተለያዩ የመንግስት ተቋማት ዛሬ ተከፍተዋል። በአካባቢው የሚገኝ የጋዜጣኞች ቡድን ባደረገው ምልከታ ሰሞኑን ተዘግተው የነበሩ የመንግስት ተቋማት ዛሬ ተከፍተው መደበኛ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ታዝበዋል። የግል ባንኮች ግን እስከአሁን ዝግ እንደሆኑ በስፍራው ያሉ ጋዜጠኞች ገልጸዋል፡፡ በጥቃቱ ጉዳት ያደረሱ ናቸው ተብለው ከተጠረጠሩ መካከል ሁለት ሰዎች ተይዘው ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኙም ታውቋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ተከስቶ የነበረው እሳት ሙሉ ለሙሉ #መጥፋቱን የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ያስታወቀ ሲሆን፣ በፓርኩ የተከሰተው የእሳት ቃጠሎ እስካሁን 700 ሄክታር የሚሆነው መሬት ላይ #ጉዳት ማድረሱን ገልጿል።

Via #ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር #የአድዋ ድልን የሚዘክር ማዕከል ሊገነባ ነው፡፡ #Adwa

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አድዋ ድል ነው።
አድዋ ታሪክ ነው።
አድዋ ፍልስፍና ነው።
አድዋ ትናንት ነው።
አድዋ ዛሬ ነው።
አድዋ ነገ ነው።
አድዋ ስለቅድመ አያቶቻችን ነው።
አድዋ ስለእኛ ነው።
አድዋ ስለልጆቻችን ነው።

ከአድዋ በላይ #ኢትዮጵያዊያንን አንድ የሚያደርግ ክስተት የለም፡፡ በመሆኑም የአድዋን ዙሪያ ገብ ሃሳብ ለመጨበጥ፣ ለማስተማር፣ ለማስፋት፣ በፅኑ ዘላቂ ፍልስፍና ላይ የተመሰረተ ቋሚ መዘክር ያስፈልገናል።

ይህ መዘክር በአገራችን እምብርት፣ የርቀትም የስልጣኔም መነሻ ፣ የሁሉም የሃገራችን ከተሞች ርቀት መጀመሪያ (ዜሮ ኪሎሜትር) በሆነው አራዳ ላይ መወጠኑ ተምሳሌትነቱን ላቅ ያለ ያደርገዋል።" ኢ/ር ታከለ ኡማ-የአድዋ ማዕከልን ለማቋቋም በተደረገ ምክረ-ሃሳብ ላይ የተናገሩት፡፡

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሽኝት ተደረገላቸው...

በሰሜን ተራሮች ፓርክ ተከስቶ የነበረውን እሳት #ለማጥፋት ለመጡት #የእስራኤል የእሳት አደጋ መከላከል ቡድን እና #ለኬንያዊው አብራሪ ሽኝት ተደረገ። ሽኝቱን የሰሜን ጎንደር ከአካባቢው ባለሀብቶች ጋር በመሆን ሲሆን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወርቁ ለምለሙ ለእሳት መከላከል ቡድኑ ለአብራሪው እንዲሁም እሳቱን ለማጥፋት ለተረባረበው ህብረተሰብ #ምስጋና አቅርበዋል።

Via Debark wereda communication
@tsegabwolde @tikvahethiopia