ከአርባ ምንጭ⬆️
ጋሞ ባይራኮ!
ጋሞይ ጊታኮ!
ዛሬ በተካሄደው የጋሞ ህዝብና የኦሮሞ ህዝብ ምክክርና ይፋ የምስጋና ፕሮግራም ላይ በርካታ የጋሞ #ናቶዎችና በርካታ የኦሮሞ #ቄሮዎች ተገኝተዋል።
ከዛ ባሻገርም የጋሞ ወጋ አባቶች የኦሮሞ አባገዳዎች እርስ በእርስ ለእርቅ ድርድር ምቹ መንገድ ፈጥረዋል።
በዛሬው ቀን ከተነሱ ሃሳቦች ውስጥ በቡራዩ በተነሳው እልቂት ቄሮ እጁ እንደሌለበት እናውቃለን ነገር ግን ቄሮ ይህንን የወንብዴ ግሩፕ ለማስቆም እንዴት ተሳነው? የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል።
በተጨማሪም በቀጣይ ቄሮና የኦሮሚያ መንግስት ለዚህ ጨዋ እና ይቅር ባይ ህዝብ ምን ዋስትና ይሰጣል? የሚል ጥያቄም ተነስቶ ነበር። ቡራዩ የሚገኙት የጋሞ ተወላጆች ከዚህ ቡኋላ አስተማማኝ ጥበቃ እንዲደረግላቸውም ተጠይቋል።
ከአመስጋኞቹ በኩልም ቄሮን በመወከል ይቅርታ የጠየቁ ሲሆን ከዚህ ቡኋላም የጋሞን ህዝብ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ በኦሮሚያ የሚገኙ የሌሎች ብሄረሰብ ህዝቦችን የመጠበቅ ግዴታ የኛ የቄሮና የክልሉ መሆኑን አስረድተዋል። ናቶንና የጋሞ ሽማግሌዎችንም አመስግነዋል።
በመጨረሻም ከሁለቱም ወገን የሰላም ፎረም የተቋቋመ ሲሆን ከኦሮሞና ከጋሞ ወጣቶች አራት አራት ወጣች በሰላም ፎረሙ ላይ እንዲካተቱ ተደርጓል።
©ፋሪስ ንጉሴ ከአርባምንጭ
@tsegabwolde @tikvahethiopia