TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሰሜን ወሎ ወጣቶች በበጎ ተግባር!

"ከሰሜን ወሎ #መርሳ ከተማ ነው፤ በክረምት በጎ አድራጎት እኛ ደስ በሚል ሁኔታ እየሰራን ነው። በከተማችን ያሉ አረጋዋያንን ቤት በመጠገን፣ አልባሳታቸውን እና ንፅህናቸውን በመጠበቅ እንዲሁም ገንዘብ በማሰባሰብ ድጋፍ እያደረግን ሲሆን አሁን ደግሞ የትምህርት ቁሳቁሶችን እየሸከፍን እንገኛለን" #ደሳለኝ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update

የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት #መርሳ እና #ግራናን በመቆጣጠር ወደፊት እየገሠገሠ መሆኑን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አሳውቋቃ።

የአትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት በቆቦ ግንባር ቀደም ብሎ የዞብል ከፍተኛ ቦታዎችን ተቆጣጥሮ የነበረ ሲሆን፣ በራያ ሰሜናዊ አቅጣጫ ያሉትን ከፍተኛ ቦታዎችን ጨምሮ ተቆጣጥሯል፡፡

በዞብል ደቡብ አቅጣጫ ደግሞ የጉራ ወርቄ አካባቢዎችን ተቆጣጥሮ የነበረው የወገን ጦር አሁን ደግሞ የጉራ ወርቄ ከፍተኛ ሰንሰለታማ ቦታዎችን ሙሉ በሙሉ በማጽዳት፣ ቀደም ብሎ የተቆረጠውን የወልድያ መቀሌ መሥመር አሰፋፍቶ፣ ወደ ወልድያ በቅርብ ርቀት እየገሠገሠ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ባለፈው ውጫሌ ከተማን ነጸ ያወጣው የወገን ጦር፣ በዚሁ ግንባር የውጫሌ ወረዳን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር የውርጌሳ፣ የሊብሶ፣የግራና፣ የመርሳ፣ የኪሌ፣ከተሞችንና በሰሜን ወሎ የሐርቡ ወረዳን ከፍተኛ ሰንሰለታማ ተራሮችን በእጁ አስገብቷል።

በእነዚህ የማጥቃት እንቅስቃሴዎች ጀግኖቹ የወገን ጥምር ጦር በንሥሮቹ አየር ኃይላችን በመታገዝ ጠላትን ከመርሳ በስተጀርባ ቆርጦ በመግባት፣ በውጫሌና ውርጌሳ መካከል የነበረውን ጠላት ሙለሉ በሙሉ ደምስሰውታል፤ ምርኮኛና ቁስለኛም አድርገውታል ብሏል የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን ፥ የአካባቢ ኅብረተሰብ ከወገን ጥምር ጦር ጋር በመቀናጀት፣ እግሬ አውጪኝ ብሎ የሚሸሸውን ጠላት ከየጢሻው እየመነጠረ በመደምሰስ አኩሪ ጀብድ ፈጽሟል ብሏል።

አክሎም " ጠላት የዘረፈውን ንብረትና ተተኳሾቹን ፈጽሞ ይዞ እንዳይወጣ አድርጎታል፡፡ የወገን ጥምር ጦር በወልድያና ሐራ ከተሞች መካከል የሚገኘውንና መውጫ ያጣውን ጠላት ለመደምሰስ፣ በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ ወደ ፊት እየገሠገሠ ነው " ሲል አሳውቋል።

@tikvahethiopia