TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሆሳዕና‼️

በሆሳዕና ከተማ በአንድ ግለሰብ ሱቅ ውስጥ 10 ቱርክ ሰራሽ #ሽጉጦች ከ358 #ጥይቶች ጋር ተደብቀው መገኘታቸውን የሃዲያ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

የመምሪያው አዛዥ ኮማንደር #ደሳለኝ_ሽጉጤ ለኢዜአ እንደገለፁት ፖሊስ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያውን ሊይዝ የቻለው ከህብረተሰቡ በተደረገ ጥቆማ አማካኝነት ነው።

በከተማው ሴች ዱና ቀበሌ ከተያዘው የጦር መሳሪያ ጋር ባለ ሱቁን ጨምሮ እጃቸው አለበት በሚል የተጠረጠሩ አራት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋላቸውንም ኮማንደሩ ተናግረዋል፡፡

ህብረተሰቡ ላከናወነው ተግባር ያመሰገኑት ኮማንደር ደሳለኝ ሰላምን የሚያደፈርስና የሚያጠራጥር መሰል ድርጊት ሲያጋጥም ለፖሊስ መጠቆሙን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia 
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ🔝

‹‹ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ቀለምን እንጅ #ዘርን መቁጠር የለባቸውም፡፡›› የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር #ደሳለኝ_መንገሻ
.
.
.
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ‹‹ኪነ- ጥበብ ለሰላም›› በሚል ሃሳብ ለተማሪዎች መድረክ አዘጋጅቷል። ዩኒቨርሲቲው መድረኩን ያዘጋጀው በግብርናና ገጠር ትራንስፎርሜሽን የትምህርት መርሃ ግብር በሚሰጥበት ጠዳ ካምፓስ ለሚገኙ ተማሪዎች ነው።

የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችም በተለያዩ ማህበራዊ የትስስር መረቦች የሚሰራጬ መረጃዎችን እውነታነት በማመዛዘን ያስተማራቸውን ማህበረሰብ የመጥቀም ሃገራዊ ሃላፊነታቸውን መወጣት እንደሚገባቸው ተገልጿል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ደሳለኝ መንገሻ እንዳሉት ተማሪዎች ለግጭት የሚዳርጉ አስተሳሰቦችንና ተግባራትን በመታገል በልዩነት አብሮ የመኖር እሴትን ማጎልበት አለባቸው። ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ቀለም ለመቁጠር እንጅ ዘር ለመቁጠር መሆን እንደሌለበትም ነው ያስገነዘቡት።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲም ኪነ ጥበብ ለሰላም ያለውን ዋጋ በመገንዘብ መድረኮችን በመፍጠር ተማሪዎች ለሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ አቅም የመፍጠር ተግባራችንን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ያነጋገራቸው ተማሪዎች በበኩላቸው ቤተሰብና ሃገርን የመጥቀም ህልማቸው እንዲሳካ ተማሪዎች #በተሳሳተ_መረጃ ሳይረበሹ በመተሳሰብ ስሜት እውቀት መቅሰም እንዳለባቸው ነው የተናገሩት። ለዚህ እውን መሆን ደግሞ የበኩላቸውን አስተዋፆ እያደረጉ መሆኑን ነው የተናገሩት።

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ባዘጋጀው የኪነ ጥበብ መድረክ ሃገራዊ አንድነትን የሚያጎሉ የጥበብ ስራዎች ቀርበዋል።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዱራሜ‼️

በደቡብ ክልል በዜጎች ላይ እየደረሰ የሚገኘው ሞትና መፈናቃል ያሳቆጣቸው #የዱራሜ_ከተማ ነዋሪዎች አደባባይ መዉጣታቸዉ ተነገረ።

በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ዛሬ በከተማው ስታዲየም በመሰባሰብ መንግሥት የዜጎችን በህይወት የመኖር ህገ መንግሥታዊ መብት ሊያስከብር ይገባል ሲሉ ድምፃቸውን አሰምተዋል።

ሠልፈኞቹ በቅርቡ ከከፋ ዞን ዴቻ ወረዳ በታጣቂዎች ጥቃት የሞት አደጋ የደረሰባቸው ነዋሪዎችን ለማሰብ የሻማ ማብራት ሥነ-ሥርዓት ያካሄዱ ሲሆን ከአካባቢው ለተፈናቀሉ ቤተሰቦችም የገንዘብ ፤ የቁሳቁስና የአልባሳት ድጋፍ አድርገዋል።

የሰልፉ አስተባባሪ አቶ #ደሳለኝ_ዳለሎ በሰልፉ ላይ የከተማው ነዋሪዎች በዋናነት ሁለት መሠረታዊ መልዕክቶችን ያስተላለፉበት ነው ሲሉ ለጀርመን ራድዮ ተናግረዋል።

በደቡብ ክልል #ከፋ_ዞን ዴቻ ወረዳ ታጣቂዎች በሰፈራ መንደር በተሰባሰቡ የከምባታ ማህበረሰብ አባላት ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን በማድረስ ላይ እንደሚገኙ የከንባታ ጠንባሮ ዞን መስተዳድር ማስታወቁ አይዘነጋም። እስከአሁን በጥቃቱ 32 ሰዎች ሲሞቱ ከ 35 ሺህ በላይ የሚሆኑት መፈናቀላቸው ይታወቃል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አብን🔝

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) በቅርቡ በሚካሄደው የህዝብና የቤት ቆጠራ ላይ ስጋት እንዳለው ገለጸ። የፊታችን መጋቢት በሚካሄደው አገር አቀፍ የህዝብና ቤት ቆጠራ ላይ ከፖለቲካዊ ተጽዕኖ ነጻ መሆን መቻል አለበት ሲል አብን የገለጸው መጪውን የህዝብና ቤት ቆጠራ አስመልክቶ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ባደረገው ውይይት ላይ ነው።

የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር #ደሳለኝ እንዳሉት በመጪው መጋቢት 29/2011 የሚካሄደው 4ኛው ዙር አገር አቀፍ የህዝብና የቤት ቆጠራ በትክክል እንዲካሄድ ህዝቡ #በንቃት መሳተፍና #ውጤቱንም መከታተል እንዳለበት ገልጸዋል።

ዶክተር #ሲሳይ_ምስጋናው በጎንደር ዩኒቨርሰቲ የስነ ህዝብ መምህር እንዳሉት ከዚህ በፊት የተደረጉ ቆጠራዎች በርካታ ችግሮች እንደተስተዋሉባቸው በውይይቱ ላይ ባቀረቡት ጥናታዊ ፅሁፍ ጠቁመዋል።

ከዚህ በፊት በተካሄዱ የህዝብና የቤት ቆጠራ የተስተዋሉ ህጸጾች በቀጣዩ ቆጠራ ወቅት እንዳይደገሙ ምሁራን ህዝቡን ማንቃት እዳለባቸው እንዲሁም የአማራ ህዝብም ሁኔታዎችን በንቃት መከታተል እንዳለበት ሊቀመንበሩ አሳስበዋል።

የህግ ባለሙያ የሆኑት አቶ #ውብሸት_ሙላት የህዝብና የቤት ቆጠራ ከህግ ማዕቀፍ በሚል ርዕስ የሌሎችን አገሮች ተሞክሮ በማጣቀስ በአገራችን የሚደረግ ቆጠራ በገለልተኛ አካል መካሄድ እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምዕራብ ጎንደር‼️

በምዕራብ ጎንደር ዞን #መቃ በተባለች አነስተኛ ከተማ በትንሹ 17 ሰዎች በትናንትናው ዕለት በአካባቢው ነዋሪዎች #መታገታቸውን የዐይን እማኝ ተናገሩ። ከጎንደር ወደ ገንደውሐ በመጓዝ ላይ የነበሩ መንገደኞችን ያገቱት የመቃ ከተማ ነዋሪዎች ናቸው ተብሏል። ታጋቾቹ ሌንጫ በተባለ ቀበሌ ጉባይ ጀጀቢት ወደተባለ ቦታ ተወስደዋል። ከታጋቾቹ መካከል ሁለት ልጆች የያዙ አንዲት እናት እንደሚገኙበት በቦታው የነበሩ የዐይን እማኝ ተናግረዋል። መቃ ከተማ በታገተው ተሽከርካሪ በመጓዝ ላይ እንደነበሩ የሚናገሩት መምህር ጋሻው ጌቴ «ትናንት ከጎንደር ተነስተን ወደ ገንደውሐ ከተማ ስንሔድ መቃ አካባቢ መኪናውን አግተው ከ17 ያላነሰ ሰው ነው ጉባይ ጀጀቢት ወደሚባል ቦታ ይዘውት የሔዱት» ብለዋል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር እና ጸጥታ ኃላፊ አቶ #ደሳለኝ_ጣሰው እገታው መፈጸሙን ቢያረጋግጡም ስብሰባ ላይ በመሆናቸው ተጨማሪ ማብራሪያ ሳይሰጡ ቀርተዋል።

በተለምዶ አባዱላ ተብሎ የሚጠራው የሕዝብ መጓጓዣ መቃ በተባለችው ከተማ ነዋሪዎች ሲታገት 20 ገደማ ሰዎች ጭኖ እንደነበር መምህር ጋሻው አስረድተዋል። ተሽከርካሪው መቃ ከተማ ላይ ሲደርስ መምህር #ጋሻው_ጌቴን ጨምሮ ሦስት ሰዎች ወርደው ወደ ሕዝብ በመቀላቀል ማምለጣቸውን የዐይን እማኙ አስረድተዋል። ኩነቱ በአካባቢው በተፈጠረው ቀውስ ሳቢያ የተከሰተ መሆኑን የተናገሩት መምህር ጋሻው እገታውን የፈጸመው «መቃ የሚባል ቀበሌ ሕዝቡ ነው» ብለዋል። የዐይን እማኙ እገታው በተፈጸመበት ወቅት «በጣም ብዙ ሰው ተደብድቧል። በጣም ብዙ ሰው ተመቷል» ሲሉ አስረድተዋል። «ሰዎቹ ይሙቱ ይዳኑ የሚታወቅ ነገር የለም። መኪናው ግን በመከላከያ ተይዟል የሚል መረጃ አግኝቻለሁ» ሲሉም አክለዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሰሜን ወሎ ወጣቶች በበጎ ተግባር!

"ከሰሜን ወሎ #መርሳ ከተማ ነው፤ በክረምት በጎ አድራጎት እኛ ደስ በሚል ሁኔታ እየሰራን ነው። በከተማችን ያሉ አረጋዋያንን ቤት በመጠገን፣ አልባሳታቸውን እና ንፅህናቸውን በመጠበቅ እንዲሁም ገንዘብ በማሰባሰብ ድጋፍ እያደረግን ሲሆን አሁን ደግሞ የትምህርት ቁሳቁሶችን እየሸከፍን እንገኛለን" #ደሳለኝ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጊዳሚ ከተማ ሁለት ሰዎች በጥይት ተመትተው ተገደሉ !

ከትናንት በስቲያ (ቅዳሜ) ከምሽቱ 1 ሰዓት ገደማ በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ከተማ ሁለት ሰዎች በጥይት ተመትተው መገደላቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በምዕራብ ኦሮሚያ ይህን መሰሉ ግድያ ነዋሪ የዕለት ተዕለት ሰቆቃ ከሆነ ሰነባብቷል።

"ቅዳሜ ምሽት ተኩስ ነበር። በዚያ ተኩስ ሳቢያ ነው ሁለቱ ነዋሪዎች የተገደሉት። እነሱን የገደለው አካል የቱ እንደሆነ ደግሞ መለየት አልቻልንም" በማለት ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸውን የማንጠቅስ አንድ የአካባቢው ነዋሪ ተናግረዋል።

ከተገደሉት ሁለቱ ግለሰቦች አንዱ የጊዳሚ ከተማ ቀበሌ 01 ነዋሪ የነበሩት አቶ ነጋሽ ፉፋ ሲሆኑ ሌላኛው ሟች ደግሞ፤ "ከቄለም ገጠራማ ስፍራ የመጡ ናቸው፤ ማንነታቸውን አለየንም" በማለት የከተማዋ ነዋሪ ተናግረዋል።

የጊዳሚ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ #ደሳለኝ_ቱጁባ በበኩላቸው ሟቾቹ አቶ ነጋሽ ፉፋ እና አቶ ያዕቆብ ቶላ እንደሚባሉ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

"አቶ ነጋሽ ፉፋ ቤት አቅራቢያ በቅኝት ሥራ ላይ በነበሩ የልዩ ፖሊስ እና የሃገር መከላከያ አባላት ላይ ቦንብ ተወረወረ፤ #ተኩስም ተከፈተ" የሚሉት የወረዳው አስተዳዳሪ፤ ቦንምቡን የወረወረው እና ተኩስ የከፈተው አካል አሁን ድረስ እንደማይታወቅ ጠቅሰው፤ ድንገተኛ ጥቃቱ የተሰነዘረው ግን በመንግሥት ኃይሎች ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

#ቢቢሲ

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-16-5