TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ሂዩማን ራይትስ ዎች⬇️

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም ሂዩማን ራይትስ ዎች ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የአፈና ስልቶችን #እንዲያስቆሙ ጠየቀ። በኢትዮጵያ በቅርቡ የተካሄዱት የጅምላ እስሮች እና "አመለካከትን የመቀየር ስልጠናዎች" ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጀመሯቸውን ፖለቲካዊ #ማሻሻያዎች አደጋ ላይ የሚጥሉ ናቸው ብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሃድሶ ስልጠና የሚሰጥባቸውን ካምፖች #እንዲዘጉ እና የዘፈቀደ እስርንም በማስቆም ቁርጠኝነታቸውን እንዲያሳዩም አሳስቧል።

ምንጭ፦ DW የአማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መቐለ
 
ከመቐለ ከተማ ተሰርቃ ልትሰወር የነበረ አንድ ተሽከርካሪ በፀጥታ ኃይሎች ርብርብ ማትረፍ ተችሏል።

ዘረፋው አመሻሽ የተፈፀመ ሲሆን ከሌሊቱ 8:00 ሰዓት በፓሊስ እርምጃ መመከን ችሏል።

ስርቆቱ እንዴት ተፈፀመ ?

መኪናዋ RAVA-4 ስትሆን በ " 03532 ኮድ-2 ትግ " የሰሌዳ ቁጥር የምትታወቅና ባለቤትነትዋ የመቐለ ከተማ ነዋሪ የሆኑት የአቶ ሃይለ ገ/መስቀል የተባሉ ግለሰብ ናት።

እስካሁን በፓሊስ ቁጥጥር ስር #ያልዋሉት ተጠርጣሪዎች መኪናዋ ጥር 4 ቀን 2016 ዓ.ም ቴድሮስ ከተባለ የመኪናዋ ባለቤት ልጅ #አፍነው በመቀማት ይዘዋት መሰወራቸው የተረዱ ባለቤቶች ወድያውኑ ወደ ፓሊስ ስልክ ደወሉ።

ፓሊስ ጊዜ ሳያጠፋ ተጨማሪ የፀጥታ ሃይሎች በማሰማራት ከመቐለ ወደ ሌሎች አከባቢዎች የሚያወጡ መንገዶች #እንዲዘጉ አደረገ።

ይህንን የተቀናጀና የተናበበ የፓሊስ የፀጥታ እንቅስቃሴ የተረዱ የሚመሰሉት መንታፊዎች መኪናዋን በአስፋልት መንገድ ጥለው ሸሽተዋል።

ፓሊስም መኪናዋን ከጥር 4 ወደ ጥር 5 /2016 ዓ.ም አጥቢያ ከሌሊቱ 8:00  በቁጥጥር ስር አውሏታል።

የሚሊዮኖች ብር ዋጋ ያላት መኪና ስርቀው ጥለዋት የጠፉት ተጠርጣሪዎች አድኖ በቁጥጥር ስር ለማዋል በከፍተኛ ጥረት ላይ እንደሆነ የገለፀው የመቐለ ከተማ ፓሊስ ፤ ባለቤቶች ንብረቶቻቸው በጥንቃቄ እንዲይዙ መክሯል።

ተጠርጣሪዎች በህግ ስር ውለው ቅጣታቸው እንዲቀበሉ ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩ እንዲያደርግ መጠየቁ መቐለ ኤፍ ኤምን ዋቢ በማድርግ የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧን።

Photo Credit - FM መቐለ
                                     
@tikvahethiopia