TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አዲስ የአስተዳደር መዋቅር ጥናት⬇️

የደቡብ ክልል አዳዲስ #የዞንና #የወረዳ አወቃቀር ምክረ ሐሳብ የያዘ ጥናት አጠናቅቆ ለአመራሮች ውይይት እንዳዘጋጀ ታወቀ፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) ሊቀመንበርና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወ/ሮ #ሙፈርያት_ካሚል ነሐሴ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፣ ክልሉ አዲስ አወቃቀር እንደሚኖረው የመንግሥት አገልግሎትን ለወረዳ ማዕከላት ቅርብ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ እንዳለ ገልጸው ነበር፡፡

አፈ ጉባዔዋ በወቅቱ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፣ ‹‹በጥናት የተለየና ሕጋዊ ሥርዓቱን ተከትሎ ወደ ተግባር የሚገባበት የመዋቅር ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱም ሕዝቡን ባወያየንበት ወቅት የነበረው ዋናው ጥያቄ የአገልግሎት ጥያቄ ነው፡፡ በጥናት አገልግሎት ወደ ኅብረተሰብ ማቅረብ አቅደናል፤››  ብለው፣ ‹‹በመንግሥታዊ መዋቅሩ ይኼንን በሕግ አግባብ ዳር ለማድረግ ምላሽ መስጠት ጀምረናል፤›› ሲሉም የደረሰበትን ደረጃ ማስረዳታቸው ይታወሳል፡፡

በዚህም መሠረት ካሁን በፊት #ልዩ ወረዳ የነበረው አላባ ወደ ዞንነት ሲያድግ ዌራ ዙሪያ፣ ድጆ ዌራና ድጆ የተባሉ ወረዳዎች ይኖሩታል፡፡ የወረዳዎቹ ማዕከላት በቅደም ተከተል ቁሊቶ፣ ጉባና የቤሻኖ ከተሞች እንዲሆኑ ጥናቱ ያሳያል፡፡

በሌላ በኩል ካሁን በፊት ከነበረው ጋሞ ጎፋ ዞን፣ ጎፋ ራሱን ችሎ በመውጣት ዞን በመሆን በሥሩ ስምንት ወረዳዎች እንዲኖሩት የሚል መዋቅር ተዘጋጅቷል፡፡ በዚህም መሠረት ጎፋ ዞን ዲምባ ጎፋ፣ ባዜ ጎፋ፣ ዛላ፣ ኡባ ደብረ ፀሐይ፣ አይደ ወረዱ፣ ሳውላ ከተማ፣ መለኮዛና ጋደ የተባሉ ወረዳዎች እንዲኖሩት በጥናቱ ተመልክቷል፡፡

ለብቻው እንደ አዲስ የተዋቀረው ጋሞ ዞን ደግሞ 13 ወረዳዎች እንዲኖሩት እንደሚደረግ የሚጠቁመው ጥናቱ፣ አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ፣ ዲታ፣ ካምባ፣ ምዕራብ አባያ፣ ጨንቻ፣ ደራማሎ፣ ቁጫ፣ ቦንኬ፣ ቦረዳ፣ አርባ ምንጭ ከተማ፣ ምዕራብ ቁጫ፣ ሰሜን ቦንኬና ጋርዳ ማርታ የተባሉ ወረዳዎችን ያቀፈ ሆኖ እንዲቋቋም ሐሳብ ቀርቧል፡፡

በተመሳሳይ ኮንሶ ከሰገን ሕዝቦች ዞን ወጥቶ በዞንነት እንዲደራጅ በጥናቱ የተመለከተ ሲሆን፣ በሥሩም ካራት ዙሪያ፣ ከና፣ ሰገን ዙሪያና ካራት ከተማ አስተዳደር የሚሉ የወረዳ መዋቅሮች እንደሚኖሩት ተጠቁሟል፡፡

ጥናቱ ካሁን በፊት የሰገን ሕዝቦች ዞን አስተዳደር በሚል ስያሜ ተዋቅሮ የነበረው አደረጃጀት ወደ ቀድሞው ተመልሶ የአማሮ ልዩ ወረዳ፣ የቡርጂ ልዩ ወረዳ፣ የዴራሼ ልዩ ወረዳና የአሌ ልዩ ወረዳዎች ተብለው እንዲቋቋሙ የሚል ይዘት አለው፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጌዴኦ‼️

የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ #ሙፈርያት_ካሚል ከአጎራባች አካባቢ ተፈናቅለው በጌዲኦ ዞን ገደብ ወረዳ ተጠልለው የሚገኙ ዜጎችን #እየጎበኙ ነው፡፡ ሚኒስትሯ በገደብ ወረዳ ገደብ ስታዲየም የተጠለሉትን እነዚህን ተፈናቃዮች አጽናንተዋል፡፡ መንግስት ዘላቂ መፍትሄ ለማበጀት እየሰራ ያለውን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም በዚህ ወቅት ገልጸዋል፡፡ ሚኒስትሯ ከተፈናቃይ ተወካዮች ጋር እንደሚወያዩም ይጠበቃል፡፡ በአሁኑ ወቅት በገደብ ወረዳ ከ96ሺ በላይ ተፈናቃዮች ተጠልለው እንደሚገኙ ታውቋል፡፡

ምንጭ፡- ኢ. ዜ. አ
@tsegabwolde @tikvahethiopia