#update የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 ለመተካት በረቂቅነት በተዘጋጀው "የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና መቆጣጠር " አዋጅ ላይ በኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል ውይይት በመደረግ ላይ ነው። በሥራ ላይ ያለው አዋጅ በዋናነት ትኩረት ያደረገው መንግሥትን ብቻ መከላከል ላይ ያተኮረ በመሆኑ፣ ስያሜውም መሻሻሉን ረቂቁ ያስረዳል። በሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ ትኩረት ያደረገው ረቂቁ በተጠርጣሪ ላይ ያለአግባብ ምርመራና ዳኝነት በሚሰጡ ላይ #ተጠያቂነትን ይጥላል። በተከፈተው የምርመራ መዝገብ ለተጠርጣሪው ከ1,000 ብር እስከ 50,000 ብር #የሞራል_ካሳ ክፍያ ውሳኔ እንደሚሰጥም ይደነግጋል።
Via ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ፍፁም አረጋ...
"ከባለቤቴ እና ከ3 ወንድ ልጆቼ ጋር በመመካከር አንዲት የ3 ሳምንት ህጻን ልጅ የማሳደግ ዕድል ስላገኘን ትልቅ #ደስታ ተሰምቶናል። ላገኘነው ዕድል የአዲስ አበባ የሴቶች እና ህጻናት ቢሮን እንዲሁም የክበበ ጸሃይ ህጻናት ማሳደጊያን ከልብ እናመሰግናለን። ልጆች ከቤተብ ጋር በፍቅር ማደግ አለባቸው እንላለን። የምትችሉ ሁሉ ወላጅ የሌላቸውን ወላጅ ሁኑላቸው። ውሰዱና በፍቅር አሳድጉ። ይህንን በማድረግ አርዓያ የሆናችሁንን ሁሉ እናመሰግናለን።"

...ቃሊቲ በእሳት #እየጋየች ነው❓ እንዲህ ያሉ በፌስቡክ የሚሰራጩ ዜናዎችን #ሼር ባለማድረግ ሀገራዊ ሀላፊነታችንን እንወጣ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በ23 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል‼️
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አማጋ የስፖንጅ ፋብሪካ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 23 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደረሰ፡፡
በእሳት አደጋው ጉዳት ከደረሰባቸው ሰዎች መካካል ስምንቱ የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን ሰራተኞች ናቸው።
15ቱ ደግሞ የፋብሪካው ሰራተኞች መሆናቸውን የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባላስልጣን የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ተናግረዋል፡፡
አደጋው የደረሰው በአቃቂ ቃሊቲ ክፍል ከተማ ወረዳ አምስት የኢንዱስተሪ ዞን አማጋ የስፖንጅ ፋብሪካ ላይ መሆኑን አቶ ንጋቱ ገልጸዋል፡፡
በአደጋው አብዛኛው ፍብሪካው ክፍል መውደሙን የገለጹት የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያ ፋብሪካው የሚጠቀማቸው ግብዓቶች ተጠቀጣጣይ መሆናቸው አደጋውን አባብሰውታል ብለዋል፡፡
አደጋው 4 ሰዓት ተኩል ላይ የተከሰተ ሲሆን÷ 11 ተሽክርካሪዎችን፣ ሁለት አምቡላንሶችን፣ 85 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችን ያሰማራው ባለስልጣኑ በ4 ሰዓታት ውስጥ እሳቱን ለመቆጣጠር ችሏል፡፡
98 ሺህ ሊትር ውሃ፣ 25 ሺ ሊትር ኬሚካል እሳቱን ለማጥፋትና ለመቆጣጠር አግልግሎት ላይ ውሏል፡፡
ምንጭ፦ ፋና

ሲአን‼️
ተፎካካሪው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን ) የሲዳማ ህዝብ ለረጅም ጊዜ የታገለለትን እራስን በእራስ የማስተዳደር ጥያቄን ለመመለስ የሚጠበቀው ህዝበ ውሳኔ ያለምንም እንቅፋት ገቢራዊ እንዲሆን ጠየቀ። ሲአን ጥያቄውን ያቀረበው ዛሬ ሀዋሳ ውስጥ በንቅናቄው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ በአቶ ደሳለኝ ሜሳ በተነበበው መግለጫው ነው።
ንቅናቄው የክልሉ ገዥ ፓርቲ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክሪያሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) የህዝበ ውሳኔውን ሂደት እያጓተተ ነው ሲልም ወቅሷል።
ደኢህዴን በአስፈጻሚ ተቋማት ላይ ያደርጋል ያለው ጣልቃ ገብነትም የሕገ-መንግሥት የበላይነትን የሚጥስ ነው ብሏል። ከዚህ ሌላ በቅርቡ የሚካሄደው አራተኛው አገር አቀፍ የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ንቅናቄው ከዚህ ቀደም ተደርጓል እንዳለው የሲዳማ ዞንን እና የሀዋሳ ከተማን በሚነጣጥል መልኩ ሊካሄድ አይገባም ሲል ገልጾ ቆጠራውን የሚያስፈጽመው አካል ጉዳዩን ከወዲሁ እንዲያጤነው ሲአን አሳስቧል።
ምንጭ:- የጀርመን ራድዮ

#update የዘንድሮ 123ኛ የአድዋ ድል በዓል “የአድዋ ድል የአንድነታችን ማህተም” በመል መሪ ቃል በመላው አገሪቱ በድምቀት እንደሚከበር የኢፌድሪ ባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል። የአድዋ ድል በዓልን ለመዘከር ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ ከ200 በላይ የሚሆኑ የስራ ሃላፊዎች፣ ታዋቂ ግለ ሰቦች፣ የአባት አርበኞች ተወካዮች የተካተቱበት የልኡካን ቡድን ታሪካዊ ቦታዎችን እየጎበኘ እየጎበኘ እንደሚገኝም ተገልጿል።
Via ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥቆማ‼️
በሳነቴ ተራራ ከትላንት ጀምሮ የእሳት ቃጠሎ ይታያል የሚመለከተው አካል አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈልግ ጥሪ ቀርቧል።
@tsegabwilde @tikvahethiopia

ወንጀል ነክ መረጃ‼️
#የማታለል_ወንጀል የፈጸመው የዓባይ ባንክ ሠራተኛ በእስራትና ገንዘብ ተቀጣ። ተከሳሽ በረከት በርሄ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 696/ሐ የተመለከተውን ክልከላ በመተላለፍ አባይ ባንክ አክሲዮን ማህበር ለሰራተኞቹ የሚሰጠውን የቤት መግዣ እና የመስሪ ቦታ ብድር አገልግሎት ለመጠቀም በማሰብ በሌላ ሰው ተመዝግቦ የሚገኝን መኖሪያ ቤት እንደ መያዣ አድርጎ በማቅረብ 656,774 ብር ከባንኩ ወስዷል፡፡
ተከሳሽ ማስገመት የሚገባው የመኖሪያ ቤት ዋጋ 441,696.87 ብር ሆኖ ሳለ ባንኩን በማሳሳት የሌላ ሰው የሆነ ቤትን በ656,774 ብር በማሰገመት ባንኩ 173,235 ብር እንዲያጣ ያደረገ በመሆኑ በፈጸመው ከባድ የማታለል ወንጀል ተከሷል፡፡
ዐቃቤ ህግም በጉዳዩ ላይ ያስረዱልኛል ያላቸውን ማስረጃዎችን አጠናቅሮ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛ ወንጀል ችሎትም የካቲት 19 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት ግለሰቡ በ3 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራትና በ17,000 ብር እንዲቀጣ ወስኗል።
ምንጭ፦ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ

የአድዋ ድል በአልን ምክንያት በማድረግ በ #6Kilo_Intellectual_Society የሚዘጋጅ የ 3ቀናት ዘመቻ[Activism]
____
➊በጫማ ጠረጋ (ሊስትሮ) የሚደረግ የገቢ ማሰባሰቢያ፦ ገቢው የሚሰበሰበው በተመረጡ የከተማችን አካባቢወች ሲሆን ከ ሰበታ አጃምባ ተፈናቅለው ዓለም ባንክ ለሚገኙ ተጎጂዎች የሚደረግ በጎ ፈቃደኞች የሚከናወን ለ3 ቀናት የሚቆይ የጫማ ጠረጋ (ሊስትሮ) ዘመቻ ነው፡፡
➋መጽሐፍ ማሰባሰብ፦ ይህም ዘመቻ በደቡብ ክልል በወራቤ ከተማ ለሚገኘው ወራቤ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ቤተ መጽሐፍት ሁሉም ሰው ለ 3 ቀናት አድዋን በማሰብና የተለያዩ መጽሐፍትን በበጎ ፈቃደኝነት በማበርከት የእንቅስቃሴው አካል የሚሆንበት ነው፡፡
➌ዘረኝነትን የመቃወም ዘመቻ፦
ዘመቻው ‹‹ ዘረኝነት›› ፣ ‹‹ጥላቻ›› … የሚሉ ፅሁፎችን በተመረጡ የከተማችን አካባቢዎች በሚቀመጡ የቆሻሻ ቅርጫቶች ውስጥ በመጣል ሁሉም የሚሳተፍበት ትዕይንት ነው፡፡
•
ማሳሰቢያ፦
1- በጫማ ጠረጋው ላይ ለመሳተፍና ተጎጂዎችን መርዳት የምትፈልጉ በውስጥ መስመር አነጋግሩን፡፡
2- መፅሐፍት በመለገስ መሳተፍ የምትፈልጉ
•ፒያሳ አራዳ ህንፃ ዋው በርገር
•ሜክሲኮ ጃዕፋር የመፅሐፍት መደብር
•አራት ኪሎ ሮሚና
• እንዲሁም በአካል ለአስተባባሪዎቹ መስጠት ትችላላችሁ፡፡
መቀላቀል የምትፈልጉ፦
0983007703
0938077868
0918511580 ደውሉልን፡፡
#ዕውቀት_ነፃ_ያወጣል!
#አዘጋጆቹ
#Share

ሮፍናን "የኔ ትውልድን" ኮንሰርት ቅዳሜ የካቲት 23 በድጋሚ
♦️በጥሪ ብቻ♦️
ቅዳሜ የካቲት 16 በተደረገው የሮፍናን 'የኔ ትውልድ' ኮንሰርት ላይ ሜዳ ቻት የዝግጅቱ አጋር በመሆን ከኮንሰርቱ በፊት ትኬቶችን ለታዳሚያን በቀላሉ ከመሸጥ ጀምሮ በዝግጅቱ ውስጥ ደሞ በርካታ ሽልማት የሚያሸልሙ ጨዋታዋችን በአፑ በማድረግ ለዝግጅቱ ድምቀት ሆኖ አልፏል።
ሆኖም የዝግጅቱ ቦታ አቅም ከሚፈቅደው በላይ ሰው በመምጣቱ እና በር ላይ በተፈጠረው ግርግር እና እንግልት ምክንያት ለአጠቃላይ ደህንነት ሲባል በፀጥታ ሀይል በር መዘጋቱ ይታወቃል።
ስለዚህ በሜዳ፣ አሞሌ ሞባይል ገንዘብ እናም በሁሉም ዳሽን ቅርንጫፍ ትኬት ቆርጣችሁ ወደ ውስጥ ሳትገቡ ለተመለሳችሁት ብቻ "የኔ ትውልድ" መጭው ቅዳሜ ለመድገም ከሮፍናን ከአሞሌ እና EML Events ጋር ተዘጋጅተናል::
የቦታውና የሙሉ ሁኔታ ዝርዝር ከዛሬ ጀምሮ ትኬት በገዛችሁበት ስልክ ቁጥራቹህ በመልዕክት እና በሜዳ አፕ ይደርሳቹሀል::
@myamole @medachat @Rophnan @EMLEvents

ድርና ማግ!
#የብሩክ_ከድር መፅሃፍ-በቅርብ ቀን በገበያ ላይ ይውላል!
የኢትዮጵያውያን የታሪክ ጉዞ አሁን እስካለንበት የፖለቲካ መድረክ ድረስ የመጣንበት መንገድ ያለው አንድምታና እውነተኛ ገፅታዎቹ፤ የታሪክ ፀሃፊያን ገፅታና #በኢትዮጵያዊነት ላይ ያሳደሩት ተፅእኖ፤ የስልጣኔዎቻችንና አሻራዎቻችን ባለቤቶች እነማን ናቸው፤ የሃገር ምስረታ ሂደታችን ምን ይመስላል፤ በሃገር ባለቤትነት ዙርያ የነበሩ ዳርና ዳር አስተሳሰቦችና ይዘውት የመጡት #መዘዝ ምንድን ነው፤ የዜግነት ፖለቲካና የማንነት ፖለቲካ የሰሜንና የደቡብ ፖለቲካ መሃከል ያለው #ፍትጊያ አመጣጡና መዘዙ የወደፊት ጉዟችን፤ እጅግ ድንቅና በሳል ሁለንተናዊ እይታ የተላበሰና ሰፊ ምርምር የተደረገበት ፅሁፍ፤ የመጣንበትን መንገድ በሚዛናዊ እና ትክክለኛ መንገድ እንድናይ እንዲሁም ከገባንበት የፖለቲካ ቀውስ ሊያወጣን የሚችል የመፍትሄ አቅጣጫዎች የተመላከቱበት በወጣቱና እጅግ ባለተሰጥኦው ወጣት ብሩክ ከድር ቀርቦላችኋል፡፡ ሁሉም ሰው በእጁ ሊኖረው የሚገባው የታሪክ የፖለቲካና ማህበራዊ ጉዳዮች ሰነድ፡፡
በቅርብ ቀን!
@taegabwolde @tikvahethiopia