TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" በታጣቂዎቹ የተወሰዱት ሕፃናት ይመለሳሉ የሚል ተስፋ የለንም " - አቶ ኡገቱ አዲንግ

#ከደቡብ_ሱዳን በመነሳት የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው ወደ ጋምቤላ ክልል የገቡ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች 2 ሕፃናት #አፍነው መውሰዳቸውን የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ፡፡

የክልሉ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡገቱ አዲንግ ለሪፖርተር ጋዜጣ የሰጡት ቃል ፦

-  ታጣቂዎቹ ከዚህ በፊትም በሕገወጥ መንገድ ድንበር ጥሰው በመግባት የሰው ሕይወት አጥፍተዋል፣ ሕፃናትን አፍነው ወስደዋል፣ ከብቶችን ዘርፈዋል፤ አሁንም ቢሆን ድርጊቱ አልቆመም።

- በተለይ በአኮቦ፣ ዋንቲዋና መኮይ ወረዳዎች ሕፃናትን አፍኖ ለመውሰድ፣ ንብረት ለመዝረፍና በሰዎች ላይ ጉዳት ለማድረስ የሙርሌ ታጣቂዎች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ተስፋፍቷል ፤ ታጣቂዎቹ ባለፈው ሳምንት 3 ሕፃናትን አፍነው የወሰዱት በ3ቱ ወረዳዎች በነበራቸው መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ ነው።

- በታጣቂዎቹ የተወሰዱት ሕፃናት ይመለሳሉ የሚል ተስፋ የለንም። የሰው ልጅ ካልሞተ ይገኛል ብሎ ማሰብ ቢቻልም፣ እስካሁን በተደረገው ሕፃናትን የማስመለስ ሙከራ አንፃር፣ አሁንም ቢሆን ሰሞኑን የተወሰዱት ሕፃናት ከደቡብ ሱዳን መንግሥት ጋር በሚደረግ ውይይት ይመለሳሉ የሚል ተስፋ የለም።

- እስካሁን ታፍነው የተወሰዱት ሕፃናትና የተዘረፉ ንብረቶች ለማስመለስ ከዚህ ቀደም የክልሉ መንግስት ከደቡብ ሱዳን መንግሥት ጋር በጉዳዩ ላይ ሰፊ ውይይት ቢያደርግም፣ ውይይቱ ውጤታማ ባለመሆኑ በተጨባጭ የተመለሰ ሕፃንም ሆነ ንብረት የለም።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Reporter-12-25-2

Credit : ሪፖርተር ጋዜጣ

@tikvahethiopia
#መቐለ
 
ከመቐለ ከተማ ተሰርቃ ልትሰወር የነበረ አንድ ተሽከርካሪ በፀጥታ ኃይሎች ርብርብ ማትረፍ ተችሏል።

ዘረፋው አመሻሽ የተፈፀመ ሲሆን ከሌሊቱ 8:00 ሰዓት በፓሊስ እርምጃ መመከን ችሏል።

ስርቆቱ እንዴት ተፈፀመ ?

መኪናዋ RAVA-4 ስትሆን በ " 03532 ኮድ-2 ትግ " የሰሌዳ ቁጥር የምትታወቅና ባለቤትነትዋ የመቐለ ከተማ ነዋሪ የሆኑት የአቶ ሃይለ ገ/መስቀል የተባሉ ግለሰብ ናት።

እስካሁን በፓሊስ ቁጥጥር ስር #ያልዋሉት ተጠርጣሪዎች መኪናዋ ጥር 4 ቀን 2016 ዓ.ም ቴድሮስ ከተባለ የመኪናዋ ባለቤት ልጅ #አፍነው በመቀማት ይዘዋት መሰወራቸው የተረዱ ባለቤቶች ወድያውኑ ወደ ፓሊስ ስልክ ደወሉ።

ፓሊስ ጊዜ ሳያጠፋ ተጨማሪ የፀጥታ ሃይሎች በማሰማራት ከመቐለ ወደ ሌሎች አከባቢዎች የሚያወጡ መንገዶች #እንዲዘጉ አደረገ።

ይህንን የተቀናጀና የተናበበ የፓሊስ የፀጥታ እንቅስቃሴ የተረዱ የሚመሰሉት መንታፊዎች መኪናዋን በአስፋልት መንገድ ጥለው ሸሽተዋል።

ፓሊስም መኪናዋን ከጥር 4 ወደ ጥር 5 /2016 ዓ.ም አጥቢያ ከሌሊቱ 8:00  በቁጥጥር ስር አውሏታል።

የሚሊዮኖች ብር ዋጋ ያላት መኪና ስርቀው ጥለዋት የጠፉት ተጠርጣሪዎች አድኖ በቁጥጥር ስር ለማዋል በከፍተኛ ጥረት ላይ እንደሆነ የገለፀው የመቐለ ከተማ ፓሊስ ፤ ባለቤቶች ንብረቶቻቸው በጥንቃቄ እንዲይዙ መክሯል።

ተጠርጣሪዎች በህግ ስር ውለው ቅጣታቸው እንዲቀበሉ ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩ እንዲያደርግ መጠየቁ መቐለ ኤፍ ኤምን ዋቢ በማድርግ የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧን።

Photo Credit - FM መቐለ
                                     
@tikvahethiopia