#ኦብነግ
የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር የተመሰረተበት 35 ዓመት በዓል ከትላንት ጀምሮ በጅግጅጋ ከተማ ከተማ እየተከበረ ነው። ትላንት በነበተው ዝግጅት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት ክልሉ የሶዴፓ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙስተፌ ሙሁመድ ግንባሩ ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብሉ በመምጣት ከአባላቱና ከደጋፊዎቹ ጋር በዓሉን ማክበር በመቻሉ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል። “የዛሬ ዓመት ኦብነግ በዚህ ቦታ በዓሉን ማዘጋጀት አይታሰብም ነበረ፤ ይህ በሀገሪቱ የመጣው ለውጥ አካል ነው” ብለዋል።
የኦብነግ ሊቀመንበር ተወካይ ጀኔራል #አብዱላሂ_ሙክታር በበኩላቸው ግንባሩ የምስረታ በዓሉን በጅግጅጋ ከተማ ሲያከብር ከ27 ዓመታት ወዲህ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን ገልጸዋል። በምስረታ በዓሉ ላይ የተገኙ የግንባሩ አመራሮች ፣አባላትና ደጋፊዎችን አመስግነዋል። በበትላንትናው የበዓሉ ዝግጅት ስነስርዓት ወቅት የሶዴፓ አመራሮችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia