TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
መግለፂ ሓዘን ብሄራዊ ክልላዊ መንግስቲ ትግራይ
------------------------------------
ብሄራዊ ክልላዊ መንግስቲ ትግራይ ክሳብ ሐዚ ብዘሎ መረዳእታ ልዕሊ 40 ዝኮኑ መናእሰይ ወገናት ካብ ወረዳ ኣፅቢ ወንበርታ ከባቢኣን ተበጊሶም ናብ ስዑዲ ዓረብን የመንን ብቀይሕ ባሕሪ ክሰግሩ ብዘጋጠሞም ሓደጋ መርከብ ጥሒሎም ህይወቶም ዝሰኣኑ ወገናት ብስም ህዝብን ብሄራዊ ክልላዊ መንግስቲ ትግራይን ዝተሰምዖ መሪር ሓዘን ብምግላፅ ንስድራ ግዳያት እቲ ሓደጋን ንመላእ ህዝቢ ትግራይን ፅንዓት ይምነ።

ቢሮ ርክብ ህዝብን መንግስትን ክልል ትግራይ
መቐለ:- 08 ሚያዝያ 2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መላው የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት #በወገኖቻችን ሞት የተሰማንን #ጥልቅ_ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦች ለወዳጅ ዘመዶች በመላ #መፅናናትን እንመኛለን!!

ነብሳቸውን በገነት ያኑርልን!
@tsegabwolde @tikvahehiopia
መብራት በመጥፋቱ ስብሰባው ተቋረጠ

ዛሬ የሚንስትር መስሪያ ቤታቸውን የ9 ወራት ሪፖርት ለማቅረብ በፓርላማ የተገኙት የባህልና ቱሪዝም ሚንስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው ሪፖርታቸውን ካቀረቡ በኃላ ከፓርላማ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርቦላቸው ነበር። ሚኒስትሯ ለቀረቡት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ሲዘጋጁ ግን የፓርላማው መብራት ድርግም ይላል። በጀነሬተሩ ብቃት የሚታማው የፓርላማው ሠራተኞች ጀነሬተሩን ለማስነሳት ላይ ታች ቢሉም የፓርላማ አባላቱ ሊታገሱ አልቻሉም። የአንዳንድ የፓርላማ አባላትን መውጣት የተመለከቱት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ የፓርላማው ወንበር ባዶ ከመሆኑ በፊት ስብሰባው ከሰዓት በኃላ ይቀጥላል ብለው ወደ ቢሯቸው አምርተዋል።

Via ቁምነገር ሚዲያ/ከኤልያስ መሰረት የፌስቡክ ገፅ/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ታራሚዎች አመለጡ...

በጋምቤላ ከተማ ማረሚያ ቤት ትላንት በተቀሰቀሰ ብጥብጥ 90 ታራሚዎች ማምለጣቸውን የከተማዋ ከንቲባ አቶ ኮት ሜንታፕ ለጀርመን ራድዮ ተናገሩ። ታራሚዎቹ ያመለጡት በአጥር ዘልለው ነው ብለዋል። በጋምቤላ ማረሚያ ቤት ብጥብጡ የተነሳው ትላንት ረፋድ ላይ በሁለት ታራሚዎች መካከል በተፈጠረ የግል ጠብ ምክንያት መሆኑን ከንቲባ ኮት ሜንታፕ ገልጸዋል። ሁለቱ ታራሚዎች ውኃ በጀሪካን ሲቀዱ መጋጨታቸውን የሚናገሩት አቶ ኮት ጠቡ የብሔር መልክ ከያዘ በኋላ ወደ ብጥብጥ ተቀይሯል ብለዋል።

ግጭቱ በተነሳበት ወቅት ከተማው ላይ ተኩስ ይሰማ እንደነበር አንድ የከተማዋ ነዋሪ ለጀርመን ራድዮ ተናግሯል። ማረሚያ ቤቱን እንደሚያውቀው የገለጸው ይሄው ነዋሪ አመለጡ የተባሉት 90 ሰዎች ከጠቅላላው የማረሚያ ቤቱ ታራሚዎች አንጻር ቁጥሩ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁሟል።

ያመለጡትን ታራሚዎች ለማስመለስ እና በቁጥጥር ስር ለማዋል የጸጥታ አካላት የተቀናጀ ዘመቻ መጀመራቸውን የጋምቤላ ከንቲባ አስታውቀዋል። አቶ ኮት ካመለጡት አንዳንዶቹ ወደ ማረሚያ ቤቱ መመለሳቸውን ቢገልጹም ትክክለኛ ቁጥራቸውን ከመግለጽ ተቆጥበዋል። ከንቲባው በትላንትናው የጋምቤላ ማረሚያ ቤት ብጥብጥ «የተጎዳ ሰው የለም» ብለዋል።

Via የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአማራ ክልላዊ መንግስት ኦሮሞ ማህበረሰብ ልዩ ዞን ባቲ ወረዳና በአፋር ክልላዊ መንግስት አጎራባች ወረዳዎች በየጊዜዉ የሚከሰቱ ግጭቶችን ለማስቆም የእርቅና የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው። የእርቅና የሰላም ኮንፈረሱ እየተካሄደ ያለዉ በአፋር ክልል የሚገኙ 3 ወረዳዎች ማለትም #በአባር#በተለላክና #በጭፍራ ወረዳዎች እንዲሁም በኦሮሚያ ማህበረሰብ ልዩ ዞን ባቲ ወረዳ በሚገኙ ኗሪዎች የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች በተገኙበት ነው። የኮንፈረንሱ አስተባባሪዎች እንደገለጹት በሁለቱ ማህበረሰቦች መካከል በየጊዜው የሚነሱ ግጭቶች መንስኤያቸዉ የግጦሽ መሬት እንደሆነ ተናግረዋል። የእርቅና የሰላም ኮንፈረንሱ በሁለቱ ህዝቦች መካከል የቆየዉን የባህል የቋንቋ እና የማህበረሰብ ግንኙነት ትስስር ወደ ቀድሞዉ ሰላማዊ ግንኙነት ለመመለስ እንደሚያግዝም ገልጸዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የስሜን ተራሮች እሳት ጠፍቷል...

ከኬኒያ የመጣችው ሄሊኮፕተርና ከእስራኤል የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የእሳት ቃጠሎ ለማጥፋት የመጣው ቡድን ተልዕኮአቻቸውን ዛሬ ሚያዚያ 08/2011 ዓ.ም ጨርሰው ነገ ወደየሀገራቸው ይመለሳሉ፡፡ ላበረከቱት በጎ አስተዋጽኦ ዛሬ ከቀኑ 10:00 ሰአት ጀምሮ የምስጋና ፕሮግራም በዞኑ አስተዳደር ፡ በደባርቅ ከተማ ባለሀብቶች፡ በቱሪዝም የተሰማሩ አስጎብኚዎች ማህበራትና በፓርክ ጽ/ቤት አዘጋጅነት ይካሄዳል፡፡ እሳቱም ሙሉ በሙሉ መጥፋቱን የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪ አቶ #ይመር_ስዩም ገልፀዋል። ቃጠሎው ደግም እንዳይነሳም የዞኑ አስተዳደር ከወረዳ አስተዳደር ጋር በቅንጅት በመስራትና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ ባለቤት እንዲሆን መስራት እንደሚገባ የዞኑ ነዋሪዎች አሳስበዋል፡፡

Via North Gondar Communication
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሹመት ሰጥተዋል፡፡ በዚሁም መሰረት፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ፣ መምህር የሆኑት፣ ዶ/ር ሙሉጌታ ፍስሃ፣ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል፡፡ ዶ/ር ሙሉጌታ ፍስሃ፣ ባለስልጣኑን ለስምንት አመታት የመሩትን አቶ ዮናስ ደስታን ይተካሉ፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ በሥነ-ጥበብና ታሪክ በረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መምህር የሆኑት አቶ አበባው አያሌው፣ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል፡፡

Via Sheger FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በቤንች ማጂ በአለመረጋጋት ተዘግተው የነበሩ መንገዶች ተከፈቱ‼️

በደቡብ ክልል ቤንች ማጂ ዞን በታጠቁ ኃይሎች ለወራት ተዘግተው የነበሩ መንገዶች ዳግም እንዲከፈቱ መደረጉን አንድ ከፍተኛ የአገር መከላከያ ሰራዊት አመራር አስታወቁ። ከባለፈው ዓርብ ጀምሮ የተከፈቱት መንገዶች የማጂን፣ የሱርማን እና የቤሮ ወረዳዎችን እርስ በእርሳቸው እና ከቤንች ማጂ ዞን ዋና ከተማ ሚዛን ተፈሪ ጋር የሚያገናኙ ናቸው ተብሏል።

በመከላከያ ሰራዊት ምዕራብ ዕዝ የዐሥራ ሁለተኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጄነራል አበበ በየነ ለዶይቼ ቬለ (DW) እንደተናገሩት ሰራዊቱ መንገዶቹን ያስከፈተው ከፌደራል ፖሊስ፣ ከደቡብ ክልል ልዩ ኃይል ጋር ያዋቀረው የዕዝ አመራር (ኮማንድ ፖስት) በወሰደው የማረጋጋት ርምጃ ነው።

በአካባቢው ኮማንድ ፖስቱ ሥራ ከጀመረ ወዲህ አንጻራዊ ሰላም መገኘቱን DW ያነጋገራቸው አንድ የቤንች ማጂ ዞን ቤሮ ወረዳ ነዋሪ ገልጸዋል። ሆኖም በወረዳው “ንጹሃን ዜጎችን የገደሉ እና ንብረት ያቃጠሉ” ያሏቸው ግለሰቦች እስካሁን ለሕግ አለመቅረባቸው ቅር እንዳሰኛቸው ተናግረዋል።

የነዋሪዎቹን ቅሬታ የሚጋሩት ብርጋዲየር ጄነራል አበበ በበኩላቸው ኮማንድ ፖስቱ ቅድሚያ ትኩረት የሰጠው አካባቢውን የማረጋጋት ሥራ መሆኑን ገልጸው በቀጣይ ቀናት ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን የመለየት ሥራዎች እንደሚጀመሩ አመልክተዋል።

ካለፈው ዓመት መጨረሻ አንስቶ በደቡብ ክልል በሱርማ፣ በቤሮና፣ በማጂ ወረዳዎች በተከሰተው አለመረጋጋት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸውን ከአካባቢው አስተዳደር የተገኘው መረጃ ያመለክታል። በአካባቢው ባለው አለመረጋጋት በርካቶች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው እንደሚገኙም የአካባቢው አስተዳደር ጠቁሟል።

Via የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በቃሊቲ አካባቢ ምን ተፈጠረ? የሚለውን ከአይን እማኞች እና ከሚመለከታቸው አካላት አጣርቼ መረጃዎችን የማቀርብ ይሆናል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር #የአድዋን ታሪክ የሚዘክር ማዕከል ሊቋቋም ነው፡፡ የማዕከሉን ግንባታ #ወጪ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንደሚሸፍን ታውቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መከላከያ_ሰራዊት በቤንች ማጂ ዞን ተዘግተው የቆዩ መንገዶችን እንዲከፈቱ አድርጓል። #ኢትዮጵያ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

በስልጤ ዞን ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ በሰዎች ህይወት ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ።

የጎርፍ አደጋው በስልጤ ዞን ቅበት ከተማ እና በስልጤ ወረዳዎች በሚገኙ አምስት ቀበሌዎች ላይ መድረሱን የወረዳው አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ዩኒት ለfbc ያደረሰው መረጃ ያመለክታል።

ትላንት ማሻውን በአካባቢው የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የሶስት ወንዞት የውኃ ሙላት የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉንም አስታውቋል።

በአደጋው ህይወታቸውን ካጡ ሰዎች መካከልም ሶስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት መሆናቸው የታወቀ ሲሆን፥ ህይወታቸው ካለፈ ሰዎች ውስጥ የአራቱ አስክሬን መገኘቱንና የሁለቱን ለማግኘት ፍለጋው አሁን መቀጠሉም ተገልጿል።

በአደጋው እስካሁን በቁጥር ያልታወቁ የቤት እንስሳት በተለይም ከብቶች የሞቱ ሲሆን፥ ከፍተኛ የንብረት ውድመት መድረሱም ተነግሯል።

የስልጤ ዞን አደጋ ስጋት ስራ አመራር ፅህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ወሲላ አሰፋ በበኩላቸው፥ በአደጋው ከ5 ሺህ 600 በላይ ቤተሰቦች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን ተናግረዋል።

342 ሄክታር መሬት ላይ የለማ ሰብል በውኃ መጥለቅለቁን የተናገሩት ኃላፊዋ 637 ቤቶችም በውኃ ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል።

ለተጎጂዎች የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ለማድረግ ምግብና ምግ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ከክልል እና ከዞን ለማቅረብ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

መጪው ክረምት እንደመሆኑ መሰል አደጋዎች እንዳይደርሱ ከአሁኑ የቅድመ መከላከል ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን አንስተዋል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የስሜን ፓርክ እሳትን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ተችሏል፤ በገደላማው የፓርኩ ክፍል ውስጥ ግን የተወሰነ ጭስ አሁንም ይታያል" - የፓርኩ የኅብረተሰብ እና የቱሪዝም ኃላፊ አቶ ታደሰ ይግዛው

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በስሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የተነሳውን ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር የተቻለ ሲሆን፤ አሁንም ድረስ ግን በፓርኩ ገደላማና ቆላማ ክፍል የተወሰነ ጭስ እንደሚታይ የፓርኩ የኅብረተሰብ እና የቱሪዝም ኃላፊ አስታውቀዋል። ሃለፊው አቶ ታደሰ ይግዛው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዛሬ (ሚያዚያ 08 ቀን 2011 ዓ.ም)ከሰአት በሁዋላ እንደገለጹት፤ እሳቱን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር የተቻለ ቢሆንም አካባቢው ወጣ ገባ የበዛበትና ቆላማ ክፍል ያለው በመሆኑ እሳት ሊኖር ይችላል የሚል ጥርጣሬ በማሳደሩ አሁንም የእሳት ማጥፋቱ ሂደቱ እንደቀጠለ ነው። ነዳጅና ውሃ በቅርበት ማቅረብ በመቻሉ ውጤታማ ስራ መስራት ተችሏል ያሉት አቶ ታደሰ፤ ለእሳቱ መጥፋት ሄሌኮፍተሯና የእስራኤል ባለሙያዎች አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደነበር ተናግረዋል። አሁን ላይ የእስራኤል ባለሙያዎች ወደ ቆላማው ክፍል ዘልቀው በመግባት በሬድዮ በመገናኘት ጭስ ያለበትን አካባቢ በማሰስ ላይ መሆናቸውን አቶ ታደሰ አስታውቀዋል። በእንሰሳት ላይ የደረሰውን ጉዳት የሚያጠና ቡድን ስራ የጀመረ መሆኑን የተናገሩት አቶ ታደሰ፤ እስካሁን ግን የተጎዳ ምንም አይነት የዱር እንስሳት #አልተገኘም ብለዋል፡፡

Via EPA
ፎቶ: AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በምዕራብ ሸዋ ዞን ባኮ ቲቤ ወረዳ በደረሱ ሁለት የተሽከርካሪ አደጋዎች  የስምንት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ። በአደጋዎቹ በ14  ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል። የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሳጂን #ረቡማ_ጉሉማ እንደገለፁት፥ ትላንት ከቀኑ 10  ሰዓት አካባቢ 17 ሰዎችን አሳፍሮ ከአምቦ ወደ ባኮ ከተማ ይጓዝ የነበረ አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ የመገልበጥ አደጋ ደርሶበታል። በአደጋው ም የስድስት ሰዎች ህይወት ወድያው ሲያልፍ በ11 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል። አደጋው በወረዳው ሰደን ቂጤ ቀበሌ ጎዳ ቡሩሳ በተባላ አካባቢ መድረሱን የገለፁት ሳጂን ረቡማ፥ አሽከርካሪው ለጊዜው በመጥፋቱ ክትትል እየተደረገበት መሆኑን ተናግረዋል። በተመሳሳይ ከአዲስ አበባ ወደ ጊምቢ ከተማ በመጓዝ ላይ የነበረ መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ በወረዳው ሲናኖ ወልቂጤ ቀበሌ ሲደርስ በመገልበጡ አሽከርካሪውን ጨምሮ የሁለት ሰዎች ህይወት ወድያው አልፏል። በሶስት ሰዎች ላይ ደግሞ  ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ሳጂን ረቡማ ገልጸዋል። “በአደጋዎቹ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች አስከሬን ለየቤተሰቦቻቸው ተሰጥቷል” ያሉት ሳጂኑ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው በባኮ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን አስታውቀዋል። እንደ ሳጅን ረቡማ ገለጻ የአደጋዎቹ መንስኤ እየተጣራ ነው።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia