TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከወለጋ ቄሮ⬆️

"ሀይ ፀጊሽ ናኦል እባላለዉ በምስራቅ ወለጋ ዞን የነቀምቴ ከተማ #ቄሮዎች ትላንት ጳጉሜ 4 እና 5 ብዙ በጎ አድራጎት ተግባር ስንሰራ ነበር። የተለያዮ ኣልባሳት፣ ጫማዎች፣ የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶችን እየሰበሰብን ነበር። አዲሱን አመት በማስመልከት ዛሬ የፕሮግራሙ ማጠቃለያ ላይ ጎዳና የሚኖሩ ህፃናትን ገላ በማጠብና ልብሳቸዉን በመቀየር መጨረሻ ላይ ከኬራጅ ሆቴል ያገኘነዉን ምግብ መግበናቸዋል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሁን! #ቄሮዎች በአዲስ አበባ ዋና ዋና መንግዶች በመኪና እየዞሩ እነዚህን መፈክሮች እያሰሙ ይገኛሉ...⬇️

እኛ ኢትዮጵያን እንወዳታለን!
#ዘረኝነትን እንጠላለን!
#ጥላቻን እንጠላለን!
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እንወዳችኋለን!
.
.
እኛ አማራን እንወዳለን!
እኛ ደቡብን እንወዳለን!
እኛ ትግራይን እንወዳለን!
እኛ ጉራጌን እንወዳለን!
እኛ ሱማሌን እንወዳለን!
.
.
እኛ ዘረኛ አይደለንም!
ለብዙ ዘመናት ዘረኛ ተብለናል እኛ ግን ዘረኛ አይደለንም!
እኛ የመጣነው ኦነግን ለመቀበል ብቻ አይደለም፤ እኛ የመጣነው #ፍቅርም ልናስተምር ነው!
ኢትዮጵያ #እናታችን ናት!
.
.
እኛ አሸባሪዎች አይደለንም!
እኛ ሀገር #አናፈርስም!
እኛ ኢትዮጵያን እንወዳታለን!
ኢትዮጵያ እናታችን ናት!
.
.
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች #እንዳችኋለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሁን! በአዲስ አበባ ከተማ ሰብሰብ ያሉ #ቄሮዎች በእግር እየተጓዙ መፈክሮቻቸውን እያሰሙ ይገኛሉ...

አዲስ አበባ የሁሉም ነች!
አዲስ አበባ የቄሮ ነች!
አዲስ አበባ የትግሬ ነች!
አዲስ አበባ የኦሮሞ ነች!
አዲስ አበባ የአማራ ነች!
አዲስ አበባ #የሁሉም ነች!
#ዘረኞች ወደመጣችሁበት!

@tsegabwolde
#update⬆️በነገው እለት አዲስ አበባ የሚገባውን የኦነግ አመራር ለመቀበል ከምሽት ጀምሮ አብዮት አደባባይ የሚገኙት #ቄሮዎች ምግብና መጠጥ እንዳላገኙ መገለጹን ተከትሎ የአዲስ አበባ ወጣቶች ከላይ በምስሉ በምትመለከቱት መልኩ ዳቦና ውኃ ይዘው እየሄዱ ይገኛሉ። #ኢትዮጵያዊነት ይህ ነው፤ ሌሎችም የከተማችን ወጣቶች አብዮት ለሚገኙት ወገኖቻችን እንድረስላቸው።

©ኤርሚያስ ቶኩማ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከለገጣፎ⬆️

"ፀጋ ለገጣፎ ከሰሞኑ በጣም ስጋት ላይ ነበርን ዛሬ ግን በጣም ደስ ብሎናል የአካባቢው #ቄሮዎች አይዟችሁ ምንም አትሆኑም በማለት ሰላማዊ ሰልፍ ወተዋል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ለገጣፎ ለገዳዲ⬆️

የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ #ቄሮዎች በቡራዩ ከተማ የተደረገውን ድርጊት አወገዘዋል። ቄሮዎቹ ዛረ ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ ድርጊቱ የኦሮሞን ህዝብ አይወክልም ብሎል። ኦሮሞ #አቃፊ እንጂ አግላይ አይደለም #ከሁሉም ብሄር ጋር አብሮ ኖሮል አሁንም ከሁሉም ጋሪ መኖራችን ይቀጥላል። ከመንግስት ጎን ሆነን እንሰራለን ብሎል በመልእክታቸው።

ምንጭ፦ OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቡራዩ ከተማ ነዋሪዎችና #ቄሮዎች የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ በትላንትናው ዕለት ቤቶችን #ሲያድሱ እና #ሲሰሩ ውለዋል።

በተጨማሪ፦

የተዘረፉና የተሸሸጉ ንብረቶች ለባለንብረቶች እንዲመለሱ ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር እንዲውሉ እየተሰራ ይገኛል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአርባ ምንጭ⬆️

ጋሞ ባይራኮ!
ጋሞይ ጊታኮ!

ዛሬ በተካሄደው የጋሞ ህዝብና የኦሮሞ ህዝብ ምክክርና ይፋ የምስጋና ፕሮግራም ላይ በርካታ የጋሞ #ናቶዎችና በርካታ የኦሮሞ #ቄሮዎች ተገኝተዋል።

ከዛ ባሻገርም የጋሞ ወጋ አባቶች የኦሮሞ አባገዳዎች እርስ በእርስ ለእርቅ ድርድር ምቹ መንገድ ፈጥረዋል።

በዛሬው ቀን ከተነሱ ሃሳቦች ውስጥ በቡራዩ በተነሳው እልቂት ቄሮ እጁ እንደሌለበት እናውቃለን ነገር ግን ቄሮ ይህንን የወንብዴ ግሩፕ ለማስቆም እንዴት ተሳነው? የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል።

በተጨማሪም በቀጣይ ቄሮና የኦሮሚያ መንግስት ለዚህ ጨዋ እና ይቅር ባይ ህዝብ ምን ዋስትና ይሰጣል? የሚል ጥያቄም ተነስቶ ነበር። ቡራዩ የሚገኙት የጋሞ ተወላጆች ከዚህ ቡኋላ አስተማማኝ ጥበቃ እንዲደረግላቸውም ተጠይቋል።

ከአመስጋኞቹ በኩልም ቄሮን በመወከል ይቅርታ የጠየቁ ሲሆን ከዚህ ቡኋላም የጋሞን ህዝብ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ በኦሮሚያ የሚገኙ የሌሎች ብሄረሰብ ህዝቦችን የመጠበቅ ግዴታ የኛ የቄሮና የክልሉ መሆኑን አስረድተዋል። ናቶንና የጋሞ ሽማግሌዎችንም አመስግነዋል።

በመጨረሻም ከሁለቱም ወገን የሰላም ፎረም የተቋቋመ ሲሆን ከኦሮሞና ከጋሞ ወጣቶች አራት አራት ወጣች በሰላም ፎረሙ ላይ እንዲካተቱ ተደርጓል።

©ፋሪስ ንጉሴ ከአርባምንጭ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለነቀምት ነዋሪዎች‼️

ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል #የተፈናቀሉ ወገኖቻችን በ03፣ 04 እና 07 ቀበሌ፤ በነቀምት የመምህራን ኮሌጅ፣ ዳንዲ ቦሩ ኮሌጅ እንዲሁም በነቀምት ከተማ አስተዳደር ግቢ ውስጥ ይገኛሉ። እነኚህ ወገኖቻችን ምግብ እና መኝታ ያስፈልጋቸዋል። የነቀምት ነዋሪዎች እና #ቄሮዎች በቻላችሁት አቅም ድጋፍ እንድታደርጉላቸው ጥሪያችንን እናቀርባለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለነቀምት ነዋሪዎች‼️

ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል #የተፈናቀሉ ወገኖቻችን በ03፣ 04 እና 07 ቀበሌ፤ በነቀምት የመምህራን ኮሌጅ፣ ዳንዲ ቦሩ ኮሌጅ፣ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም በነቀምት ከተማ አስተዳደር ግቢ ውስጥ ይገኛሉ። እነኚህ ወገኖቻችን ምግብ እና መኝታ ያስፈልጋቸዋል። የነቀምት ነዋሪዎች እና #ቄሮዎች በቻላችሁት አቅም ድጋፍ እንድታደርጉላቸው ጥሪያችንን እናቀርባለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia