TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ከ36 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የአርሲ ኔጌሌ ሆስፒታል በዛሬው ዕለት ተመርቋል፡፡ በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የክልሉ ምክትል ፕሬዝደንት እና የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ ወ/ሮ #ጠይባ_ሀሰን ተገኝተዋል፡፡ በሆስፒታሉ የህክምና መርጂያ ቁሳ ቁሶችን ለማሟላት 28 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል፡፡

ምንጭ፡- OBN አማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ታራሚዎች እስር ቤት ቆፍረዉ አመለጡ‼️
.
.
ትናንት የካቲት 20 ቀን 2011 ዓ. ም ዳባት ከተማ በሚገኝ እስር ቤት በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው በእስር ላይ የነበሩ ታራሚዎች የእስር ቤቱን ግድግዳ #በመቆፈር ማምለጣቸውን የሰሜን ጎንደር ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ምክትል ኮማንደር #ደሴ_ሙሉዬ ለቢቢሲ ተናገረዋል።

እንደ ኮማንደሩ ገለጻ እስር ቤቱ ስላረጀ በቀላሉ የሚሰበርና የሚቆፈር በመሆኑ ታራሚዎቹ ሰብረው መውጣት ችለዋል።

ካመለጡት እስረኞች መካከል ሁለቱ #በግድያ የተጠረጠሩና ጉዳያቸው በምርመራ ሂደት ላይ ያነበረ መሆኑን ምክትል ኮማንደሩ ገልጸዋል። ሌሎቹ አስራ አምስት እስረኞች ግን በሌሎች ወንጀሎች የተጠረጠሩ ናቸው።

እስር ቤቱ ውስጥ በአጠቃላይ 25 እስረኞች የነበሩ ቢሆንም ሌሎቹ ስምንት ሰዎች እንዳላመለጡ ያብራሩት ምክትል ኮማንደር ደሴ፤ "ስምንቱ ሰዎች የማምለጥ እድል ቢኖራቸውም ሕግን በማክበር በእስር ቤቱ ቆይተዋል" ብለዋል።

ምክትል ኮማንደር ደሴ "እስረኞቹ ከተለያዩ ቀበሌዎች የመጡ በመሆናቸው በአንድ ላይ የመሆን እድል የለም። #የተባበሩት ከእስር ማምለጥን ግብ አድርገው ነው" ሲሉ አስረድተዋል።

በግድያ ከተጠረጠሩት ውጪ ሌሎቹ አርሶ አደሮች እንደሆኑ ጨምረው ተናግረዋል። ታራሚዎቹ በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት ባስመዘገቡት አድራሻ መሰረት ወደ መኖሪያ አካባቢያቸው በመሄድ እንደሚያዙ ተናግረዋል። በወቅቱ ተረኛ የነበሩ የፖሊስ አባላትም ሃላፊነትን ባለመወጣት እንደሚጠየቁም አክለዋል።

እስረኞቹ እንዲያመልጡ ከውጭ #እርዳታ ስለመደረጉ የተጠየቁት ምክትል ኮማንደር ደሴ፤ "እስር ቤቱ የተቆፈረው ከውስጥ ነው። ምንም አይነት የውጪ እርዳታ አልተጨመረበትም" ብለዋል።

ያላመለጡት ስምንት ታራሚዎች ነገሩን ባሉት መሰረት፤ ያመለጡትን እስረኞች ያስተባበረው በዳባት ከተማ በወንጀል ተጠርጥሮ የታሰረ ወጣት ነው።

በእስረኛው ሃሳብ አመንጪነት ያረጀውን ግድግዳ በመስበርና ትንንሽ የዲንጋይ ካቦችን በመናድ ሊያመልጡ መቻላቸውን ምክትል ኮማንደር ደሴ ገልጸዋል።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአሁን ሰዓት #ፌስቡክ በኢትዮጵያ፦

•የስድብ እና የጥላቻ መድረክ
•የሀሰት መረጃ መፈብረኪያ
•የጦርነት መቀስቀሻ
•የክፋት እና ተንኮል መጠንሰሻ
•ህዝብ መከፋፈያ
•ደም ማፋሰሻ
•በብሄር ተቧድኖ መሰዳደቢያ
•ሀገር ማተራመሻ
•ሰላም ማደፍረሻ....የሆነ ማህበራዊ ሚዲያ ሆኗል።

ያሳዝናል‼️

መፍትሄው ምን ይሆን?? በቃ በዚሁ ነው የምንቀጥለው?? ስድብ፣ ጥላቻ፣ የጦርነት ቅስቀሳ የኛ መገለጫ ሆኖ ይቀጥላል?? ወገኖቼ የፌስቡክ አጠቃቀማችን በዚህ ከቀጠለ እመኑኝ ሀገር ያሳጣናል።

•እኛ #ከሩብ_ሚሊዮን የምንልቅ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በዚህ ጉዳይ ተነጋግረን አንዳች ነገር ላይ መድረስ ይኖርብናል። እኛ ሀላፊነታችንን እንወጣ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን🔝

በአዲስ መልክ በመሰራት ላይ ባለው የኮተቤ ካራ የመንገድ ፕሮጀክት በግንባታ ላይ ያለ ድልድይ አርማታ እየተሞላ ባለበት ወቅት ድልድዩን ለመስራት የሚያግዝ መወጣጫ የካቲት 11 ቀን 2011 ዓ.ም በመደርመሱ በሰራተኞች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ ጉዳት እንዲደርስ #ምክንያት ሆኗል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ ስራ ተቋራጭ ተክለ ብርሀን አምባዬ ኮንስትራክሽን የተጎጂዎችን ህይወት ለማትረፍ የተሳተፉ አካላትን #ለማመስገን ባዘጋጀው ፕሮግራም በተጎጂዎቹ ላይ የሞትና ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ የአካባቢው ማህበረሰብ፣ የፖሊስ አባላት፣ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ሰራተኞች፣ የህክምና ባለሙያዎች እና ሌሎች የህብረተሰብ አካላት ከፍተኛ ርብርብ በማድረጋቸው ከፍተኛ #ምስጋና አቅርቧል፡፡

በአደጋው በአንድም ሰው ላይ የሞት አደጋ እንዳልደረሰ እና የተጎዱ ሰራተኞች የህክምና እርዳታና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኙ ያሥታወቀው ስራ ተቋራጩ አደጋው ባጋጠመበት ወቅት የአካባቢው ነዋሪዎችና የተለያዩ አካላት አፋጣኝ ትብብር ማድረጋቸው የከፋ ችግር እንዳይፈጠር አስችሏል ብሏል፡፡

የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ #ሰይፉ_አምባዬ በአደጋው እና በደረሰው ጉዳት በጣም አዝነናል፤ የአደጋው ምንጭም በገለልተኛ አካል እየተጠና ይገኛል ብለዋል፡፡

በምስጋና ፕሮግራሙ ላይ የተገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችም በቀጣይ ተመሳሳይ አደጋዎች እንዳይደገሙ ስራ ተቋራጮች ቅድመ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ሞገስ ጥበቡ በበኩላቸው የስራ ላይ አደጋዎች ባለስልጣኑን እንደሚያሳስበው ገልፀው መንገድ የምንገነባው ለህብረተሰቡ ልማትና ዕድገት በመሆኑ ስራዎች ሲከናወኑ የህብረተሰቡንና የሰራተኞችን ደህንነት ማዕከል አድርገው መሆን አለበት ብለዋል፡፡

ኢ/ር ሞገስ አክለውም የኮተቤ ካራ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ መጓተቱ በአካባቢው ማህበረሰብ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ጫና እየፈጠረ በመሆኑ የግንባታ ስራውን ማጠናቀቅ በሚቻልበት ዙሪያ ከስራ ተቋራጩ ጋር በልዩ ሁኔታ ተነጋግረን ስምምነት ላይ ደርሰናል ብለዋል፡፡

በመጨረሻም ኢ/ር ሞገስ በድልድዩ ስራ ያጋጠመው አደጋ መንስኤ ጥናት እንደተጠናቀቀ ለህብረተሰቡ ይፋ የሚደረግ መሆኑን ገልፀው ጉዳት የደረሰባቸው ሰራተኞች ወደ ጤንነታቸው እንዲመለሱ አስፈላጊ የሚባለውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለግራፊክስ ዲዛይነሮች ደስ የሚል አጋጣሚ
# ድ ድ ር
እስከ የካቲት 23 ቅዳሜ 6፡00 ድረስ
@Amanuelme በተጠቀሰው ሊንክ በመላክ ይሳተፉ ይሸለሙ
የውድድሩ ርዕስ ፡ #የአድዋ_ድል
#አድዋ

@Tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፋ መሀመድ የተመራው የኢትዮጵያ ልኡክ ከሶማሊ ላንድ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሙሴ ባሂ አብዲ ጋር ተወያይቷል። በሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፋ መሀመድ የተመራው የኢትዮጵያ ልኡክ በሶማሊ ላንድ ጉብኝት እያደረገ ባለበት ወቅት ነው ከአስተዳደሩ ፕሬዚዳንት ጋር ተገናኝተው የተወያዩት።

Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ #ነገ የካቲት 22 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ አበባ ይገባሉ።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የካቲት 21/2011 ዓ.ም

በወላይታ ዞን አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት፦

በወላይታ ዞን በተለይም በሶዶ ከተማ ህግን የማስከበርና የህዝቡን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የዞኑ አስተዳደር እና የሶዶ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት በወቅታዊ የሶዶ ከተማ ፀጥታ ዙሪያ ለአካባቢው ሚዲያዎች ትናንት ማምሻውን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ እንዳሉት የወላይታ ሶዶ ከተማ ሰባት የመግቢያና መውጫ በር ያላት፣ በፈጣን ዕድገት ውስጥ የሚትገኝ ከተማ በመሆኗ በርካታ ግለሰቦች በከተማዋ ውስጥ በህገወጥ መንገድ ግንባታ በማከናወን የቤት ባለቤት ለመሆን ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

በሰኔ 8/2010 ዓ.ም በከተማው የተፈጠረውን የፀጥታ መደፍረስ መነሻ በማድረግ የህግ የበላይነት የማይከበርበት ከተማ አድርጎ በመቁጠር በርካታ ግለሰቦች ህገወጥ ግንባታ ፈጽመዋል ብለዋል፡፡

በተለይም በቅርቡ ወደ ከተማ የተካለሉ ቀበሌያት ላይ እየተፈጸመ ያለው ህገወጥ ቤቶች ግንባታ አሳሳቢ በመሆኑ ህብረተሰቡ ከህገወጥ ድርጊቶች ሊቆጠብ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በህገወጥ መንገድ የተገነቡ ቤቶችን ለማፍረስና የህግ የበላይነትን ለማስከበር በየደረጃው ያሉ ምክር ቤቶች በወሰኑት ውሳኔ እና በየቀበሌው በህገወጥ መንገድ የተገነቡ ቤቶች መፍረስ እንዳለባቸው ህዝቡ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት እርምጃው እየተወሰደ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የሶዶ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ኢንስፐክተር ጥበቡ ዳዊት እንደገለጹት በሀገራችን እየመጣ ያለውን የለውጥ እንቅስቃሴ ተከትሎ የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ከህብረተሰቡ ጋር በተደረገው ውይይት በከተማው አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን ተችሏል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ እጅግ በጣም ሰፊ፣ የንግድ ማዕከል እና በፍጥነት እያደገች የሚትገኝ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ አንዳንድ ደላሎች ህብረተሰቡን በማታለልና የቀበሌ አመራሮችም ጭምር እንዲሳተፉ በማድረግ በከተማው ክልል በርካታ ህገወጥ ግንባታ እንዲካሄድ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

እነዚህን በህገ ወጥ መንገድ ቤቶችን የገነቡ ግለሰቦች በግብረ ኃይል ከመፍረስ አስቀድመው በራሳቸው ፈቃድ እንዲያፈርሱ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ በመሠራቱ በርካቶች በራሳቸው ፈቃድ ማፍረሳቸውን ኢንስፐክተሩ አስታውቀዋል፡፡

ባልፈረሱ ህገ ወጥ ቤቶችን ለማፍረስ ግብረ-ኃይሉ ሲሄድ አንዳንድ ግለሰቦች ሁከት ለመፍጠርና መንገድ ለመዝጋት ሙከራ አድርገዋል ብለዋል፡፡

ግብረ ኃይሉ ባደረገው ጥረት በከተማው በ3 ቀበሌያት ብቻ ከ518 በላይ ህገወጥ ቤቶች መፍረሳቸውን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

በትናንትናው ዕለት በከተማው ውስጥ ሁምቦ ላሬና ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ አንድ ግለሰብ በህገወጥ መንገድ የገነባውን የራሱን ቆርቆሮ ቤት በራሱ ፈቃድ ለማፍረስ ከወጣበት በድንገት ወድቆ በሆስፒታል ሲታከም ቆይቶ ህይወቱ አልፏል ብለዋል፡፡

ይህንን ተከትሎ አንዳንድ ግለሰቦች ፖሊስ በጥይት ተኩሶ ገድሏል በማለት የተሳሳተ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያ በማሰራጨታቸው በከተማው አዲሱ መናኻሪያ አከባቢ አሮጌ ጎማ በማቃጠል ሁከት እንዲፈጠር ሙከራ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡

የተፈጠረው ሁከት በፀጥታ አካላትና በህብረተሰቡ ትብብር ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ሳያመራ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሉን ኢንስፐክተር ጥበቡ ገልጸዋል፡፡

በተለይም በሶዶ ከተማ የህግ የበላይነትን የማስከበርና የህዝቡን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ሥራ በህገ ወጥ መንገድ የተሰማሩ ጥቂት ግለሰቦች በሚፈጥሩት ሁከት ሊቆም እንደማይችል የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ እና የከተማው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ በጋራ በሰጡት መግለጫ አረጋግጠዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ገበታ ለሸገር...

በሚከተለው የባንክ አካውንት የ”ገበታ ለሸገር” ተሳትፎዎን ያረጋግጡ።

👉 1000275826317

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia