TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለገጣፎ ለገዳዲ‼️

በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር ሕገወጥ ናቸው ተብለው የፈረሱ ቤቶች ጉዳይ የሰሞኑ መነጋገሪያ አጀንዳ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከኦሮሚያ ክልል የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው እስከ ትናንት ምሽት ድረስ 3,800 ቤቶች ፈርሰዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ቤቶቹ #በሕገወጥ መንገድ የተሰሩ በመሆናቸው የወሰድኩት #እርምጃ ሕግን የማስከበር ሥራ ነው ብሏል፡፡

ነዋሪዎች በበኩላቸው ከ10 እስከ 19 ዓመት ቤት ገንብተው መኖራቸውን የአፈር ግብር ለመንግሥት እንደሚከፍሉና ውሃና መብራትን ጨምሮ መሰረተ ልማት የከተማ አስተዳደሩ እንዳሟላላቸው ለተለያዩ መገናኛ ብዙሃን መናገራቸው ይታወቃል፡፡ ነዋሪዎች ቤታችን በመፍረሱ ጎዳና ላይ ወድቀናል የሚል #እሮሮ እያሰሙ ነው፡፡

የኦሮሚያ ክልል የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ሃላፊውን ዶክተር #ሚልኬሳ_ሚደግሳ ሸገር 102.1 ራድዮ በጉዳዩ ዙሪየ አነጋግሯቸዋል።

Via Sheger FM 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ አዲሱ አረጋ‼️

"...ሰሞኑን #እርምጃ እየተወሰደባቸዉ ካሉ ከተሞች አንዱ በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ ነዉ፡፡ ይሁን እንጂ በማህበራዊ ሚዲያ እና በመደበኛ ሚዲያም ጭምር ህገ ወጥ ግንባታ ላይ እየተወሰደ ያለዉ እርምጃ በለገጣፎ ለገዳዲ ብቻ እየተደረገ ያለ እና #ብሄር ለይቶ #እርምጃ አስመስሎ እየቀረበ መሆኑን አስተዉለናል፡፡ ይህ #ስህተት ነዉ፡፡ እስካሁን በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ 25 ከተሞች በተደረገ እንቅስቃሴም ህግን ብቻ ባማከለ 36,117 ህገ ወጥ ይዞታዎች እና ህገ ወጥ ግንባታዎች ላይ ህግን የማስከበር ስራ ተሰርቷል፡፡"

https://telegra.ph/ህገ-ወጥ-ግንባታን-በተመለከተ-አቶ-አዲሱ-አረጋ-02-22
ሰላማዊ ሰልፍ አልተጠራም‼️

በአዲስ አበባ ከተማ እሁድ የካቲት 17/2011 ዓ/ም #በመስቀል_አደባባይ ሠላማዊ ሰልፍ ተጠርቷል በሚል በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች የተላለፈው ዘገባ ሀሰተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በነገው ዕለት ምንም ዓይነት የሠላማዊ ሰልፍ ሆነ ስብሰባ እናድርግ የሚል #ጥያቄ ያልቀረበለት መሆኑን ለኮሚሽኑ የገለፀ ሲሆን ሰልፉ በከተማ አስተዳደሩ ይሁን በፖሊስ ኮሚሽኑ እውቅና የሌለው ነው።
በመሆኑም #ሰልፍ_እንወጣለን በሚል በህብረተሰቡ ላይ የፀጥታ ችግር ለመፍጠር የሚፈልጉ አካላት ከተግባራቸው እንዲታቀቡ ኮሚሽኑ #በጥብቅ አሳስቧል።

ይህን ተላልፎ በሚገኙ አካላት ላይም የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል አስፈላጊውን ህጋዊ #እርምጃ የሚወስድ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል ፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥብቅ ማሳሰቢያ‼️

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር #በነገው ዕለት ምንም ዓይነት የሠላማዊ ሰልፍ ሆነ ስብሰባ እናድርግ የሚል #ጥያቄ አልቀረበለትም።

በመሆኑን በማህበራዊ ሚዲያ ተጠራ የተባለው ሰልፍ በከተማ አስተዳደሩ ይሁን በፖሊስ ኮሚሽኑ እውቅና የሌለው ነው።

ስለሆነም #ሰልፍ_እንወጣለን በሚል በህብረተሰቡ ላይ የፀጥታ ችግር ለመፍጠር የሚፈልጉ አካላት ከተግባራቸው እንዲታቀቡ ኮሚሽኑ #ጥብቅ_ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

ይህን ተላልፎ በሚገኙ አካላት ላይም የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል አስፈላጊውን ህጋዊ #እርምጃ_የሚወስድ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወላይታ ሶዶ🔝

መንግስት በወላይታ ሶዶ ከተማ ዙሪያ ህገወጥ ናቸው #ባላቸው ግንባታዎች ላይ የማፍረስ #እርምጃ መውሰዱን ተከትሎ የተፈጠረው አለመረጋጋት ረገብ ብሏል። ከተማዋም ወደቀደመ #ሰላማዊ እንቅስቃሴዋ እየተመለሰች ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቤንሻንጉል ጉምዝ‼️

በአሶሳ ወረዳ ከ190 በላይ የሚሆኑ የሚሊሺያ አባላት ከክልሉ መንግስት እውቅና ውጭ #ወታደራዊ ስልጠና መውሰዳቸው ተገለፀ። ይህን ባደረጉ አመራሮች ላይም ህጋዊ #እርምጃ ተወስዶባቸዋል።

በክልሉ የሰላም ግንባታና የፀጥታ ቢሮ የሚሊሺያ ዘርፍ ሃላፊ አቶ #ደርጉ_ዚያድ ለኢቢሲ እንደተናገሩት በክልሉ ደረጃ የሚሊሺያ ሰራዊትን በአዲስ መልክ ለማደራጀት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ከሰሞኑ የሚሊሺያ ሰራዊት አባላት ግምገማ የተካሄደ ሲሆን ለውጡን ማስቀጠል የሚችል የሚሊሺያ ሰራዊት መዋቅር ለመዘርጋት በሚያስችል መልኩ ግምገማ ተካሂዷል። በዚህም ከአሶሳ ወረዳ ብቻ 140 የሚሊሺያ አባላት በክብር ተሰናብተዋል። እንዲሁም ሰኔ 17 በአሶሳ ከተማ ተከስቶ በነበረው ግጭት የተጠረጠሩ 9 የሚሊሺያ አባላት በህግ #ቁጥጥር ስር ውለዋል።

በአሶሳ ወረዳ 190 የሚሆኑ የሚሊሺያ ሰራዊት ከክልሉ መንግስት እውቅና ውጭ ወታደራዊ ስልጠና ወስደዋል ያሉት አቶ ደርጉ ይህን ባደረጉ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸው ብለዋል። የክልሉን የሚሊሺያ ሰራዊት በአዲስ መልክ ለማደራጀት እየተሰራ መሆኑን አቶ ደርጉ ለኢቢሲ ተናግረዋል።

Via ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበበ የስራ ፍቃዳቸዉን ባላሳደሱ የንግድ ተቋማት ላይ ህጋዊ #እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡ በአዲስ አበበ ከተማ ዉስጥ በ2011 የንግድ ፍቃዳቸዉን ማሳደስ የሚጠበቅባቸው 251 ሺ 6 መቶ የንግድ ተቋማት ቢኖሩም፣ ፍቃዳቸዉን እስከ ታህሳስ 30፣2011 ዓ.ም ድረስ ማደስ የቻሉት ግን ከ218ሺ አይበልጡም ተብሏል፡፡

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዳንሻ ከተማ ወቅታዊ ሁኔታ‼️

ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በዳንሻ እየተስተዋለ ባለው #ግጭት የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የትግራይ ክልል መንግሥት አስታውቋል፡፡

ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በዳንሻ እየተስተዋለ ባለው ግጭት የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉ የትግራይ ክልል መንግስት ዐስታውቋል፡፡ የከተማዋ ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች በተሽከርካሪዎች ላይ እየወሰዱት ያለው #እርምጃ የተቃወሙ ወጣቶች ከፖሊስ ጋር ወደ ግጭት ገብተው እንደሰነበቱ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ግጭቱ በመስጋት የዳንሻ ነዋሪዎች ከተማዋ ለቀው በአቅራብያቸው ወደሚገኙ አካባቢዎች #መሰደዳቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

በምዕራብ ትግራይ ዞን ፀገዴ ወረዳ የምትገኘው ዳንሻ ከተማ ካሳለፍተው ሳምንት ጀምሮ ግጭት ስታስተናግድ ሰንብታለች፡፡ የአካባቢው ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች «ሕገ ወጥ» ያልዋቸው ሞተር ብስክሌቶችና ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎች መያዝ መጀመራቸው ተከትሎ በተከሰተው አለመግባባት ወደ ሁከት ገብታ የሰነበተችው ዳንሻ ከረቡዕ የካቲት 20 ጀምሮ በከተማዋ በተስተዋለ ግጭት የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡ ከሞቱት በተጨማሪ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ዜጎች ጉዳት ደርሶባቸው በተለያዩ ሆስፒታሎች እየታከሙ መሆኑ ነዋሪዎች ነግረውናል፡፡ በፖሊስና እርምጃው በተቃወሙ ወጣቶች መካከል የተከሰተው ግጭቱ እየተባባሰ መቀጠሉ ተከትሎ የከተማዋ ነዋሪዎች ዳንሻን እየለቀቁ መሆኑ ሰምተናል፡፡ በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት የሚተዳደር የነበረው በድህንነት ስጋት ምክንያት ከተማዋ ለቆ አሁን ሑመራ እንዳለ የሚናገረው ፀሐዬ የተባለ አስተያየት ሰጪ በግል ንብረቱ ጨምሮ በብዙዎች ሀብት ላይ ውድመት መድረሱ ለጀርመን ራድዮ ተናግሯል፡፡

እንደ ጀርመን ራድዮ ምንጮች መረጃ ግጭቱ ከተከሰተበት ቀን ጀምሮ የከተማዋ የመንግስት መስሪያቤቶች፣ የግል ድርጅቶች፣ የፋይናንስ ተቋማትና ሌሎች አገልግሎት አቋርጠው ሰንብተዋል፡፡ በከተማዋ ቅኝት ማድረጉ የሚናገረው ተመስገን ካሳሁን የተባለ የአይን እማኝ፡ ዳንሻ ዛሬ በአንፃራዊነት #ተረጋግታ ውላለች ብሏል፡፡ የተወሰነ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ መመልከቱም ተናግሯል፡፡

መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ግጭቱ ለማብረድ ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ከተማዋ ገብተው የነበሩ ሲሆን ከጥቂት ቆይታ በኋላ የትግራይ ልዩ ሐይል ፖሊሶች በቦታው #ተተክተዋል፡፡

የዳንሻን ጉዳይ አስመልክተን የተጠየቁት የትግራይ ክልል ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሐላፊዋ ወይዘሮ #ሊያ_ካሳ የክልሉ መንግስት ለችግሩ ትኩረት መስጠቱ ተናግረዋል፡፡ ግጭት የፈጠሩ አካላትም "ሕግ የማስከበር ተግባር የማይዋጥላቸው ጥቂት ግለሰቦች ናቸው" ብለዋል፡፡ በከተማዋ ትራፋክ ተቆጣጣሪዎች የተወሰድ እርምጃ ክልል የለየ እንዳልሆነና ሕግ የማስከበር ተግባር ብቻ መሆኑ ሐላፊዋ ለጀርመን ራድዮ ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በምዕራብ ኢትዮጵያ #የጥፋት ኃይሎች በስፋት ሲንቀሳቀሱበት የነበረውን የምዕራብ ኦሮሚያና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የምዕራብ ኢትዮጵያ ኮማንድ ፖስት በወሰደው #እርምጃ ማረጋጋት እንደተቻለ የኢፌዴሪ መከላከያ ምክትል ኢታማጆር ሹም ጀኔራል #ብርሃኑ_ጁላ ተናገሩ ። ዛሬ የምዕራብ ኢትዮጵያ ኮማንድ ፖስት በአሶሳ ከተማ ገምገማ አካሂዷል። በግምገማው ወቅት ህብረተሰቡ ከነበረበት የሥጋት ስሜት ወጥቶ በአካባቢው #ሠላማዊ በሆነ መንገድ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ተገልጿል፤ ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ማጠናከር ይገባል ተብሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፌደራል እና የአማራ ክልል የጸጥታ አስከባሪ ተቋማት #እርምጃ እንዲወስዱ ታዘዙ‼️

በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ሸዋ ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች ያለውን የጸጥታ መደፍረስ ለማረጋጋት የፌደራል እና የክልል የጸጥታ አስከባሪ ተቋማት እርምጃ እንዲወስዱ ታዘዙ። የጸጥታ ኃይሎቹ “አስፈላጊውን ህጋዊ እና #ተመጣጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ” ትዕዛዝ መተላለፉን ያስታወቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጸጥታ ምክር ቤት ነው።

ምክር ቤቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በአማራ ክልል “ከሚሴ እና በአጎራባች አካባቢዎች የተከሰተው የሰው ሕይወት መጥፋት እና የንብረት ውድመት በምንም አግባብ ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው” ብሏል። የምክር ቤቱ መግለጫ በአካባቢዎቹ በተፈጸመው ጥቃት ስለሞቱ ሰዎች ብዛት ከመጥቀስ ተቆጥቧል።

በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን እና የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አጣዬ፣ ማጀቴ እና ካራቆሬ በተባሉ ከተሞች በተፈጸመ ጥቃት የሰው ሕይወት መጥፋቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። በሰሜን ሸዋ ዞን የኤፍራታና ግድም ወረዳ መንግስት ኮሚዩንኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት “የኦነግ ታጣቂዎች” ሲል የጠራቸው ጥቃት ፈጻሚዎች በከፈቱት ተኩስ አራት ሰዎች መሞታቸውን በትላትናው ዕለት አስታውቆ ነበር። ህይወታቸው ካለፈው መካከል ሶስቱ “የከተማይቱን ሰላም ለማስጠበቅ የተሰማሩ የፀጥታ አባላት” መሆናቸውን የገለጸው የወረዳው የመንግስት ኮሚዩንኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አንደኛው በተባራሪ ጥይት ተመትቶ መሞቱን ገልጿል።

በአካባቢዎቹ የተከሰተውን ጥቃት “ብጥብጥ” ሲል የጠራው የብሔራዊ ጸጥታ ምክር ቤት “ችግሮች የሚከሰቱት የራሳቸው አጀንዳ ባላቸው ውስን የጥፋት ሃይሎች ነው” ብሏል። ምክር ቤቱ “በአካባቢዎቹ በተከሰተው ብጥብጥ ላይ “እጁ ያለበት ማንኛውም አካል በህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ” ገልጿል። ብጥብጡን ያቀናበሩት፣ ያነሳሱትና የፈጸሙ አካላትን ለህግ ለማቅረብ እንዲቻል ጥናት የሚያደርግ፣ ከአማራ ክልል እና ከፌደራል ተቋማት የተውጣጣ ቡድን ወደ አካባቢዎቹ መሰማራቱንም አስታውቋል።

መንግስት ህግን ለማስከበርና የዜጎችን ሰላም ለማስጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ ቁርጠኛ እንደሆነ የገለጸው የብሔራዊ ጸጥታ ምክር ቤት “በሕገወጥ ተግባራት ላይ የሚሳተፉ አካላት ከድርጊታቸው የማይቆጠቡ ከሆነ መንግስት ሕግን ከማስከበር ወደ ኋላ እንደማይል በድጋሚ ያረጋግጣል” ሲል አስጠንቅቋል።

ምንጭ-የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እርምጃ ተወሰደባቸው...🔝

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት አጀንሲ የትምህርት ጥራት ችግር ያለባቸውን ከፍተኛ የግል የትምህርት ተቋማት ላይ #እርምጃ ወሰደ፡፡

አጄንሲው በአዲስ አበባና በዙሪያዋ በሚገኙ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ድንገተኛ ጉብኝት በማድረግ የህግ ጥሰት ፈፅመዋል ባላቸው ተቋማት ላይ ህጋዊ እርምጃ መወሱዱን አስታውቋል፡፡

አጄንሲው የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት አጀንሲ በአዋጅ ቁጥር 650/2011 እና በሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 261/2004 ያለዉን ስልጣንና ኃላፊነት መሰረት በማድረግ ከላይ በተገለፁት የግል ከፍተኛ ተቋማማት ላይ ከእገዳ እስከ ፅሁፍ ቅጣት ማስተላለፉን ከኤጀንሲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰበር_ዜና #ባህር_ዳር

በአማራ ክልል የተሞከረው መፈንቅለ መንግስት #መክሸፉን አቶ ንጉሱ ጥላሁን ተናግረዋል። ይህንን ድርጊት በፈፀሙት ላይ #እርምጃ እንዲወሰድ ትእዛዝ ተሰጥቷል፤ እንቅስቃሴም ተጀምሯል ሲሉ ገልፀዋል።

Via #etv/#Elias_Meseret/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን በአማራ ክልል መንግስት ላይ ተሰነዘረ ያሉትን "መፈንቅለ መንግስት" አወገዙ። አሜሪካን ሀገር የሚገኙት የአዴፓ ሊቀመንበር "የፌደራል መንግስት ጉዳዩን በመከታተል አስፈላጊው #እርምጃ ይወስዳል" ብለዋል። #elu

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቁልፍ ቦታዎች በኦሮሞ ተይዟል

ቁልፍ የሚባሉ የመንግሥት የሥልጣን ቦታዎች በኦሮሞ ነው የተያዙት የሚለው አስተያየት ''ውሸት'' ነው ሲሉ አጣጥለውታል ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በዛሬው የፓርላማ ውሏቸው። ''የተከበረው ምክር ቤት፤ በእያንዳንዱ ተቋም ኦሮሞ ያልተገባ ሥልጣን ይዞ ከሆነ አጣርቶ ከእኔ ጀምሮ #እርምጃ መውሰድ ይችላል" ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ "ኦሮሞ በአንድም ቦታ ያልተገባ ሥልጣን አልያዘም" ብለዋል።

Via #BBC
🗞ቀን ሰኔ 24/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የስዋዚላንድ መንግስት የድግምትና ጥንቆላ ውድድር በሃገሪቱ ማገዱን ኤ ኤፍ ፒን ዋቢ በማድረግ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ከጥንቆላና ጥንታዊ ከሆኑ ልማዶች ጋር የተያያዘ ድርጊት የሚከውኑ ግለሰቦች ከተገኙ በህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ የሃገሪቱ የመንግሰት ቃል-አቀባይ ፐርሲ ሲመላኔ መናገራቸውን በዘገባው ተመልክቷል፡፡

በሳምንቱ መጨረሻም በሃገሪቱ የሚገኙ የድግምት ፈዋሾች የእርስ በርስ የጥንቆላና ድግምት ፉክክር ለማድረግ ቀጠሮ ይዘው እንደነበር አጃንስ ፋራንስ ፕሬስ በዘገባው ጠቅሷል።

የአፍሪካ ጋማ የተሰኘው የጥንት አባቶች ባህላዊ የፈውስ ፉክክር በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሊዘጋጅ እንደነበርም ታይምስ ኦፍ ስዋዚላንድን በዋቢነት በመጥቀስ ዘገባው አመልክቷል።

ባህላዊ ፈዋሽ የነበረው ሚስተር ጋማ እኤአ በ1982 ህልፈተ ህይወታቸው በተሰማው በዳግማዊ ሶቡዛ የንግስና ዘመን ተመሳሳይ በሆነ ውድድር ላይ ተሳትፎ ያደርጉ እንደነበርም ታይምስ ኦፍ ስዋዚላንድ አክሏል።

ንጉሱ ይህን #እርምጃ ለመውሰድ የወሰኑት አንዳንድ ሃሰተኛ ፈዋሾችን ለማጥፍት ፈልገው ይሆናል፤ ነገር ግን ይህን ትክክለኛ ውድድር ባልተደራጀ ሁኔታ መከልከል ተገቢ አይደለም ሲሉሚስተር ጋማ መናገራቸውን ዘገባው አስፍሯል፡፡

Via #BBC/#ENA
🗞ቀን ሃምሌ 4/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#GRAPHIC_CONTENT ከላይ በፎቶው የምትመለከቱት ኢትዮጵያዊ ዜጋ በፖሊሶች የተያዘበት መንገድ በርካቶችን አስቆጥቷል፤ በርካቶች በማህበራዊ ሚዲያ እየተቀባበሉት ነው፤ በርካቶችም ድርጊቱን አውግዘዋል።

በዛሬው ዕለት የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ስለጉዳዩ ተጠይቆ ይህን ምላሽ ሰጥቷል፦

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ፅህፈት ቤት ሃላፊ ኮማንደር #ታዬ_ግርማ  ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ችግር እንደተፈጠረ ተደርጎ በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተሰራጨ ስላለው ምስል በኮሚሽኑ በኩል በትክክል አለመረጋገጡን ተናግረዋል። ከዚህ ባለፈ ግን ችግሩ በማን እና እንዴት እንደተፈጠረ #እያጣራ እንደሚገኝም ነው የገለጹት። የክልሉ ፖሊስ ለኦሮሞ ህዝብ አለኝታውና መከታው ሆኖ በርካታ ችግሮችን እየተጋፈጠ ሲታገል የቆየና አሁንም በዚያው ቁርጠኝነት እያገለገለ እንዳለም አስረድተዋል፡፡ ድርጊቱ የክልሉን ፖሊስ ስም ለማጥፋት የተፈጸመ በመሆኑ የፖሊስ ኮሚሽንም ይሁን ሌላ አካል ጉዳዩን በፈጸሙ አካላት ላይ #እርምጃ እንደሚወስድ ገልጸዋል። በምስሉ ላይ የሚታዩ ግለሰቦችንም የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽንን የደንብ ልብስ ከመልበሳቸው ውጭ ማንነታቸውን ማረጋገጥ እንዳልተቻለም ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Qatar

- የኳታር አሚር በትላንትናው እለት ለበርካታ የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አድርገዋል።

- በረመዳን የፆም ወቅት የመንግስት ሰራተኞች በቀን አራት ሰዓታት ብቻ (ከ 9:00 AM - 1:00 PM) እንዲሰሩ፤ በግል ተቋማት የሚሰሩ ሰራተኞች ደግሞ በቀን ለስድስት ሰዓታት (ከ 9:00 AM - 3:00 PM) እንዲሰሩ ተወስኗል። ሆኖም ውሳኔው ምግብ ነክ ምርቶችን የሚያቀርቡ ሱቆችን፣ ፋርማሲዎችን እና በትዕዛዝ የሚሰሩ ምግብ ቤቶችን አይመለከትም።

- ማንኛውም ነዋሪ ወደ ሱቆች፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ እንዲሁም የህዝብ እና የግል ቢሮዎች ሲሄዱ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ የማድረግ ግዴታ አለባቸው። ይህን ውሳኔ ተላልፎ የሚገኝ ግለሰብ ህጋዊ #እርምጃ ይወሰድበታል።

- ከImam Muhammad ibn Abd al-Wahhab መስጅድ በስተቀር ሁሉም መስጅዶች ዝግ ሆነው ይቆያሉ።

(የኢትዮጵያ ኤምባሲ-ዶሃ)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#FDREDefenseForce

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሐመድ በሕዝቦች መካከል ቁርሾ እና ግጭት በመፍጠር ፣ በሃይማኖትና በተለያዩ ምክንያቶች ሰዎችን እየፈረጁ ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት የሚደረጉ ሴራዎች ካሁን በኋላ ቦታ አይኖራቸውም ሲሉ አስታውቀዋል።

ሕዝብን ከሕዝብ ጋር የሚያጋጩ ፤ ሃይማኖትን ከሃይማኖት የሚያጋጩ ፤ ጎሳን ከጎሳ የሚያጋጩ ስራዎች ሆነ ተብለው የሚሰሩ ከሆነ ፤ አድገው ወደ ዘር ማጥፋት ፣ ወደ እልቂት የሚያመሩ በመሆኑ መንግስት #እርምጃ ይወስዳል ሲሉ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሐመድ ከአዲስ ዘመን ጋር በነበራቸው ቆይታ የሰራዊቱ ወታደራዊ ቁመና የአገሪቱን ሉዓላዊነት እና የሕዝቡን ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ መጠበቅ የሚያስችል እንደሆነም አመልክተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
የታክሲዎች አድማ በአዲስ አበባ ፦

(በአል-ዐይን - AlAIN)

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ተሳፋሪዎች ከፍተኛ የትራንስፖርት እጥረት ገጥሟቸዋል።

ተሳፋሪዋች በታክሲ እጦት ሲንገላቱ ነበር፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከወትሮው የተለዩ ረጃጅም ሰልፎች ተስተውለዋል፡፡

‘ታሪፍ አነሰን’ እንዲሁም ‘በትራንስፖርት ተቆጣጣሪዎች የተጋነነ ቅጣት እየተቀጣን ነው’ በሚሉ ምክንያቶች አድማ የመቱ ታክሲዎች መኖራቸው ተሰምቷል።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር ስጦታው አከለ “የተወሰኑ ባለታክሲዎች ዛሬ ወደ ስራ እንዳልገቡ እናውቃለን” ብለዋል፡፡ “የታክሲ ባለቤቶች ታሪፍ እንዲሻሻልላቸው ጠይቀውናል ፤ በዚህም የህዝብን የመክፈል አቅም እና የነዳጅ ዋጋን ታሳቢ ያደረገ ማሻሻያ ተደርጓል” ሲሉ ገልጸዋል።

ይሁንና ከላይ ከተቀመጡት ምክንያቶች ውጭ “ዝም ብለን የታሪፍ ማሻሻያ አናደርግም” ያሉት ኃላፊው “በዛሬው አድማ ላይ በተሳተፉት ላይ #እርምጃ እንወስዳለን” ሲሉ ተናግረዋል።

በአድማው የተሳተፉት “ጥቂት ታክሲዋች ናቸው” ያሉት ኃላፊው በከተማው የትራንስፖርት ችግር እንዳይፈጠር ፐብሊክ ባስ፣ ሸገር ባስ እና ድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶችን በስፋት በመጠቀም ላይ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia