TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ሶማሌ ክልል ሸላቦ⬇️

በሶማሌ ክልል #ሸላቦ አቅራቢያ በበርሀ ደን ላይ በደረሰ #የእሳት ቃጠሎ ከፍተኛ ስፋት ያለው የእፀዋት ክምችት መውደሙን የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) አስታውቋል። #የኦጋዴን የጋዝ ክምችት በሚገኝበት በዚህ አካባቢ የደረሰውን ቃጠሎ ለማቆም የክልሉ መንግስትም ሆነ ፌደራል መንግስት ምንም ጥረት አላደረጉም ሲል #ኦብነግ ከሷል። የእሳቱ መንስዔ አልታወቀም።

©ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ከሐምሌ 26 እስከ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ በሶማሌ ክልል በጅግጅጋ ከተማና በአካባቢው በተፈጸመ #የእሳት_ቃጠሎ የወደሙት የኦርቶዶክስ የእምነት ተቋማት ግምት ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ መርማሪ ቡድን አስታወቀ፡፡ መርማሪ ቡድኑ ሐሙስ ኅዳር 13 ቀን 2011 ዓ.ም. ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት እንደገለጸው ሃይማኖትን፣ ማንነትንና ቋንቋን መሠረት በማድረግ ለአምስት ቀናት በተፈጸሙ ግድያ፣ ቃጠሎና መፈናቀል ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን አስታውሷል፡፡ በእምነት ተቋማቱ ላይ የደረሰው ጉዳት የተገለጸውን ያህል መሆኑንም፣ በክልሉ ያለው መርማሪ ቡድን ማሳወቁን ገልጿል፡፡ በተጨማሪም ክራውን የሚባል ሆቴል ሙሉ በሙሉ መቃጠሉንና የወደመው ንብረት ግምትም 42 ሚሊዮን ብር መሆኑ እንደታወቀ ለፍርድ ቤቱ ገልጿል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ #የእሳት_ቃጠሎ እንዲደርስበት አድርገዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች በፖሊስ #ቁጥጥር_ስር መዋላቸውን EBC ዘግቧል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️

#በባሌ_ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ በድጋሜ #የእሳት_ቃጠሎ ተከሰተ። ከሳምንታት በፊት ስድስት ቀናት የዘለቀ ቃጠሎ በፓርኩ ውስጥ መከሰቱ ይታወሳል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia