TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወንጀል ነክ መረጃ‼️

ከባድ የአካል ጉዳት ያደረሰዉ #ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ፡፡ ተከሳሽ #ሳሙኤል_ጎችል_ወልደመስቀል በ1996 ዓ.ም የወጣዉን የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 555/ለ ስር የተመለከተዉን ድንጋጌ ተላልፎ በፈፀመዉ ከባድ የአካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ተከሷል፡፡

ተከሳሽ በሌላ ሰዉ አካል ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ ሰኔ 2 ቀን 2010 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 12፤30 ሲሆን በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታዉ በግ ተራ ተብሎ ከሚጠራዉ አካባቢ የግል ተበዳይ አብርሀም ታፈረን በቦክስ በመምታት የላይኛዉ የፊት ለፊት አራት ጥርሶቹ እንዲወልቁ ያደረገ በመሆኑ በፈፀመዉ ከባድ የአካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ነዉ፡፡

ተከሳሽ ከላይ በክስ ዝርዝሩ አደረክ የተባልኩትን ድርጊት አልፈፀምኩም ሲል የእምነት ክህደት ቃሉን ቢሰጥም ዐቃቢ ህግ 4 የሰዉ ምስክሮችንና የሰነድ የማስረጃዎቹን አጠናቅሮ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡

መዝገቡን የተመለከተዉ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የየካ ምድብ የወንጀል ችሎትም ተከሳሽ ጥፋተኛ ነዉ ሲል ታህሳስ 08 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለዉ 3ተኛ ወንጀል ችሎት በቅጣት ዉሳኔው ተከሳሽን ያርማል ሌሎችንም ያስተምራል በማለት በ2 አመት ከ9 ወር እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን‼️

መጭው የጥምቀት በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር ተከብሮ እንዲውል ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር #ሰኢድ_አህመድ ለአብመድ እንደገለጹት የጥምቀት በዓል ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል፡፡

በዓሉ በአደባባይ የሚከበር በመሆኑ ከተለመደው ጊዜ የተለየ የተጠናከረ ጥበቃ ይዳረጋልም ብለዋል ረዳት ኮሚሽነሩ፡፡

በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከህብረተሰቡ ጋር ተቀላቅለው ወንጀል የሚፈጽሙ አካላትን ለመቆጣጠር የሰውር የወንጀል ክትትል አባላት አቅማቸው ከፍ እንዲል መደረጉንም ረዳት ኮሚሽነር ሰኢድ ተናግረዋል፡፡

በጥምቀት በዓል የውጭ ሀገራት ጐብኝዎች ቁጥር ይጨምራል፤ጐብኝዎች በሚጓጓዙበትና በሚያርፉበት አካባቢ ልዩ ጥበቃ እንደሚደረግም ገልጸዋል፡፡

ረዳት ኮሚሽነር ሰኢድ እንዳስታወቁት በዓሉ በሚከበርበት ወቅት ለተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይኖራሉ፡፡

በዚህ ወቅት አሸከርካሪዎች በተዘጋጀላቸው አማራጭ መንገዶች መጠቀም አለባቸው ነው፤ ፍጥነታቸውን ቀንሰው ማሽከርከር እንዳለባቸውም ጠቁመዋል፡፡

በዓሉን በማስመልከት በአንዳንድ አካባቢዎች የሚደረግ የጦር መሣሪያ ተኩስ በህግ ያስጠይቃል፡፡ስለሆነም ከእንደዚህ አይነት ድርጊት መቆጠብ ተገቢ መሆኑንም አሣስበዋል፡፡

ህብረተሰቡ በበዓሉ ወቅት ሊያጋጥም የሚችልን የወንጀል ድርጊት በስልክ ቁጥሮች 058 220 13 27 እንዲሁም 058 220 19 21 ደውሎ ፈጣን አገልግሎት ማግኘት እንደሚችልም ምክትል ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎንደር🔝

#የጥምቀት_በዓል ከመድረሱ በፊት የማዕከላዊ #ጎንደር ዞን የባሕል ሳምንት ያካሂዳል፡፡ የባሕል ሳምንቱም የአካባቢውን ትውፊታዊ ማንነት እና አጋጊያጥን ጨምሮ ለጎብኝዎች በጎዳና ላይ ትርኢት ያሳያል፡፡ የጎዳና ላይ ትርኢቱም የጥምቀት በዓል ከመከበሩ በፊት የሚካሄድ በመሆኑ የአካባቢውን ባሕል በአምባሳደሮቹ አማካኝነት ፍንትው አድርጎ በማሳየት ትልቅ ሚና እንደተወጣም ተነግሯል፡፡ ስምንተኛው የባህል ሳምንት ፌስቲባል በጎንደር ከጥር 7 እስከ 9/2011 ሲከበር ቆይቶ ከማዕከላዊ ጎንደር የተወጣጡ የባሕል አምባሳደሮች ዛሬ ትርኢታቸውን በጎዳና ላይ በማቅረብ አጠናቅቀዋል፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በታላቁ የህዳሴ ግድብ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ውይይት እያደረጉ ነው። የውይይቱ ዓለማ #የተቀዛቀዘውን ህዝባዊ ተሳትፎ ለመመለስ እንደሆነ ተገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የጀርመኑ ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ፡፡ በአዲስ አበባ የጀርመን ኢምባሲ ባሰራጨው መረጃ ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታንማየር ከጥር 19-22 ባሉት ለቀናት በሚያደርጉት ጉብኝት ከፕሬዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴና ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ይወያያሉ፡፡ ላሊበላ የጉብኝታቸው አንዷ አካል ናት፡፡

Via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሟቾች ቁጥር 21 ደረሰ‼️

በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ በሚገኝ ባለ አምስት ኮከቡ ዱሲት ዲ2 ሆቴልና የንግድ ማዕከል ባሳለፍነው ማክሰኞ #በታጠቁ_ኃይሎች በተፈጸመው ጥቃት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 21 ደርሷል።

ጥቃቱ ከተከፈተበት ቅንጡ ሆቴልና የገበያ ማዕከል በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ጉዳት ሳይደርስባቸው የወጡ ሲሆን 28 ሰዎች ቆስለዋል። የኬንያ ቀይ መስቀል ማህበር እንዳስታወቀው 19 ሰዎች እስካሁን የገቡበት አልታወቀም።

አልሸባብ እጄ አለበት ያለውን ጥቃት ለመቆጣጠር የፀጥታ ኃይሎች 19 ሰዓታት ወስዶባቸዋል።

የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ትናንት በበብሔራዊ ቴሌቪዥን ባደረጉት ንግግር ጥቃተን የፈፀሙት #አምስት ታጣቂዎችን #በመግደል የኦፕሬሽን ስራው #መጠናቀቁን ተናግረዋል።

ከጥቃቱ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የተጠረጠሩ ሁለት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።

ኬንያ አልሸባብን ለመዋጋት ወታደሮቿን ወደ ሶማሊያ ከላከችበትከፈረንጆቹ 2011 ጥቅምት ጀምሮ የሽብር ቡድኑ የጥቃት ዒላማ ሆናለች።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ሰበታ ዓይነ ስውራን ትምህርት ቤትን እየጎበኙ ነው፡፡ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ ከመምህራን ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ከሰበታ አይነስውራን ት/ቤት የተወከሉ መምህር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ት/ቤቱን እንዲጎበኙ ጠይቀዋቸው የነበረ ሲሆን ዶ/ር ዐቢይም ከቻሉ እርሳቸው ካልቻሉ ግን ቀዳማይ እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው እንደሚጎበኟቸው ቃል መግባታቸው ይታወሳል፡፡

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አትሌት ደራርቱ ቱሉ የአድዋን ድል ለመዘከር በባዶ እግሯ 500 ሜትር ልትሮጥ ነው። የአድዋ ድልን የሚዘክር የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በአዲስ አበባ የካቲት 24 ቀን 2011 ዓ.ም ሊካሄድ ነው። የውድድሩ የክብር አምባሳደር የሆነችው አትሌት ደራርቱ ቱሉ በጎዳና ሩጫው ላይ እንደምትሳተፍ ገልጻለች። ''ለመጨረሻ ጊዜ በውድድር የተሳተፍኩት ከስምንት ዓመት በፊት ነው፤ ከሁለት ዓመት በፊት በህዳሴው ግድብ ሩጫ ተሳትፎ ነበረኝ፤ ለአድዋው ሩጫ ልምምድ ሰርቼ 9 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትሩን በጫማ የተቀረውን 500 ሜትር በባዶ እግሬ ለመሮጥ ቃል እገባለሁ'' ብላለች። ኢዜአ እንደዘገበው የውድድሩ አምባሳደር ሆና በመመረጧ ከፍተኛ ኩራትና ክብር እንዲሁም እድለኝነት እንደተሰማት ተናግራለች። በአድዋ ድል እናቶችና አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው ያቆዩትን ታሪክና ጀግንነት ሁሉም በተሰማራበት መስክ ውጤታማ በመሆን በስራው ጀግና መሆን እንዳለበትነው የጠቆመችው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምዕራብ ጉጂ ዞን‼️

በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ጉጂ ዞን በፀጥታ ችግር ተዘግተው የነበሩ 33 ትምህርት ቤቶች #ማስተማር ጀምረዋል። በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ተፈጥሮ የነበረው የፀጥታ ችግር ተሻሽሎ  አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ዋና አስተዳዳሪው አቶ አበራ ቡኖ ተናግረዋል። በዞኑ ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ፈጥሮ እንደነበርም ገልጸዋል። በአባገዳዎች ሰብሳቢነት አስተዳደሩ ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አባላት ጋር በመወያየት በአሁኑ ወቅት በአካባቢው አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ጠቁመዋል። በዞኑ በሚገኙ ዘጠኝ ወረዳዎችና በሁለት ከተሞች የተካሄደውን የሰላም ውይይት ተከትሎ ተዘግተው የነበሩ 33 ትምህርት ቤቶች ተከፍተው ማስተማር መጀመራቸውን ጠቅሰዋል።

በፀጥታ ችግር አገልግሎት መስጠት ያቆሙ የመሰረተ ልማት ተቋማትም በአብዛኛው ሥራ መጀመራቸውን አስታውቀዋል። በዱግዳ ዳዋና ቡሌ ሆራ ዙሪያ ወረዳ ያልተከፈቱ አንዳንድ ትምህርት ቤቶችን ሥራ ለማስጀመር በአሁኑ ወቅት ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ውይይት እየተካሄደ መሆኑንም አቶ አበራ አመልክተዋል፡፡ በጉጂ ዞን በአሁኑ ወቅት 592 ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ተግባራቸውን በአግባቡ እየተወጡ ይገኛሉ። በትምህርት ቤቶቹ ከ300 ሺህ የሚበልጡ ተማሪዎችም መደበኛ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ መሆኑን ከዞኑ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

ምንጭ፦ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ🔝በጅማ ከተማ #የነዳጅ_እጥረት መከሱትን የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ገልፀዋል። መንግስት ችግሩን እንዲቀርፍም ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ብርጋዴር ጀኔራል #አሳምነው_ጽጌ

"በቅማንት ስም የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎች በሰነዘሩት ጥቃት #በአንድ መንደር 200 ቤቶች ተቃጥለዋል፤ 2 ሺ ዜጎች ተፈናቅለዋል፤ 55 ሰዎች ሞተዋል፡፡"
.
.

"ከሌላ አካባቢ መጥተው #በግጭት ሲሳተፉ የነበሩና የሞቱ ሶስት ሰዎች መኖራቸውን መታወቂያቸውን በመመልከት #አረጋግጠናል፡፡"
.
.

"ጥፋት #ለመፈጸም የተደራጀው ኃይል ለጊዜው #ተገቷል፤ የታጠቁ ኃይሎች በመሸጉበት ስፍራ ተደምስሰዋል፡፡ በአማራ ክልል በኦሮሚያ ልዩ ዞን ባቲ አካባቢና በጎረቤት ክልልም ሕገወጥ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ጣቢያዎች በቅርብ ርቀት አሉ። የእኛን እርምጃ ወስደናል፡፡ የቀረውንም ከሚመለከታቸው ጋር #መፍትሄ ለመስጠት በቅንጅት እየሰራን ነው፡፡"

©አዲስ ዘመን
@tsegabwolde @tikvahethiopia