TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አብዲ ኢሌ ላይ ክስ ተመሰረተ‼️

በሶማሌ ክልል የቀድሞው ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ #መሃመድ_ዑመርን ጨምሮ በ47 ግለሰቦች ላይ #ክስ ተመሰረተ።

ተከሳሾቹ አቶ አብዲ ሙሃመድ፣ ራህማ መሀመድ ሀይቤ፣ አብዱራዛቅ ሰሀኔ ኢልሚ፣ አቶ ፈርሃን ጣሂር በርከሌ፣ ጉሌድ ኦበል ዳውድ እና ወርሰሜ ሼህ አብዲ ሸሂድን ጨምሮ 47 ግለሰቦች ናቸው። ተከሳሾች በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የወንጀል ችሎት ነው ክስ የተመሰረተባቸው። ግለሰቦቹ ለጊዜው ካልተያዙ ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን በቀጥታ ወይም በአድራጎታቸው በወንጀሉ ተካፋይ በመሆን በህብረትና በማደም፥ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ቀኑ ባልታወቀ ሰኔ ወር 2010 ዓ.ም እስከ ሀምሌ 30 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናቶች በክልሉ ውስጥ አንዱ ወገን በሌላው ወገን ላይ የጦር መሳሪያ እንዲያነሳ ለማድረግ በማሰብ መንቀሳቀሳቸው
ተጠቅሷል።

በዚህም በአንዳንድ የሶማሌ ብሔር ተወላጆች እና በሶማሌ ክልል በሚኖሩ የሌሎች ብሄር ተወላጆች መካከል አለመግባባት እንዲፈጠር በማሰብ በግጭቱ ውስጥ የሚሳተፉና ሄጎ በሚል ወጣቶችን ማደራጀታቸውም በክሱ ተነስቷል። የተደራጀውን የሄጎ ቡድን በገንዘብ እና በተለያዩ ቁሳቁሶች በመደገፍ፣ መሳሪያ በማስታጠቅ፣ ግጭቱ የሚመራበትና መልዕክት የሚተላለፍበት ሄጎ ዋሄገን የሚል የፌስቡክ ገጽ በመክፈትና በተለያዩ ስብሰባዎች ላይ ሰዎችን ሊያነሳሱ የሚችሉ መልእክቶችን አስተላልፈዋልም ነው ያለው የአቃቢ ህግ ክስ።

በኦሮሞ ወታደሮች ተወረናል፣ የኦሮሞ ተወላጆች መሬታችንን ለቀው መውጣት አለባቸው፣ ነዳጃችንን፣ መሬታችንን እና ወርቃችንን በጉልበት ሊወስዱብን ነው፣ የፌደራል መንግስት በህገወጥ መንገድ ሊወረን እና አዲስ መንግስት ለማቋቋም እንቅስቃሴ እያደረገ ነው፣ ሁላችንም አንድ በመሆን በክልላችን ውስጥ ከሶማሌ ብሄር ውጭ ያሉ ብሔረሰቦችን መግደል፣ ንብረታቸውንም መዝረፍ እና ማውደም፣ ባንኮችን እና ኢንሹራንሶችን መዝረፍ፣ ቤተክርስቲያኖችን እና ነዳጅ ማደያዎችን ማቃጠል አለብን የሚል ይዘት ያላቸውና ሌሎች መልዕክቶችም ተላልፈዋል ነው ያለው አቃቢ ህግ።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ይህንን ማድረግ የሚያስችል የራሳችን ወታደሮች እና የተደራጁ የሔጎ አባላት አሉን በሚል እንዲሁም በስብሰባና በፌስ ቡክ ቅስቀሳ በማድረግ እንዲሁም የክልሉ አድማ ብተና ሃይልም ሄጎዎች የሚሰሩትን ማንኛውንም ነገር እንዳይከላከል ከካምፕ እንዳይወጣ ትእዛዝ ሰጥተዋልም ተብሏል።

እንዲሁም በክልሉ ውስጥ ግጭት እንዲነሳ በማድረግና በግጭቱ ምክንያት የሰው ህይወት እንዲጠፋ፣ በመንግስት እና በእምነት ተቋማት እንዲሁም በግለሰብ ንብረት ላይ ጉዳት እንዲደርስ፣ ሴቶች እንዲደፈሩና እና በርካታ የከተማው ነዋሪ እንዲፈናቀል ማድረጋቸውም በክሱ ተካቷል። በአጠቃላይ ከ1ኛ እስከ 26ኛ ተራ ቁጥር የተመለከቱት ተከሳሾች ከላይ በተገለጸው አግባብ በመቀስቀስና በማነሳሳት በዚህ የማነሳሳት ተግባራቸው በሶማሌ ብሔር ተወላጆች እና በክልሉ የሚኖሩ ሌሎች ብሔሮች መካከል አለመግባባት እና ግጭት እንዲፈጠር አድርገዋልም ነው የተባለው።

በዚህ ግጭትም በሰነድ ማስረጃው ላይ በተገለፀው አግባብ ከ59 ሰዎች በላይ ህይወት እንዲጠፋ፣ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑ ካህናት እና የእምነቱ ተከታይ የሆኑ ግለሰቦች በአሰቃቂ ሁኔታ ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ በመግደልና በእሳት እንዲቃጠሉ ማድረጋቸው በክሱ ተነስቷል። ከ266 በላይ ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት እንዲደርስ፣ በምስክርነት የተጠቀሱ ሴቶችን በሄጎ ቡድን እና በክልሉ ልዩ ሀይል ፖሊስ አባላት እንዲደፈሩ በማድረግ እንዲሁም ግምቱ 412 ሚሊየን 468 ሺህ 826 ብር በላይ የሚሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፣ የመንግስት፣ በግለሰብ መኖሪያ ቤትና የንግድ ድርጅት ንብረቶች እንዲቃጠሉ፣ እንዲዘረፉ እና ብዛታቸው በውል ያልታወቁ ከሶማሌ ብሔር ተወላጅ ውጭ የሆኑ የከተማው ነዋሪዎች ከቤትና ንብረታቸው እንዲፈናቀሉ አድርገዋልም ነው የሚለው ክሱ።

በዚህም ተከሳሾች በፈፀሙት የጦር መሳሪያ ይዞ በማመጽ ወይም የእርስ በእርስ ጦርነት በማስነሳት በመንግስት ላይ የሚደረግ ወንጀል ክስ ቀርቦባቸዋል። በዛሬው እለት ተከሳሾች ከጠበቆቻቸው ጋር የቀረቡ ባለመሆናቸው ክሳቸውን በንባብ ለመስማት ፍርድ ቤቱ ለጥር 29 ቀን 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። በተያያዘም አቶ ቴዎድሮስ አዲሱ (ቴዲ ማንጁስ) በ80 ሺህ ብር ዋስ እንዲወጣ ተፈቅዶለታል። ቴዲ ማንጁስ በሶማሌ ክልል በተፈጠረው ግጭት የሰው ህይወት መጥፋትና መፈናቀል ወንጀል ላይ ተሳትፏል በሚል መጠርጠሩ ይታወሳል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ለከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉትን ‹‹ቪ8›› መኪኖች በሌሎች አዳዲስና ወጪ ቆጣቢ ተሽከርካሪዎች የመተካቱ ሂደት በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ ተገለፀ። ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የአዳዲሶቹ ተሽከርካሪዎች ግዢ የተፈፀመ ሲሆን፤ ከየካቲት 1 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ተተኪዎቹ ወደ ስራ ይገባሉ።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድሬዳዋ ፖሊስ‼️

በድሬዳዋ ከተማ ተፈጥሮ በነበረው #አለመረጋጋት እና የተቃውሞ ቀናት ጉዳት ሳይደርስበት በሀሰት ጉዳት የደረሰበት በማስመሰልና ይህንን የሃሰት ፎቶ በማህበራዊ ድረ ገፅ በመልቀቅ ግጭቶች እንዲፈጠሩ ለማድረግ የሞከረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

በፎቶው ላይ ምስሉ የሚታየው ተጠርጣሪ #ወርሰሜ_ሀሸ_መሀመድ የተባለው ግለሰብ በፀጥታ ሀይሎች ጉዳት የደረሰበት በማስመሰል ነው በፌስቡክ ገፁ ላይ ይፋ ያደረገው ፡፡ እንደ ፖሊስ ገለፃ ግለሰቡ ምንም አይነት አካላዊ ጉዳት ያልደረሰበት መሆኑን ገልጾ ከእንዲህ አይነት ተግባሮች መጠበቅ እንደሚገባ ያሳሰበ ሲሆን ግለሰቡ በበኩሉ ለፖሊስ በሰጠው ቃል ይቅርታ ጠይቋል ሲል የድሬዳዋ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ዘግቧል።

ምንጭ፦ waltainfo.com
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሶማሌ ክልል ግጭት፣ ግድያና ቃጠሎ ጋር በተያያዘ ከአራት ወራት በላይ በእስር ላይ የነበረው #ቴዎድሮስ_አዲሱ (ቴዲ ማንጁስ) በ80,000 ብር ዋስ ከእስር እንዲፈታ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ሰጠ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን "ግዴታዬን እወጣለሁ ፣ መብቴንም እጠይቃለሁ!" በሚል መርህ ቃል የከተማ አቀፍ የታክስ ንቃናቄ መድረክ እያካሄደ ይገኛል፡፡ መድረኩ በዋነኛነት የታክስ ንቅናቄው ትግበራ የሚበሰርበት እና የባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ግዴታ ለመወጣት ቃል የሚገቡበት ይሆናል። በመድረኩ ላይ ኢ/ር #ታከለ_ኡማ፣ የፌደራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ የንግዱ ማህበረሰብ አካላት፣ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች ተሳታፊ እንደሆኑበት ከክንቲባ ጽህፈት ቤት የተኘው መረጃ ያሳያል።

ምንጭ፦ የከንቲባ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከኮንሶ ዞን ወደ ሶያማ ቡርጂ ወረዳ ሲጓዝ በነበረ የጭነት መኪና ላይ ባልታወቁ #ታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ በትላንትናው ዕለት የአራት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ በጥቃቱ ሳቢያ አደጋው የተከሰተበትን ሁኔታ ለማወቅ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን የደቡብ ክልል ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ፍቅሬ አማም በተለይ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡ በጥቃቱ እስካሁን የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉንም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡ የጥቃቱ ፈፃሚዎች ማንነት አለመታወቁንም አቶ ፍቅሬ ገልፀዋል፡፡

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተማሪዎች 2ሺህ 380 ዩኒት ደም ለገሱ‼️

#በምሥራቅ_ወለጋ_ዞን በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ በጎ ፈቃደኛ ተማሪዎች 2ሺህ 380 ዩኒት ደም መለገሳቸውን የነቀምቴ ደም ባንክ አገልግሎት አስታወቀ።

ባለፉት ስድስት ወራት ደሙን የለገሱት በስምንት ወረዳዎችና በነቀምቴ ከተማ  የሚገኙ የመሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎች መሆናቸው ተገልጿል።

የደም ባንክ አገልገሎቱ ኃላፊ አቶ #ዴሬሣ_ባየታ እንደገለፁት ከበጎድቃደኛ ተማሪዎች የተሰበሰበው ደም በምስራቅ፣ ሆሮጉድሩና ቄለም ወለጋ ዞኖች ለሚገኙ ሆስፒታሎች ተከፋፍሏል።

በግማሽ በጀት ዓመቱ ከትምህርት ቤቶች 4ሺህ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ ቢታቀድም በአካባቢው በነበረው አለመረጋጋት ዕቅዱን ሙሉ ለሙሉ ለማከናወን አለመቻሉን ተናግረዋል።

የነቀምቴ መሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪ ሊሊ ተመስጌን በሰጠችው አስተያየት በደም እጥረት ሕይወታቸው የሚያላፍ ወላድ እናቶችን ለመታደግ ባላት ፍላጎት በሁለት ዙር ደም ለግሳለች።

ተማሪ ኢዮብ አሰፋ በበኩሉ ደም መለገስ ከሰብአዊ ድጋፎች ትልቁ መሆኑን በመግለፅ ወደ ፊትም የደም ባንኩ ቋሚ አባል በመሆን ልገሳውን አጠናክሮ የማስቀጠል ዓላማ እንዳለው ተናግሯል ።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድሬዳዋ‼️

የመልካም አስተዳደርና የሥራ  አጥነት መሠረታዊ ጥያቄዎች በፍጥነት ለመመለስ የሚያግዝ የ60 ቀናት ዕቅድ ተዘጋጅቶ እንቅስቃሴ መጀመሩን የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ተናገሩ።

የድሬዳዋ አስተዳደርና የሐረሪ ክልል ፖሊስ ገለልተኛ ሆኖ አገር አቀፍ ለውጡን በሚያግዝ መንገድ ማዋቀር /ሪፎርም/ እንደሚያስፈልግ የፀጥታ ጊዜያዊ ኮሚቴ ሰብሳቢ ብርጋዲዬር ጄኔራል #ተስፋዬ_ወልደማርያም አስታውቀዋል፡፡

ዕቅዱ ሕዝብ #ብሶቱን የሚያሰማባቸውን 17 መሠረታዊ ጉዳዮች በመለየት  ሁሉን አቀፍ ምላሽ ለመስጠት መዘጋጀቱን ከንቲባው አቶ #ኢብራሂም_ዑስማን አስታውቀዋል፡፡

አመራሩ ከፖለቲካ ፣ከሰላምና ፀጥታ እንዲሁም ከልማትና ከመልካም አስተዳደር አኳያ የተጀመረውን እንቅስቃሴ ዳር ለማድረስ  መሥራት እንደሚገባውም አሳስበዋል፡፡

”በዕቅዱ መሰረት የተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ጭምር በማጠናቀቅ የሕዝቡን  የዓመታት ጥያቄ ምላሽ የሚያገኝበት ይሆናል። በየሥፍራው የተገነቡ የመሸጫና የማምረቻ ቦታዎች ለወጣቱ ይሰጣሉ” ብለዋል፡፡

ከሚመለከተው የበላይ አካል ጋር በመነጋገር ፖሊስ በአስቸኳይ ወደ ሪፎርም እንደሚገባም አስታውቀዋል፡፡

ኅብረተሰቡ ዕቅዱ ስኬታማ ለማድረግ ድጋፍና ትብብር ከማድረግ ጎን ለሰላምና #ለፀጥታ መረጋገጥ ግንባር ቀደም ኃላፊነቱን እንዲወጣ ከንቲባው ጠይቀዋል፡፡

የድሬዳዋ ጊዜያዊ የፀጥታ ኮሚቴ ሰብሳቢ የምሥራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን ብርጋዲዬር ጄኔራል ተስፋዬ ወልደማርያም በከተማዋ ሰሞኑን የተፈጠረው ሕገ-ወጥ ተግባራትና ሁከት መንስዔ አመራሩ የተሰጠውን ኃላፊነት ባለመወጣቱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አሁንም አመራሩ ባለበት ተጠያቂነትና ይቅርታ በመጠየቅ ዕቅዱን በማከናወን ሕዝቡን መካስ እንዳለበት አሳስበዋል። ”ሕዝቡን የማያገለግል አመራር መነሳት አለበት፤ በብጥብጥና ሁከት ውስጥ የተገኘ አመራር የማያስፈልግና በሕግ መጠየቅ ያለበት ይሆናል” ብለዋል፡፡

ኅብረተሰቡ ለውጥ በሂደት የሚመጣ  መሆኑን በመገንዘብ አገራዊ ለውጡን ለማደናቀፍና በሚፈለገው መንገድ አንዳይጓዝ የሚፈልጉ አካላትን በተቀናጀ መንገድ መከላከል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

ብርጋዲዬር ጄኔራል ተስፋዬ እንደተናገሩት በድሬዳዋም ሆነ በምሥራቁ የአገሪቱ ክፍል #አስተማማኝ ሰላምና ፀጥታ የሚያሰፍን ዕቅድ ተዘጋጅቶ  በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡

ሰሞኑን በድሬዳዋ በተፈጠረው ሁከትና ነውጥ በማራገብ ሂደት #ፖሊስና #አድማ_በታኝ አሉበት፤ ይህም በፖሊስ ውስጥ መሠረታዊ ሪፎርም እንደሚያስፈልግ ያመለክታል ብለዋል።

በመሆኑም የድሬዳዋ አስተዳደርም ሆነ የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች ውስጥ ሥር ነቀል ለውጥ ማድረግና የኅብረተሰቡን ሰላምና ፀጥታ በአስተማማኝ መንገድ መጠበቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ምንጭ፦ ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ድሬዳዋ

ሰሞኑን በድሬዳዋ በተፈጠረው ሁከትና ነውጥ #በማራገብ ሂደት #ፖሊስ እና #አድማ_በታኝ አሉበት፤ ይህም በፖሊስ ውስጥ መሠረታዊ ሪፎርም እንደሚያስፈልግ ያመለክታል ተብሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ማስጠንቀቂያ

በድሬዳዋ ከተማ የትራንስፖርትና የግብይት #አድማ ለማድረግ ያቀዱ ነዋሪዎች ከድርጊታቸው ይቆጠቡ ዘንድ የምስራቅ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ አስጠነቅቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትኩረት ለቴፒ‼️

ለፌደራሉ መንግስት
ለደቡብ ክልል መንግስት
ለሀገር መከላከያ
ለፌደራል ፖሊስ
.
.
የክልሉ መንግስት እንዲሁም የፌደራሉ መንግስት በቴፒ ያለውን ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጠው ለTIKVAH-ETH አሁን የተላኩ መልዕክቶች ያስረዳሉ። ሁኔታዎችን አሁን ካሉበት ወደሌላ ደረጃ ሳይሸጋገሩ መንግስት #መፍትሄ_ሊያበጅ እንደሚገባ ተጠቁሟል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update 15ኛው የኢትዮ-ጅቡቲ የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በዛሬው ዕለት በጂቡቲ ተጀምሯል፡፡
@tsegsbwolde @tikvahethiopia