TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የአገር መከላከያ ሚኒስቴር‼️

በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተግባር ላይ የነበሩ ወታደሮች ኮንቮይ ላይ #የአልሸባብ ታጣቂዎች #ጥቃት_መፈጸማቸውን የአገር መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

#የአገር_መከላከያ_ሚኒስቴር ለሪፖርተር በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፣ ‹‹በሠራዊቱ ላይ ጥቃት የደረሰው ኮንቮዩ ከቡራሃካባ ወደ ባይዶአ በመጓዝ ላይ እያለ ሲሆን፣ ሠራዊታችን ጥቃቱን በጽናት በመመከት ኮንቮዩን ባይዶአ ይዞ ገብቷል፤›› ብሏል፡፡

ሠራዊቱ ካሁን ቀደም በርካታ የአልሸባብ ጥቃቶችን #በመመከት አልሸባብን ያዳከመው መሆኑን ያስታወሰው መግለጫው፣ በአሁኑ ጥቃትም አልሸባብ በቀቢፀ ተስፋ የሠራዊቱን ንቅናቄ ለመግታት ሙከራ እንዳደረገ አስታውቋል፡፡

በመሆኑም ሠራዊቱ የአልሸባብን ጥቃት ተከትሎ ጠንካራ የማጥቃት እርምጃ ለመውሰድ በስምሪት ላይ እንደሚገኝም ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

ዓርብ ጥር 10 ቀን 2011 ዓ.ም. የአገር መከላከያ ሠራዊት አራት መኪኖች ላይ ጥቃት ተፈጽሞ በርካታ የሠራዊቱ አባላት ተገድለዋል የሚል ዘገባ የወጣ ቢሆንም፣ የመከላከያ ሚኒስቴር መግለጫ ጥቃቱ ምን ያክል ጥፋት እንዳደረሰ አልገለጸም፡፡ ሆኖም የመከላከያ ሠራዊት በአሚሶም ተልዕኮ በሶማሊያ ሰላም በማስፈን ረገድ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ አስታውሷል፡፡

ምንጭ:- ሪፓርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update መቅዲሹ፤ በደረሰው ጥቃት 19 ተገደለዋል። ትናንት ምሽት በአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ፍንዳታ በደረሰባት የሶማሊያ ዋና ከተማ #ሞቃዲሾ ዛሬም ተኩስ መቀጠሉ እየተነገረ ነው። በፍንዳታው የደረሰውን ጨምሮ እስካሁን ቢያንስ 29 ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል። በርካቶችም ተጎድተዋል። ትናንት ምሽት አንድ አጥፍቶ ጠፊ እንቅስቃሴ በሚበዛበት መንገድ ዳር ከሚገኝ ሆቴል አቅራቢያ በመኪና ውስጥ ባጠመደው ፈንጂ ራሱን ሲያጋይ እሳቱ ተዛምቶ ጉዳቱን እንዳሰፋውም ተጠቅሷል። ከፍንዳታው በኋላ የሶማሊያ ኃይሎች በአካባቢው ወደ አንድ ሕንፃ ተጠግተው ከመሸጉ #የአልሸባብ ታጣቂዎች ጋር መታኮስ መቀጠላቸውንም ተገልጿል። ሆቴሉ ውስጥ የአልሸባብ ታጣቂዎች ሰላማዊ ሰዎችን አግተው መቆየታቸውን የሶማሊያ መንግሥት የዜና አውታር ዘግቧል። የሀገሪቱ የፀጥታ ኃይል ባልደረባ አብድራህማን አሊ ለፈረንሳይ የዜና ወኪል የተጎዱ ሰዎችን የማዳን ሥራ እየተከናወነ መሆኑን፣ ተኩሱ በመቀጠሉም የሟቾች ቁጥርም ሊጨምር እንደሚችል አመልክተዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ አቅራቢያ በአንድ የጦር ሰራዊት ካምፕ ዛሬ የአልሸባብ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ቢያንስ ስድስት መንግሥት ወታደሮች እና አንድ ካሜራ ባለሙያ ገደሉ። ሌሎች አስራ ሦስት ሰዎች አቆሰሉ፡፡
 
የሶማሊያ ባለሥልጣናት ፈንጂ የተጫኑ መኪናዎች ተከታትለው ከጦር ሰፈሩ ጋር በመላተም ፍንድታውን ካደረሱ በኋላ ከሁለት በኩል ተኩስ እንደከፈቱበት ነው የገለፁት።
ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደው አልሸባብ ቢያንስ ሃምሳ የመንግሥት ወታደሮች ገድያለሁ ብሉዋል። መንግሥት ስድስት ሰው ተገድሎብናል ነው ያለው። የታችኛው ሸበሌ ክፍለ ግዛት አገረ ገዢ ኢብራሂም አደን ናጃህ ለቪኦኤ የሶማሊኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል የመንግሥት ኃይሎች 23 #የአልሸባብ ነውጠኛ ገድለዋል ብለዋል።

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Photoshop

ከሰሞኑን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች #ISIS የለቀቀው ተብሎ እየተሰራጨ የሚገኘው #የኢትዮጵያ ስም ያለበት ፎቶ #ሀሰተኛና በphotoshop የተሰራ ነው።

NB. በፎቶው ላይ የምትመለከቷቸው ታጣቂዎች #የISIS ሳይሆኑ #የአልሸባብ ታጣቂዎች ናቸው። #TIKVAH_ETH

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Somalia #SW ሀሰን ኢብራሂም ሉግቡር ተገደሉ። የሶማሊያ ደቡብ ምዕራብ ክልል ፍትህ ሚኒስትር ሀሰን ኢብራሂም ሉግቡር በባይዶዋ ከነ ልጃቸው በአጥፍቶ ጠፊ የቦንብ ጥቃት ተገደሉ። ሚኒስትሩ የተገደሉት ዛሬ ዓርብ ዕለት ከመስጂድ ሲወጡ በተፈፀመ ጥቃት ነው። በጥቃቱ ሌሎች 11 ሰዎችም ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም። የደቡብ ምዕራብ ክልል ፕሬዜዳንት አብዲአዚዝ ሀሰን…
" የሽብር ጥቃቱን አጥብቄ አወግዛለሁ " - ጠ/ሚ ሀምዛ አብዲ ባሬ

ትላንት በባይድዋ የተፈፀመውን የሽብር ጥቃት አጥብቀው እንደሚያወግዙ የሶማሊያ ጠ/ሚ ሀምዛ አብዲ ባሬ ገልፀዋል።

ትላንት በባይዶዋ በተፈፀመው ጥቃት የደቡብ ምዕራብ ክልል የፍትህ ሚኒስትር ሀሰን ኢብራሂም ከነልጃቸው እንዲሁም በርካታ ንፁሃን መገደላቸው አይዘነጋም።

የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር በጥቃቱ የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀው የሽብር ድርጊቱን አጥብቀው አውግዘዋል።

ለትላንቱ ጥቃት ኃላፊነት የወሰደ ባይኖርም የደቡብ ምዕራብ ክልል ፕሬዜዳንት አብዲአዚዝ ሀሰን ሞሀመድ ከጥቃቱ ጀርባ #የአልሸባብ የሽብር ቡድን መኖሩን ማመልከታቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#BeledHawo

በደቡባዊ ሶማሊያ ፤ ጌዶ ክልል ፣ በሌደሀዎ በተባለ ወረዳ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ኢትዮጵያውያን እና አንድ ሶማሊያዊ መገደላቸውን ቢቢሲ ሶማልኛ ዘግቧል።

በዚህ ምክንያት በርካቶች ስጋት ውስጥ መሆናቸው ተነግሯል።

ታጣቂዎቹ ሌሊት ኢትዮጵያውያን ወደ ሚኖሩበት ቤት በመግባት በፈጸሙት ጥቃት 3 ሴቶች እና 3 ወንዶችን ሲገድሉ 1 ሶማሊያዊም መገደላቸው ተነግሯል።

ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ በሶማሊያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ተወካይ በሰጡት ቃል ፤ ቅዳሜ ሌሊት 6 እሁድ 1 በተለያየ ስራ ላይ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ተገድለዋል ብለዋል።

" ከተገደሉት መካከል ሁለቱ ሕጻናት ሲሆኑ ፣ እናት እና አባቷ ተገድለውባት ብቻዋን የቀረች ሕጻንም አለች " ሲሉ አክለዋል።

" የተገደሉት ሰዎች ወደ አገራቸው ተመልሰው በሥነ ሥርዓት ቀብራቸው እንዲፈጸም እንፈልጋለን። መንግሥት ይህን ማድረግ ይችላል። ለተገደሉትም ፍትሕ እንዲሰፍንም እንፈልጋለን " ሲሉ አክለዋል።

ጥቃቱ ተከትሎ ኢትዮጵያውያን ስጋት ላይ እንደሆኑና በርካቶች ወደ አገር ቤት መመለስ እንደሚፈልጉም ተናግረዋል።

የበለደሀዎ አስተዳዳሪ አብዲራሺድ አብዲ ፤ ግድያው ሌሊት 9 ሰዓት መፈጸሙን እንደታወቀ አመልክተዋል።

ግድያ መፈፀሙ የታወቀው የአካባቢው የፀጥታ ባልደረቦች የተኩስ ድምጽ ከሰሙ በኋላ ሲሆን 7 ሰዎች ተገድለው መገኘታቸውን አስረድተዋል።

" ማቾቹ በአጠቃላይ ለሥራ የመጡ ስደተኞች ናቸው " ሲሉ ገልጸዋል።

በአካባቢው ሆስፒታል የሚሠራ አንድ ዶክተር በሰጠው ቃል በጥቃቱ የተገደሉ የ6 ኢትዮጵያውያን አስከሬን ወደ ሆስፒታሉ መምጣቱን አረጋግጧል።

በተጨማሪ ጉዳት የደረሰባቸው ሌሎች 6 ሰዎች ሆስፒታል መግባታቸውንም ገልጿል።

ምንም እንኳን እስካሁን ከግድያው ጀርባ ማን እንዳለ ያልታወቀና ኃላፊነት የወሰደም አካል የሌለ ቢሆንም የአካባቢው አስተዳዳሪ " ማስረጃዎች እንደሚጠቁሙት ገዳዮቹ #የአልሸባብ አሸባሪዎች ናቸው " ብለዋል።

" እስካሁን አልተያዙም። ለምን ስደተኞን ዒላማ አደረጉ ለሚለው ጥያቄ፣ ይህ ግድያ በመላው አገሪቱ ከሚፈጸመው ግድያ የሚለይ አይደለም " ሲሉ ተናግረዋል።

መረጃው የቢቢሲ ሶማልኛ አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia