#update የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 ለመተካት በረቂቅነት በተዘጋጀው "የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና መቆጣጠር " አዋጅ ላይ በኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል ውይይት በመደረግ ላይ ነው። በሥራ ላይ ያለው አዋጅ በዋናነት ትኩረት ያደረገው መንግሥትን ብቻ መከላከል ላይ ያተኮረ በመሆኑ፣ ስያሜውም መሻሻሉን ረቂቁ ያስረዳል። በሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ ትኩረት ያደረገው ረቂቁ በተጠርጣሪ ላይ ያለአግባብ ምርመራና ዳኝነት በሚሰጡ ላይ #ተጠያቂነትን ይጥላል። በተከፈተው የምርመራ መዝገብ ለተጠርጣሪው ከ1,000 ብር እስከ 50,000 ብር #የሞራል_ካሳ ክፍያ ውሳኔ እንደሚሰጥም ይደነግጋል።
Via ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia