TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰበር ዜና-ኦብነግ(ONLF)⬆️

#ኦብነግ (የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር) የተኩስ ማቆም አዋጅ ማወጁ ተሰማ። ኦብነግ ባወጣው መግለጫ የድርጅቱ አባላት ከዛሬ ጀምሮ በኢትዮጵያ መንግስት የፀጥታ አካላት ላይ ጥቃት እንዳይፈፅሙ አዟል።

©wariye Amiin Mahamed
@tsegabwolde @tikvajethiopia
#update ሶማሌ ክልል ሸላቦ⬇️

በሶማሌ ክልል #ሸላቦ አቅራቢያ በበርሀ ደን ላይ በደረሰ #የእሳት ቃጠሎ ከፍተኛ ስፋት ያለው የእፀዋት ክምችት መውደሙን የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) አስታውቋል። #የኦጋዴን የጋዝ ክምችት በሚገኝበት በዚህ አካባቢ የደረሰውን ቃጠሎ ለማቆም የክልሉ መንግስትም ሆነ ፌደራል መንግስት ምንም ጥረት አላደረጉም ሲል #ኦብነግ ከሷል። የእሳቱ መንስዔ አልታወቀም።

©ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኦብነግ

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር የተመሰረተበት 35 ዓመት በዓል ከትላንት ጀምሮ በጅግጅጋ ከተማ ከተማ እየተከበረ ነው። ትላንት በነበተው ዝግጅት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት ክልሉ የሶዴፓ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙስተፌ ሙሁመድ ግንባሩ ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብሉ በመምጣት ከአባላቱና ከደጋፊዎቹ ጋር በዓሉን ማክበር በመቻሉ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል። “የዛሬ ዓመት ኦብነግ በዚህ ቦታ በዓሉን ማዘጋጀት አይታሰብም ነበረ፤ ይህ በሀገሪቱ የመጣው ለውጥ አካል ነው” ብለዋል።

የኦብነግ ሊቀመንበር ተወካይ ጀኔራል #አብዱላሂ_ሙክታር በበኩላቸው ግንባሩ የምስረታ በዓሉን በጅግጅጋ ከተማ ሲያከብር ከ27 ዓመታት ወዲህ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን ገልጸዋል። በምስረታ በዓሉ ላይ የተገኙ የግንባሩ አመራሮች ፣አባላትና ደጋፊዎችን አመስግነዋል። በበትላንትናው የበዓሉ ዝግጅት ስነስርዓት ወቅት የሶዴፓ አመራሮችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"ማንኛውም #የIS እንቅስቃሴ እንመክታለን" #ኦብነግ

ኦብነግ ወደ ኢትዮጵያ ሰርጎ በመግባት ጥቃት ለመፈጸም የሚያስቡ የውጭ ሃይሎችን እታገላለሁ ብሏል፡፡ የኦብነግ ሊቀመናብርት ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ከሱማሊያ እየተነሳ ኢትዮጵያ ላይ ሽብር ጥቃት መፈጸም የሚያስበው ጽንፈኛው አይኤስ በሱማሌ ክልል በኩል ሰርጎ እንዳይገባ ኦብነግ ጠንክሮ ይመክታል፤ ከክልሉ እና ፌደራል መንግሥትም ጋር በቅርበት ተባብሮ ይሠራል ብሏል፡፡

Via ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኦብነግ ፓርቲ ልሆን ነው አለ!

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (#ኦብነግ) ወደ ፓርቲነት ራሱን ለመቀየር እየሰራሁ ነው አለ። ለአምስት ቀናት የሚቆየው የግንባሩ አራተኛ ድርጅታዊ ጉባዔ በጎዴ ከተማ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል።

የግንባሩ ሊቀመንበር  አድሚራል መሐመድ ዑመር ጉባዔውን ሲከፍቱ እንደተናገሩት ድርጅታቸው ከነጻ አውጪነት ወደ ፓርቲነት ራሱን በመቀየር ለመንቀሳቀስ ይፈልጋል። ለዚህም ጉባዔው የሕዝቡን ፍላጎት መሠረት ያደረጉ የፖለቲካ አቅጣጫ የሚነድፍበት እንደሚሆንም አስታውቀዋል።

(ENA)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኦብነግ

የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) ለረጅም ጊዜ በውጭ ጉዳይ ኃላፊነት ያገለገሉትን አብደረህማን ማሓዲን ጎዴ ላይ ባደረገው ስብሰባ የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ፡፡ ለረጅም ጊዜ የድርጅቱ ሊቀመንበር የነበሩት አዲሚራል ሙሐመድ ኦማር ኦስማን ጡረታ መውጣታቸው ታውቋል፡፡ መሓዲ 340 ድምጽ በማግኘት 247 ድምጽ ያገኙትን ተፎካካሪውን በማሸነፍ ተመርጠዋል፡፡

Via Harun Maruf(Addis Zeyebe)

@tsegabwolde @tikvahethiopia