TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጥንቃቄ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ፦

" ምናባዊ ንብረትን (ዲጂታል መገበያያ ገንዘብ) ለግብይት ወይም ለክፍያ መጠቀም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዕውቅና ያልተሰጠው ድርጊት በመሆኑ ህብረተሰቡ ከእንደዚህ አይነት ሕገ-ወጥ ተግባር እራሱን ይጠብቅ።

የኢትዮጵያ የገንዘብ መደብ ብር እንደሆነና በብሔራዊ ባንክ በሌላ አኳኋን ካልተፈቀደ በስተቀር በሀገሪቱ የሚከናወኑ ማናቸውም የገንዘብ ግንኙነቶች ሁሉ የሚከፈሉት በብር እንደሚሆን የብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 591/2000 በግልጽ ይደነግጋል።

በተጨማሪም በክፍያ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 718/2003 መሠረት በየትኛውም የክፍያ መፈጸሚያ ሰነድም ሆነ ሥርዓት ያለ ብሔራዊ ባንክ ፍቃድ የገንዘብ ዝውውርም ሆነ ገንዘብ ነክ አገልግሎት መስጠት አይቻልም፡፡

ነገር ግን ከጥናት ለመረዳት እንደተቻለው በአሁኑ ወቅት ከህግ እውቅና ውጪ የክሪፕቶ ከረንሲ፣ እንደ ቢትኮይን እና የመሳሰሉት የዲጂታል መገበያያ ገንዘብ አገልግሎት በኢትዮጵያ እየተስፋፋ መጥቷል።

በተጨማሪም ይህ ተግባር ከብሔራዊ ባንክ እውቅና ውጪ ከፍተኛ የገንዘብ ዝውውር የሚደረግበት እና በተለይ በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ለማሸሽ ምቹ ሁኔታን እየፈጠረ እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል።

ይህ እየተስተዋለ ያለው የዲጂታል መገበያያ ገንዘብን ለግብይት ወይም ለክፍያ መጠቀም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዕውቅና ያልተሰጠው ድርጊት በመሆኑ ህብረተሰቡ ከእንደዚህ አይነት ሕገ-ወጥ ተግባር እራሱን መጠበቅ ይኖርበታል።

ይህን ፈጽመው በሚገኙ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ ሲሆን ህብረተሰቡ ይህንን ህገወጥ ተግባር የሚሠሩ አካላትን ሲመለከት ለብሔራዊ ባንክ እና ለሚመለከታቸው ሕግ አስከባሪ አካላት ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ እናቀርባለን ። "

#የኢትዮጵያ_ብሄራዊ_ባንክ

@tikvahethiopia
#የኢትዮጵያ_እና_ግብፅ_ፍልሚያ !

ሀገራችን ኢትዮጵያ ፍፁም የበላይ ሆና ባጠናቀቀችበት የመጀመሪያው አጋማሽ ግብፅ አንድም የጎል ሙከራ አላደረገችም።

የመጀመሪያ አጋማሽ ውጤትና የበላይነት በሁለተኛው አጋማሽም እንዲቀጥል እየተመኘን ድል ለሀገራችን 🇪🇹ይሆን ዘንድ እንመኛለን።

የሁለተኛው አጋማሽ ፍልሚያ ጀምሯል።

@tikvahethiopia
#ደራሽ

በሳምንት ለአምስት ቀናት የሚታየው ተከታታይ ድራማ ፦

በኢትዮጵያ ያለው የፊልም ኢንደስትሪ በተቀዛቀዘበት በዚህ ወቅት በተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማዎች ኢንዱስትሪውን ለመነቃቃት ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል።

በዘርፉ ላይ ተግዳሮት ሆኖ የቆየውን የአቅም ችግር በመጠኑም ቢሆን በመቅረፍ ለሙያተኞች እንዲሁም ለተመልካቾች ትልቅ እድል ይዞ የመጣው አቦል ቲቪ ተጠቃሽ ነው፡፡

የሀገራችን የፊልም ኢንዱስትሪ ፈተና ውስጥ በገባበት በዚህ ወቅት አቅም ያላቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት መቀላቀላቸው ሰፊ የሥራ ዕድል ለሚፈጥረው ለዘርፉ ትልቅ ተስፋን የሚሰጥ ሆኗል።

አቦል ከኤምኔት ቻናሎች አንዱ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከ80 በላይ #የኢትዮጵያ ፕሮዳክሽን ካምፓኒዎች በተለያየ መልኩ አብረው የመስራት ዕድል አግኝተዋል።

አቦል ቴሌቪዥን ለተመልካች ካቀረባቸው ውስጥ '' ደራሽ '' የተሰኘው ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ አንዱ ሲሆን ከ200 በላይ ባለሞያዎችን በማሳተፍ ከሰኞ እስከ አርብ በተከታታይ ይተላለፋል፡፡

ያንብቡ : https://telegra.ph/ደራሽ-08-03
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ

በበረራ ቁጥር ET343 ላይ ስለነበረው ክስተት እና ከዛም ጋር ተያይዞ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ስለደረሱ ሪፖርቶች ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል።

አየር መንገዱ ምርመራውን አከናውኖ ሲጨርስ ምን እንደተፈጠረ በማረጋገጥ ተገቢውን የእርምት እርምጃ ይወስዳል ፤ እስከዛው የበረራ ሰራተኞቹ ታግደው ይቆያሉ።

በወቅቱ ምን እና እንዴት ተፈጠረ ? ስለሚለው በጉዳዩ ቀጥተኛ ባለቤት ከሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ መስማት የሚያስፈልግ ሲሆን ምርመራ እንደተጠናቀቀ ጉዳዩን አየር መንገዱ ይገልፃል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በድፍን አፍሪካ አንጋፋና ቁጥር አንድ ፤ በዓለም ደረጃ ተወዳዳሪ ፣ በደህንነቱ መረጋገጥ እና በአገልግሎቱ ሁሉም የሚመርጠው ፤ የሀገርን ክብር ይዞ የሚንቀሳቀስ ሀገር የሚያስተዋውቅ፣ በርከት ያለ ሀብት የሚያስገባ የኢትዮጵያ ህዝብ አለኝ የሚለው ትልቁ እና ጠንካራው ተቋም ነው።

@tikvahethiopia
የዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች ጥያቄ ምንድነው ? ፤ የትምህርት ሚኒስቴር ምላሽስ ?

• " እንደዚህ ዓይት ውሳኔ ላይ የተደረሰው አጠቃላይ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ኃላፊዎች ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው " - የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት ፍቅረስላሴ አካሉ (ለአዲስ ስታንዳርድ)

• " ማህበራችን የሥራ ማቆም አድማ እንዲደረግ ጥሪ አላቀረበም " - ዶ/ር በፍቃዱ ዘለቀ (ለዶቼ ቨለ)

• " መምህራን የሚያነሷቸውን ጥያቄዎችን ህጋዊ ከሆነው #የኢትዮጵያ_መምህራን_ማህበር ጋር ብቻ በመነጋገር የሚፈታ ነው " - ወይዘሮ አመለወርቅ ህዝቅኤል (ከትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ

በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እየሰሩ ያሉ መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች ከህዳር 26 ቀን 2015 ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የስራ ማቆም አድማ እንደሚመቱ የሚገልፅ ፅሁፍ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ከሰሞኑን ተሰራጭቷል።

መምህራኑና ቴክኒካል ረዳቶቹ አድማ እንደሚያደርጉ የተገላፀበት ይኸው ፅሁፍ ለትምህርት ሚንስቴር እና ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መፃፉን የሚገልፅ ሲሆን " ያቀረብነው ጥያቄ ምላሽ አላገኘም " በሚል ምክንያትነው አድማው ይደረጋል የሚለው።

ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ቃላቸውን ለ " አዲስ ስታንዳርድ " ሚዲያ የሰጡ መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች ተከታዩን ብለዋል ፦

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት ፍቅረስላሴ አካሉ ፦

" እንደዚህ ዓይት ውሳኔ ላይ የተደረሰው አጠቃላይ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ኃላፊዎች ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው።

ስራ የማቆሙ ሃሳብ ሁሉም መምህራን የሚጋሩት ነው። በቀጣይ የዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማህበር መግለጫ ያወጣል። "

የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ መምህር ጥላሁን ረጋ ፦

" የመምህራን ደሞዝ አነስተኛ በመሆኑ በአገሪቱ ያለውን የኑሮ ውድነት መቋቋም አልተቻለም።

በሁለተኛ ዲግሪ ደረጃ ላሉ መምህራን የሚደርሳቸው የተጣራ ደሞዝ  8 ሺህ 5 መቶ ብር ብቻ ነው። ይህ እንዲሻሻልልን የጠየቅን ቢሆንም እስካሁን ድረስ አልተመለሰልንም።

መንግስት የመምህራንን ጥያቄ ባለመመለሱና ችላ  በማለቱ በትምህርት ጥራቱ ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እያደረሰ ነው። ከምስራቅ አፍሪካ በኢኮኖሚ ትልቅ ሆና ለመምህራን ዝቅተኛ ደሞዝ የምትከፍል ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት።

የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ መምህራን በሙሉ ስራ ለማቆም ዝግጁ ናቸው። "

አንድ ስማቸውን መግለፅ ያልፈለጉ የዲላ ዩኒቨርሲቲ መምህር ፦

" የመምህራን ማህበር #ለጥያቄዎቻችን ትኩረት መስጠት ባለመቻሉ ከሁሉም ዩኒቨርሲቲ የተውጣጡ መምህራን ተመካክረንበት ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች በኩል መግለጫችንን ይፋ አድርገናል።

መምህራን ወር በደረሰ ቁጥር የቤት ኪራይ ምን እከፍላለሁ ልጆቼን ምን አበላለሁ እያለ በመጨናነቅ ለማስተማር በቂ ዝግጀት ስለማያደርግ የትምርት ጥራቱ ላይ ተፅኖ እያደረሰ ነው። "

(መምህራንና ቴክኒካል ረዳቶች የስራ ማቆም አድማ እንደሚያደርጉ የሚገልፀው ፅሁፍ በዚህ የተያያዘ ነው ፦ https://telegra.ph/University-11-29

የኢትዮጵያ የዩኒቨርስቲዎች መምህራን እና ቴክኒክ ረዳቶች ማኅበር ለዶቼ ቨለ ሬድዮ በሰጠው ቃል  በዩኒቨርሲቲዎች መምህራን የፊታችን ሰኞ ኅዳር 26 ቀን/2015 ይደረጋል የተባለውን የሥራ ማቆም አድማ
እኔ አልጠራሁትም ሲል አስታውቋል።

ፕሬዜዳንቱ ዶክተር በፍቃዱ ዘለቀ ፤ የመምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች ማኅበር የሥራ ማቆም አድማ እንዲደረግ ጥሪ አላቀረበም ብለዋል። ተናግረዋል።

ዶክተር በፍቃዱ ፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ ሲሆን የሚመሩት ማኅበር ለኢትዮጵያ መንግሥት የቀረቡት 14 ጥያቄዎች በእርግጥም ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች መሆናቸውን ቢያረጋግጡም የሥራ ማቆም አድማ ግን አልጠራንም ሲሉ ገልጸዋል።

ማኅበሩ ይህንን ያደረጉት " የማናውቃቸው የተደራጁ አካላት ናቸው " ብሏል። ይህን ያደረጉ ያላቸውንም አካላት እንደሚከስ ለዶቼቫለ ሬድዮ አሳውቋል።  

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ " መምህራን የሚያነሷቸውን የተለያዩ ጥያቄዎች ለመፍታት ከመምህራን ማህበር ጋር በቅርበት እየሠራ መሆኑን " ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ትላንት ለህ/ተ/ም/ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተናግረዋል።

መምህራኑ ባነሱት ጉዳይ አስተያያታቸውን ለቲክቫህ  የሰጡት የትምህርት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ አመለወርቅ ህዝቅኤል በበኩላቸው ፤ መመህራን የሚያነሷቸውን ጥያቄዎችን ህጋዊ ከሆነው የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ጋር ብቻ በመነጋገር የሚፈታ መሆኑን አመልክተዋል።

@tikvahethiopia
የአምባሳደር ሄኖክ ተፈራ የስራ ጊዜ አበቃ።

በፈረንሳይ፣ ስፔን፣ፖርቹጋል ፣ ሞናኮ እንዲሁም UNSECO #የኢትዮጵያ 🇪🇹 አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ የስራ ጊዜያቸውን እንዳጠናቀቁ አሳውቀዋል።

አምባሳደር ሄኖክ በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰራጩት ፅሁፍ ፤ በፈረንሳይ፣ ስፔን፣ ፖርቹጋል፣  ሞናኮ እና UNSECO በአምባሳደርነት ሀገራቸውን ያገለገሉበት የስራ ጊዜ ማብቃቱን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያን በውጪ ሀገር ከወከል የበለጠ ትልቅ ነገር እንደሌለ የገለፁት አምባሳደር ሄኖክ ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ሀገራቸውን የማገልገል እድል ስላመቻቹላቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በተጨማሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ ፓሪስ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና ማህበረሰቡን አመስግነዋል ፤ ሰላምና ብልፅግናን ለኢትዮጵያ ተመኝተዋል።

@tikvahethiopia
#Tigray

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከአቢ ዓዲ – ዐድዋ የተዘረጋው የባለ 132 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና 90 % መጠናቀቁን ዛሬ ምሽት አሳውቋል።

የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ጥገና በአብዛኛው በመጠናቀቁ የዐድዋ እና አክሱም ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኃይል እንዲያገኙ ለማድረግ በነገው ዕለት የሙከራ ሥራ እንደሚሠራ ገልጿል።

በተጨማሪም ከዐድዋ – ሽረ ማከፋፈያ ጣቢያ ድረስ የተዘረጋው የ66 ኪሎ ቮልት የሥርጭት መስመር በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠግኖ የተጠናቀቀ ቢሆንም ከሽረ ማከፋፈያ ጣቢያ ኃይል ለመስጠት የሙከራ ሥራ ሲከናወን በብሬከሩ ላይ ችግር ማጋጠሙ ተገልጿል።

የብሬከሩን ብልሽት በመጠገን ከመስመሩ ኃይል የሚያገኙ አካባቢዎች ኃይል እንዲያገኙ ይደረጋል ተብሏል።

#የኢትዮጵያ_ኤሌክትሪክ_ኃይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከውሸት ዜናዎች ተጠንቀቁ። በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) በህይወት በነበረበት ሰዓት የዓይን ብሌኑን ለመለገስ ቃል በገባው መሰረት የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ የአርቲስቱን ቃል ተፈፃሚ ማድረጉ አይዘነጋም። ነገር ግን ከአርቲስት ታሪኩ ጋር በተያያዘ በዩትዩብ እና በሌሎች ሶሻል ሚዲያዎች ሀሰተኛ ዜናዎች እና መልዕክቶች እየተሰራጩ መሆኑን የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ አሳውቋል።…
#እንድታውቁት

ስለ ዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ፦

(የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ)

- የዓይን ባንኩ ንቅለ ተከላ የተደረገላቸው ሰዎች የማን እንደተሰራላቸው አያሳውቅም፤

- ባንኩ አስፈላጊውን ፍተሸ በማድረግ ለንቅለ ተከላ ማዕከላት ያሰራጫል፤

- የዓይን ባንኩ የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ህክምና ከሚሰሩ ተቋማት ጋር ይሰራል፤

- የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ህክምና የሚሰጠው የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ የሚሰራበቸው ማዕከላት ውስጥ ብቻ ነው እነዚህም ፦
👉 ዳግማዊ ምኒልክ ኮምፕርሄንሲቭ ሪፈራል ሆሰፒታል
👉 ቅ.ጳውሎስ ሚሊኔም ኮሌጅ
👉 ጎንደር ስፔሻላይዝድ ማስተማሪያ ሆስፒታል
👉 ጅማ ስፔሻይዝድ ማስተማሪያ ሆስፒታል
👉 ሐዋሳ ስፔሻላይዝድ ማስተማሪያ ሆስፒታል ናቸው።

በተጨማሪም አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ የግል የዓይን ህክምና ጣቢያወች መካከል ፦
👉 ብሩህ ቪዢን ልዩ የዓይን ክሊኒክ
👉 ዋጋ ቪዥን ልዩ የዓይን ክሊኒክ
👉 አልአሚን የዓይን ህክምና ማዕከል
👉 ላቪስታ ስፔሻሊስት የዓይን ክልኒክ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዓይን ባንክን በምን ላግኛቸው ?

አድራሻ ፦ ዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ

ስልክ ፦
0111223838
0930006367
0930006368
Email [email protected]

#የኢትዮጵያ_ዓይን_ባንክ

@tikvahethiopia
አዲስ አበባ 🛫 መቐለ !

#ከአዲስ_አበባ ወደ #መቐለ ከነገ ጀምሮ ዳግም በረራ እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፥ " ተቋርጦ የነበረው ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ የአየር ትራንስፖርት በነገው ዕለት ይጀምራል " ብለዋል።

" በፌዴራል መንግስቱ እና በህወሓት መካከል የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የአቬየሽን ሰራተኞች ወደ መቐለ አቅንተው የመቐለ አየር መንገድ ለበረራ ምቹ ሁኔታ ላይ መሆኑን አረጋግጠዋል " ሲሉ አቶ መስፍን ገልፀዋል።

ነገ በሚጀምረው በረራ በቀን አንድ ጊዜ የሚካሄድ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን የደንበኞችን ፍላጎትን መሰረት በማድረግ የበረራው ቁጥሩ ከፍ ሊል የሚችልበትን ሁኔታ እንደሚፈጠርም አሳውቀዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው ፤ ተቋርጦ የነበረውን የበረራ እንቅስቃሴ #በሁሉም የትግራይ ክልል የበረራ መዳረሻዎች ለማስጀመር ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነም ዛሬ በሰጡት መግለጫ አንስተዋል፡፡

" ነገ የሚጀምረው በረራ (ወደ መቐለ) ከሌላው ወገኑ ጋር ግንኙነቱ ተቋርጦ የነበረውን የትግራይ ህዝብ ዳግም እንዲገናኝ ለማድረግ ትልቅ እድል የሚፈጥር " ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈ የሸቀጦችና ሌሎች ተደራሽ የመሆን እጥረት የነበረባቸውን የሰብዓዊ ድጋፎችን በበቂ ተደራሽ ለማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ይህም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታውን ከፍ ማድረግ የሚያስችል እንቅስቃሴ መሆኑንም ዋና ስራ አስፈፃሚው ገልፀዋል፡፡

#የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ #ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia