TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኦነግ(ABO)፣ አግ 7...⬇️

በሀገሪቱ የሚገኙ 7 የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰሞኑን በአዲስ አበባና በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች የተከሰቱ #ግጭቶችን አወገዙ።

የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎቹ አሁን ላይ በሀገሪቱ በተለይም በአዲስ አበባ እየታየ ያለው ወቅታዊ ግጭት ላይ መስከረም 6 እና 7 ውይይት ካደረጉ በኋላ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የጋራ #መግለጫ ሰጥተዋል።

የጋራ መግለጫውን የሰጡት የፖለቲካ ፓርቲወችም የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ)፣ ኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)፣ የኦሮሞ ዴሞራሞክራቲክ ግንባር፣ የኦሮሞ አንድነት ለነጻነት፣ የኦሮሞ አንድነት ግንባር፣ ሰማያዊ ፓርቲ እና የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንደነትና
ዴሞክራሲ ንቅናቄ መሆናቸውም ነው የተገለጸው።

የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎቹ ባለፉት 2 ቀናት ባደረጉት #ግምገማ መሰረትም ግጭቱ አሳሳቢና አሳዛኝ መሆኑን ነው በጋራ መግለጫቸው ያመለከቱት።

በዚህም በሰዎች ህይወት፣ አካልና ንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት በጽኑ ማውገዛቸውን ነው በጋራ መግለጫቸው ያስታወቁት።

የግጭቱ #ተዋናያን እና ከጀርባ ሆነው ግጭቱን የሚያስተባበሩ የውጭና የሀገር ውስጥ ሃይሎች ከዚህ ድርጊታቸው በአስቸኳይ እንዲቆጠቡም በጋራ መግለጫቸው አሳስበዋል።

#ወጣቱም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በራሱ መስዋትነት የመጣውን ሃይል #ለመቀልበስ ከሚሰሩ ሀይሎች ጎን #እንዳይሰለፍም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

በዚህ አስቸጋሪ ወቅት በሀገሪቱ የመጣውን ለውጥ የመምራት ሃለፊነት የተጣለባቸው የመንግስት አካላትም የሀገርንና የህዝብን ደህንነት ለመጠበቅ ሲሉ እንዲህ ዓይነቱ ግጭት #ከመከሰቱ በፊት የመከላከል እርምጃ እንዲወስዱ እና ወንጀለኞችን #በአስቸኳይ ለህግ እንዲያቀርቡ ጠይቀዋል።

አሁን ላይ በሀገሪቱ ሀሳብን በነጻነት ለማራመድ የሚያስችል ሰላም መስፈኑና ለዘመናት የታገሉለትና ሁሉንም ለማስተናገድ የሚያስችል የፖለቲካ ምህዳር መፈጠሩንም አስረድተዋል።

ስለሆነም ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል የዴሞክራሲ ባህልን በጋራ ማዳበሩ ጠቃሚ መሆኑ ነው በመግለጫው የተመላከተው።

ልዩነቶችን በሃይል ለመፍታት የሚደረጉ ጥረቶች ለማንኛውም አካል ጠቃሚ ያለመሆኑን በመግለጫቸው ያመላከቱት የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎቹ፥ ሀገሪቱን የፍትህ፣ የዴሞክራሲና የአንድነት ተምሳሌት ለማድረግ መስራት እንደሚገባም በመግለጫው ጠቁመዋል።

ለሰላም፣ ዴሞክራሲና ለህዝቦች አንድነት መጠናከር የበኩላቸውን ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውንም የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎቹ በጋራ መግለጫቸው አስታውቀዋል።

ለዚህም ለፖለቲካ ፓርቲ አባሎቻቸው፣ ደጋፊዎቻቸውና ለመላው ህዝብ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ፦

ብሄራዊ የደህንነት ምክር ቤት በ08/01/2011 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በአገራችን እየተስተዋሉ ያሉ ህገ-ወጥና የስርዓት አልበኝነት እንቅስቃሴዎችን ገምግሞ የሚከተለውን መግለጫ አውጥቷል።

ባለፉት አምስት ወራት የዴሞክራሲ ምህዳርን ለማስፋት በርካታ ስራዎች ተከናውነው ተስፋ ሰጪ ውጤቶች ተገኝተዋል። በዚህም መላው ህዝባችን ከመቼውም ጊዜ በላይ በአገሩ ተስፋ እንዲሰንቅና በሃገሩ መጻዒ እድል ላይ የራሱን አስተዋፅኦ ለማበርከት እንዲነሳሳ አድርጓል።

ሆኖም ግን የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ከህግ የበላይነት ውጭ #የሚታሰብ አለመሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

በለውጥ ውስጥ እንደመሆናችን መጠን መንግስት ችግሮችን በሀይል ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ ሆደ ሰፊነትን ቢያሳይም ይህን እንደ አቅመ ቢስነት የተመለከቱ የጥፋት ሀይሎች #የወጣቱን ስሜት በማነሳሳት የሚፈፅሟቸው ወንጀሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱና እየተበራከቱ
መጥተዋል።

ሰሞኑን በአዲስ አበባና በዙሪያዋ በተከሰቱ ግጭቶች በርካታ ዜጎች ውድ #ህይወታቸውን አጥተዋል። ይህን ብጥብጥ በተለያዩ አካባቢዎች
ለማስቀጠል፣ በሱማሌ ክልልና በሌሎች አካባቢዎች የከሸፈባቸውን የጥፋት አቅድ በሌላ ሙከራ ለመቀጠል እንዲሁም በመስከረም መጨረሻ የሚካሄደውን #የኢህአዴግ ጉባኤ ለማደናቀፍ በርካታ ጥረቶች እየተደረጉ ነው።

#ሁከቱ ከላይ እንደሚመስለው በትናንሽ ችግሮችና ልዩነቶች የሚነሳ ሳይሆን በታቀደ መልኩ የሚከናወን፣ ድብቅ ፖለቲካዊ ዓላማ ያለው፣ ህዝብን ከህዝብ በማጋጨት ወይም ግጭቶች ሲከሰቱ እነሱን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የማባባስ እና ሃገራችንን የማያባራ ግጭት ሰለባ በማድረግ ለውጡን ለማሽመድመድና ለመቀልበስ የሚደረግ ሴራ አካል ነው።

በመሆኑም መንግስት ያለበትን የህግ የበላይነትና የዜጎችን #ደህንነት የማስጠበቅ ሃላፊነት ለመወጣት ማንኛውንም ህጋዊ፣ #የማያዳግምና
ተገቢ #እርምጃ ለመውሰድ በሙሉ ዝግጅትና አቋም ላይ እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል። ስርዓት አልበኝነትን ከዚህ በኋላ የምንታገስበት ልብ፣ የምንሸከምበት ትከሻ የለንም። በመሆኑም ለዜጎች ህይወት ዋስትና ለመስጠት መንግስት ማንኛውንም ህጋዊና የማያዳግም እርምጃ መውሰድ የጀመረ ሲሆን ይህ ሁኔታ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

#ወጣቱም በስሜት እየተገፋፋ፣ የፖለቲካ ነጋዴዎችና ዘራፊዎች መሳሪያ እየሆነ አፍራሽ ወደሆነ ድርጊት መምጣቱን መረዳት ይኖርበታል፡፡

በመሆኑም አውቆም ይሁን ሳያውቅ በህገ-ወጥ ድርጊት ላይ የሚሳተፍ ወጣትና ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል ህጋዊ እርምጃ #የሚወሰድበት መሆኑን አውቆ ከጥፋት ተግባሩ #እንዲሰበሰብ መንግስት ያሳስባል፡፡

የጥፋት ሀይሎች በሚያደርጉት የመጨረሻ መፍጨርጨር ለጊዜው የታወከው የህዝብ #ሰላም ወደ ነበረበት እንደሚመለስ መንግስት እያረጋገጠ በየትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ የደህንነት ስሜት ተሰምቶት መንቀሳቀስና መኖር እስከሚችል ድረስ፥
መንግስት ሰላምና መረጋጋትን የማስከበር ስራውን አጠናክሮ ይቀጥላል።

በዚህ ሂደት ውስጥ ወንጀሎቹን #በማቀነባበር ደረጃም ሆነ ለተቀነባበሩ ወንጀሎች መሳሪያ ሆኖ የተገኘ ሰው፣ በማንኛውም ደረጃ ወንጀል ላይ የተሳተፈ አካል ከህግ-ሊያመልጥ አይችሉም፤ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በህግ ተጠያቂ ይሆናል። በማወቅም ይሁን ባለማወቅ #ልዩነትን በሚያሰፉና ብጥብጥን በሚፈጥሩ እንቅስቃሴዎች ላይ ተሳትፎ የሚያደርጉ #አክቲቪስቶችና የፖለቲካ #ፓርቲዎች እጃሁን መሰብሰብ ይኖርባችኋል፡፡

በመጨረሻም፥ አሁን ከጀመርነው የሰላምና የዴሞክራሲ የለውጥ መንገድ ማንም ሀይል ሊያደናቅፈን እንደማይችል ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን።

መስከረም 8 ቀን 2011 ዓ.ም
የኢፌዴሪ ብሄራዊ የደህንነት ምክር ቤት
አዲስ አበባ፣ #ኢትዮጵያ

@tsegabwolde @tikvahethiopia