TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን‼️

መጭው የጥምቀት በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር ተከብሮ እንዲውል ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር #ሰኢድ_አህመድ ለአብመድ እንደገለጹት የጥምቀት በዓል ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል፡፡

በዓሉ በአደባባይ የሚከበር በመሆኑ ከተለመደው ጊዜ የተለየ የተጠናከረ ጥበቃ ይዳረጋልም ብለዋል ረዳት ኮሚሽነሩ፡፡

በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከህብረተሰቡ ጋር ተቀላቅለው ወንጀል የሚፈጽሙ አካላትን ለመቆጣጠር የሰውር የወንጀል ክትትል አባላት አቅማቸው ከፍ እንዲል መደረጉንም ረዳት ኮሚሽነር ሰኢድ ተናግረዋል፡፡

በጥምቀት በዓል የውጭ ሀገራት ጐብኝዎች ቁጥር ይጨምራል፤ጐብኝዎች በሚጓጓዙበትና በሚያርፉበት አካባቢ ልዩ ጥበቃ እንደሚደረግም ገልጸዋል፡፡

ረዳት ኮሚሽነር ሰኢድ እንዳስታወቁት በዓሉ በሚከበርበት ወቅት ለተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይኖራሉ፡፡

በዚህ ወቅት አሸከርካሪዎች በተዘጋጀላቸው አማራጭ መንገዶች መጠቀም አለባቸው ነው፤ ፍጥነታቸውን ቀንሰው ማሽከርከር እንዳለባቸውም ጠቁመዋል፡፡

በዓሉን በማስመልከት በአንዳንድ አካባቢዎች የሚደረግ የጦር መሣሪያ ተኩስ በህግ ያስጠይቃል፡፡ስለሆነም ከእንደዚህ አይነት ድርጊት መቆጠብ ተገቢ መሆኑንም አሣስበዋል፡፡

ህብረተሰቡ በበዓሉ ወቅት ሊያጋጥም የሚችልን የወንጀል ድርጊት በስልክ ቁጥሮች 058 220 13 27 እንዲሁም 058 220 19 21 ደውሎ ፈጣን አገልግሎት ማግኘት እንደሚችልም ምክትል ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia