TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በድጋሚ ሀዘናችን ጥልቅ መሆኑን እንገልፃለን!

በሀገራችን #ወጣቶች ህልፈት የተሰማን #ሀዘን ጥልቅ ነው። ልባችን ደምቷል!! ለቤተሰቦቻቸው፤ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለመላው የሀገራችን ህዝብ መፅናናትን እንመኛል።

ነብስ ይማር!!
#ቀይ_ባህር ወንድም እህቶቻችንን በላብን!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከዶክተር #ኤልያስ_ገብሩ የፌስቡክ ገፅ!
.
.
"የሚጓዙት በዝናብ ነው!
የሚጓዙት በምሽት ነው!
የሚጓዙት ለሰላም ነው!
የሚጓዙት ለፍቅር ነውና በውሽንፍሩ መሐል ነጩን የሰላም አርማ ከፍ አድርገው ይዘዋል። ለኢትዮጵያ ለአንድነት እንጓዛለን! እኛ ልጆቿ እያለን ኢትዮጵያ አትፈርስም ብለው የተነሱትን የTIKVAH ቤተሰቦች እናመሰግናለን። በሁሉም የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች ሲመጡ የጀግና አቀባበል ይደረግላቸው። ትላንት በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ደስ የሚል የአንድነት መንፈስ ፈጥረው ተመልሰዋል። ቀጣይ መዳረሻቸው የሐዋሳ ዩኒቨርስቲ እንደሆነም አሳውቀዋል።
#ጀግኖቻችን_ናችሁ!
#Keep_Walking #My_Generation"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከቃሊቲ...

"ሀይ ፀግሽ ትላንት ቃሊቲ ላይ የተፈፀመብንን ግፍ ለህዝብ አድርስልን እባክክህ እባክህ፤ነገሩ እንዲ ነዉ ቃሊቲ መናኸርያ አካባቢ ነስር ሚባል መስጂድ አለ፤ እና እዚ መስጂድ ላይ ህፃናት የሚማሩበት፤ አስክሬን ሚታጠብበት even ሰዉ ከበዛ የሚሰግድበት ቦታ እንኳ የለም፤ነገር ግን መስጂዱ ፊት ለፊት ያለ ቦታ ላይ መስገድ ተፈቅዶልን እየሰገድን እያለ ያለምንም ማስጠንቀቂያ የፀጥታ ሀይሎች ጥይት በመተኮስ አስለቃሽ ጭስ በመልቀቅ ብዙዎች ተጎድተዋል። እባክህ ለሚመለከተው አካል አሳዉቅልን። Ak ነኝ ከቃሊቲ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ፓሊስ ጥቃት ፈጽሞብናል!››

‹‹በአዲስ አበባ አቃቂ አካባቢ በሚገኘው አብድልቃድር መስጅድ ውስጥ ፓሊስ ጥቃት ፈጽሞብናል!› … ፖሊስ በእምነት ተቋም ውስጥ ገብቶ የመሳሪያ እሩምታ እና በንፁሀን ዜጎች ላይ ያደረሰው ጉዳት እናወግዛለን! … መንግስት ይህንን ህገወጥ ድርጊት ባደረጉ ፓሊሶች ላይ በአፋጣኝ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል!›› - የህዝበ ሙስሊሙም አቤቱታ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ትላንት በቃሊቲ #አብዱልቃድር_መስጂድ የተፈጠረው ችግር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዕውቅና ውጪ የተደረገ ነው፡፡ ምንም ዓይነት ጥያቄ ቢኖር በመነጋገር መፍታት እየተቻለ አላስፈላጊ #ጉዳት ወደሚያደርስ እንቅስቃሴ ውስጥ መግባት ከየትኛውም አካል የማይጠበቅ ተግባር ነው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጉዳዩ #ከዕውቅናው_ውጪ እንዴት እንደተፈፀመ እና በቀጣይም መጣራት የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች በሙሉ በመፈተሽ በመዋቅሩ የማስተካከያ ዕርምት እንደሚወስድ በዚህ አጋጣሚ ያረጋግጣል፡፡ በተፈፀመው ነገር ሁሉ የከተማ አስተዳደሩ የተሰማውን #ሃዘን ይገልፃል፡፡" Mayor Office of Addis Ababa

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ቃሊቲ የአዲስ አበ ከተማ አስተዳደር ትላንት በቃሊቲ አብዱልቃድር መስጅድ የተፈጠረው ችግር ከእውቅናዬ ውጪ ነው አለ። ጥያቄ ቢኖር እንኳን #በመነጋገር መፍታት እየተቻለ አላስፈላጊ ጉዳት የሚያደርስ እንቅስቃሴ ውስጥ መግባት ከየትኛውም አካል የማይጠበቅ ተግባር ነው ሲል ድርጊቱን ኮንኖታል። ከተማ አስተዳደሩ ጉዳዩ #ከዕውቅናው_ውጪ እንዴት እንደተፈፀመ እና መጣራት የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች በሙሉ #በመፈተሽ በመዋቅሩ #የማስተካከያ ዕርምት እንደሚወስድ አረጋግጧል፤ በደረሰው ጉዳትም የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከቃሊቲ...

"ዛሬ ቃሊቲ ቶታል #ወደመረጋጋት ተመልሷል፤ ሁሉም ወደስራ ገብቷል፤ ታክሲዎችም አገልግሎት እየሰጡ ነው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ኢትዮጵያ ከተለወጠች የምትለወጠው በትጉ አይነት ሰራተኛ ልጆቿ ነው ። የነገዋ ኢትዮጵያ ልታምር የምትችለው #ከጥላቻና #ዘረኝነት ይልቅ የስራ ባህልን ለልጆቻቸው ባወረሱ ቅን ወላጆች ነው።" Mesued M.

መልካም ቀን ይሁንልን!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የአገር ውስጥ ጎብኝዎችን ቁጥር 37 ሚሊዮን 171 ሺህ 869 ለማድረስ አቅዶ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 23 ሚሊዮን 415 ሺህ 53 መድረሱን አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአጣዬ ከተማ በአንጻራዊነት ሰላም በመስፈኑ ከጥቃቱ በኋላ ተዘግተው የነበሩ ባንክ እና የተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት ትናንትና ተከፍተዋል። አጎራባች የሰሜን ሸዋ ዞን ወረዳ ህዝብ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን ተገልጿል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia