TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሳዛኝ ዜና‼️

ከበኒሻንጉል ጉሙዝ መስተዳድር ርዕሠ-ከተማ አሶሳ 18 መንገደኞችን አሳፍሮ ቶንጎ ወደተባለዉ ልዩ ወረዳ ይጓዝ የነበረ መለስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ አዉቶቡስ በተቀበረ ፈንጂ ጋይቶ 10 ተሳፋሪዎች ሞቱ፣ቁጥራቸዉ በዉል ያልታወቀ ቆሰሉ።

የበኒ ሻንጉል ጉሙዝ መስተዳድር ፖሊስ እንዳስታወቀዉ አዉቶቡሱ በተቀበረ ፈንጂ የጋየዉ ቶንጎ-ጎሬ በተባለዉ አካባቢ ጠጠራማ ጎዳና ላይ ሲጓዝ ነዉ።

በፍንዳታዉ የቆሰሉ ሰዎች ቤጊ ሆስፒታል ዉስጥ ሕክምና እየተደረገላቸዉ ነዉ።መኪናዉ የግለሰብ ነዉ።

የአሶሳዉ የDW ዘጋቢያ ነጋሳ ደሳለኝ በስልክ እንደገለጠው የበኒሻንጉል ጉሙዝ መስተዳድን ከምዕራብ ወለጋ (ኦሮሚያ) ጋር በሚያዋስነዉ ቶንጎ ልዩ ወረዳ ባለፈዉ ሰኔ በተቀሰቀሰ ጎሳን የተባለበስ ግጭት ሰዎች ተገድለዉ ነበር። ያሁኑ የፈንጂ አደጋ ካለፈዉ ግጭት ጋር ሥለ መያያዝ አለመያያዙ ግን የታወቀ ነገር የለም። ፈንጂዉን የቀበረዉ ወገን ማንነትም እስካሁን ግልፅ አይደለም።

ምዕራብ ኦሮሚያን ከበኒ ሻንጉል መስተዳድር ጋር በሚያዋስኑ ድንበሮች ሰኔ የተጀመረዉ ደም አፋሳሽ ግጭት ከመስከረም አጋማሽ ወዲሕ ተባብሶ የበርካታ ሰዎች ተገድለዋል።በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ተፈናቅለዋል።

ምንጭ፦ DW የአማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቀድሞው ርዕሰ ብሄር ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ቀብር ስነ ሥርዓት ሲከናወን ውሏል፡፡ በቅድሥት ሥላሴ ካቴድራል በተከናወነው የቀብር ስነ ሥርዓት ላይ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ተገኝተዋል፡፡ ቀደም ሲል ቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጆቻቸው፣ ሚንስትሮች፣ ከፍተኛ ሌሎች የመንግሥት ባለስልጣናት እና የውጭ ሀገራት አምባሳደሮች በተገኙበት በሚለኒዬም አዳራሽ ስንብት ተደርጎላቸዋል፡፡

Via~WazemaRadio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ተስፋዬ እና አቶ ማርክስ‼️

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ የወንጀል ችሎት በቀድሞዎቹ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባልደረቦች አቶ ተስፋዬ ኡርጌ እና አቶ ማርክስ ፀሃዬ ላይ ፖሊስ የጠየቀውን የጊዜ ቀጠሮ ፈቀደ።

ማርክስ ፀሃዬን በተመለከተ መርማሪ ፖሊስ ከዚህ በፊት በተሰጠው ጊዜ ተገቢውን ስራ መስራቱን ገልጾ፥ ቀሪ ስራዎችን ለመስራት የ14 ቀን ጊዜ ጠይቆ ችሎቱ በከፊል ተቀብሎታል።

ከሰኔ 16ቱ ጥቃት ጋር በተያያዘ የቀረበባቸው አዲስ የወንጀል ተሳትፎን በተመለከተ ማቅረብ አይገባም የሚል የህግ ክልከላ አለመኖሩን በመጥቀስም፥ መርማሪ ፖሊስ ይቀረኛል ያለውን ስራ አጠናቆ እንዲመጣ ከታህሳስ 8 ቀን ጀምሮ የሚታሰብ 14 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።

በከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና ሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ጋር በተያያዘም ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ችሎቱ ፈቅዷል።

ተጠርጣሪው በእስር ቦታ ላይ ሰብዓዊ መብቴ እየተጣሰ ነው በሚል ያቀረቡትን አቤቱታ ፖሊስ አጣርቶ እንዲያቀርብ ችሎቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ከዚህ ባለፈም ግለሰቡ ደመወዛቸው በፍርድ ቤት ሳይታገድ እየተከፈላቸው አለመሆኑን ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል።

ፍርድ ቤቱ መርማሪ ፖሊስ ጉዳዩ እንዲፈታ እንዲያግዛቸው ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥብቅ ማስታወቂያ🔝ለሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች...
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥብቅ ማስታወቂያ🔝ለቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች...
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሜጀር ጀኔራል ክንፈ ዳኛው‼️

በሜጀር ጀኔራል #ክንፈ_ዳኘው ላይ መርማሪ ፖሊስ የጠየቀው 14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ።በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት የቀረቡት ቀድሞው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ላይ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፍርድ ቤት ፈቀደ።

አመልካች መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪው ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ላይ ተጨማሪ የሙስና ወንጀል ድርጊት ማግኘቱን ከትናንት በስቲያ ለችሎቱ አመልክቶ ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቆ ነበር።

ድርጅቱ የሚያከናውናቸውን ስምምነቶች 90 በመቶ በተጠርጣሪ የሚፈጸሙ መሆኑን በመግለጽ፣ ተጠርጣሪው ቢወጡ አጠቃላይ የምርመራውን ሂደት ያደናቅፋሉ በሚል የተጠርጣሪ ጠበቆች ያቀረቡትን ዋስትናም ተቃውሞ ነበር።

ምንጭ፦ ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በዚምባብዌ የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ በተፈጠረ ተቃውሞ የአገሪቱ መከላከያ ሰራዊት የወሰደው እርምጃ ተመጣጣኝ እንዳልነበረ ጉዳዩን ሲያጣራ የቆየው አጣሪ ኮሚቴ ዛሬ ባወጣው ሪፖርት ይፋ አደረገ፡፡ በዝምባብዌ የተደረገውን ፕሬዘዳንታዊ ምርጫን ተከትሎ በዋና ከተማዋ ሀራሬ በምርጫ ውጤት ጋር ተያይዞ ግጭትና ብጥብጥ መነሳቱ ይታወሳል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ መንግስት የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት በሚል ባለፈዉ ዓመት የደነገገዉ #የምህረት_አዋጅ ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት ቀርተዉታል። የኢትዮጵያ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዛሬ እንዳስታወቀዉ አዋጁ የወጣዉ የዜጎችን ፖለቲካዊ ተሳትፎ ለማሳደግ ታስቦ ስለሆነ፤ አዋጁ ቀነገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት መጠቀም የሚፈልጉና የሚመለከታቸዉ ሰዎች ማመልከቻ እንዲያቀርቡ የጠቅላይ አቃቤ ሕግ ፅሕፈት ቤት አሳስቧል።

ምንጭ፦የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቤንሻንጉል ጉምዝ‼️

የመከላከያ ሰራዊት ዛሬ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተሽከርካሪ ላይ የደረሰውን #የፈንጅ_አደጋ ተከትሎ አካባቢውን #የማፅዳት ስራ እየሰራ ነው።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ #ጀይላን_ከበደ ዛሬ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከአሶሳ ወደ ቶንጎ ይጓዝ በነበረ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ላይ የደረሰውን የፈንጂ አደጋ በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም አደጋውን ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊት ስፍራውን በመቆጣጠር አካባቢውን የማጽዳት ስራ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ዳይሬክተሩ አያይዘውም በቀጣይ የፌደራል ፖሊስ ከአደጋው ጋር በተያያዘ ምርመራውን እንደሚያደርግም ነው የተናገሩት።

አደጋው ኮድ 3 በሆነ ተሽከርካሪ ላይ መፈጸሙን ጠቅሰው፥ በአደጋው ንጹሃን ዜጎች መሞታቸውን አንስተዋል።

አደጋው የደረሰበት አካባቢ በርካታ ታጣቂ ሃይሎች የሚንቀሳቀሱበት ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፥ የዛሬው አደጋም ለውጡን በማይቀበሉ ፀረ ሰላም ሃይሎች የተፈጸመ ነው ብለዋል።

የዛሬው አደጋ መንግስት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን ማንነት ለመለየት ጥረት እያደረገ ባለበት ሰዓት መፈጸሙንም አውስተዋል።

በአደጋው የሞቱ ዜጎች ማንነትም በቀጣይ በምርመራ እንደሚለይም የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

በቀጣይም ህብረተሰቡ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን በመለየትና መረጃዎችን በመስጠት የምርመራ ሂደቱን እንዲያግዝም ጥሪ አቅርበዋል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንም በአደጋው ህይዎታቸውን ባጡ ዜጎች የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ገልጿል።

በዛሬው እለት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከአሶሳ ወደ ቶንጎ ይጓዝ የነበረ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የፈንጂ አደጋ የአስር ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል።

አደጋው የደረሰው ዛሬ ጠዋት 14 ሰዎችን አሳፍሮ ከአሶሳ ወደ ቶንጎ ይጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ፥ ቤጊ መገንጠያ በተባለ ስፍራ ላይ በደረሰ የፈንጂ አደጋ ነው።

በአደጋው በተሸከርካሪው ተሳፍረው ከነበሩት ውስጥ የአስር ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፥ አራት ተሳፋሪዎች ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ቤጊ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት 41 ሺህ 693 የአሜሪካ ዶላር በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር ለማስወጣት የሞከሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ ግለሰቦቹ በዛሬው ዕለት #በቶጎ_ጫሌ መቆጣጠሪያ ጣቢያ መያዛቸዉን የጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ደመላሽ ተሾመ ተናግረዋል፡፡

Via~etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ብሄራዊ ምርጫ ቦርድን እንደገና ለማዋቀር የሚስችል ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቷል፡፡ ረቁቁን ያዘጋጀው የጠቅላይ አቃቤ ሕግ የሕግ እና የፍትህ አማካሪ ጉባዔ ጽሕፈት ቤት ሲሆን ዛሬ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ምሁራን እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ሲደረግበት ውሏል፡፡ ረቂቅ አዋጁ 36 አንቀጾች አሉት፡፡ የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ጥላሁን ተሾመ (ፕ/ር) የምክክሩ ዐላማ ጠቃሚ ግብዓቶችን መሰብሰብ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

Via~wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ዘርፍ በቴክኖሎጂ በመታገዝ የበለጠ ለማጎልበት የሚያስችል “IGude” የተሰኘ የኦንላይን ድረ-ገጽ ቴክኖሎጂ ይፋ ሆነ። ቴክኖሎጂው ኢንቨስተሮችን ለመሳብ ከፍተኛ ሚና የሚኖረው ሲሆን በኤሌክትሮኒክ ኢንቨስትመንት አገልግሎት የሚሰጠው ይህ የኢንተርኔት አገልግሎት የኢንቨስትመንት ዘርፉን የሚያስተዋውቅ እንደሆነ ተነግሯል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ‼️

የግቢው በር በመዘጋቱ ምክንያት በግቢው ውስጥ በቂ ምግብ ለማግኘት እንደተቸገሩ የተቋሙ ተማሪዎች ተናግረዋል። የሚመለከተው አካል አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርግም ጠይቀዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ታጋይ #መሳፍንት እና ከ250 በላይ የትግል አጋሮቹ ዳባት ከተማ ገቡ። በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የዳባት ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አንተነህ ደሴ ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት እንደገለጹት ታጋይ መሳፍንት እና አጋሮቹ ‹‹የአማራ መብት ይከበር›› በሚል ለነጻነት ሲታገሉ ቆይተዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽንን ለማቋቋም የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ፀደቀ፡፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽንን ለማቋቋም የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አፀደቀ፡፡ ረቂቅ አዋጁ በ33 ተቃውሞና በአራት ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ ነው የፀደቀው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አብዲ ኢሌ‼️

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የወንጀል በዛሬ ውሎው በቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት #አብዲ_መሀመድና በሳቸው መዝገብ በተከሰሱ ሌሎች ባለስልጠናት ላይ 14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።

መርማሪ ፖሊስ ከሀምሌ 26 አስከ 30 ቀን 2010 ዓ.ም በጂግጂጋ ከተማና ሌሎች አካባቢዎች በተከሰተው ሁከት 742 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን ከክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ባሰባሰበው መርጃ ማረጋገጡን ለችሎቱ አስርድቷል።

መርማሪ ፖሊስ ባለፉት 14 ቀናት ምርመራ ተገኝቷል ከተባለው የ200 ሰዎች የጅምላ መቃብር ጉዳይ ጋር በተያያዘ የ5 ሰዎችን የምስክር ቃል እንዲሁም፥ ከሁከትና ብጥብጡ ጋር በተያያዘ የሌሎች የአራት ሰዎች የምስክርነት ቃል መቀበሉን አስርድቷል።

ከጅምላ መቃብሩ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ተጨማሪ የምስክር ቃል ለመቀበልና የአስከሬን ምርመራ ውጤት የመቀበል ስራዎች እንደሚቀሩት የገለጸው መርማሪ ፖሊስ ከጉዳዩ ጋር በተያያዙ የምርመራ ስራዎቹ የ20 ሰዎችን የምስክር ቃል መቀበሉን አስረድቷል።

ከወንጀሉ ውስብሰብነት፣ ከሟቾች ቁጥር ብዛትና ከጉዳቱ ስፋን አንጻር ምርመራያን ባለማጠናቀቄም የተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ይፈቀድልኝ ሲል ፍርድቤቱን ጠይቋል።

የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ከዋሉ 116 ቀናት ማስቆጠራቸውን በመግለጽና ምርመራው አለመጠናቀቁ ተገቢ አይደለም፣ መርማሪ ፖሊስ በዚህ ጊዜ ውስጥ የምስክር ቃል ማሰባሰብና ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር የማዋል ተግባሩን ሊያጠናቀቅ ይገባው የነበረ ሲሆን፥ የተጠርጣሪዎችን የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት ህገ ምንግስታዊ መብት የሚጥስ ነው ብለዋል።

ግራና ቀኙን ያዳመጠው ፍርድ ቤቱ የምርመራ ስራው በአግባቡ እየተካሄደ መሆኑን በመግለጽ ጉዳዩ በርካታ ሰዎች የሞቱበትና ውስብስብ በመሆኑ መርማሪ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ በመቀበል ለታህሳስ 25 ቀን ተለዋጭ ቀጠሩ ሰጥቷል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኢትዮጵያ የሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ ዋሽንግተን በጠ/ሚር አብይ አህመድ ምርጫ ወቅት እጇን አስገብታለች መባሉን አስተባብሏል። ማስተባበያው የወጣው በቅርቡ የህወሀት መስራች ከሆኑት አንዱ አቶ #ስብሐት_ነጋ አምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶ ጠ/ሚር አብይ መሪ ሆነው እንዲመረጡ ጫና ፈጥረዋል ማለታቸውን ተከትሎ ነው።

Via~ENF
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮ ቴሌኮም ቅናሽ አደረገ‼️

ኢትዮ ቴሌኮም በዓለም አቀፍ ጥሪዎች እና የአጭር የፅሁፍ መልዕክት ዋጋ ላይ #ቅናሽ ማድረጉን ገለፀ። ኩባንያው ዛሬ በሰጠው መግለጫ በዓለም አቀፍ የድምፅ ጥሪዎች ላይ ከ10 እስከ 40 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን ነው ያመለከተው።

በተጨማሪም በዓለም አቀፍ በአጭር የፅሁፍ መልዕክት ላይ እስከ 51 በመቶ ቅናሽ አድርጓል።

በመግለጫው የዋጋ ቅናሹ በስድስት ዞኖች ተከፋፍሎ መደረጉም ተመልክቷል።

በዚህም መሰረት፦

በአፍሪካ- ቀደም ሲል በደቂቃ 10 ብር ከ29 ሳንቲም የነበረ ሲሆን፥ በቅናሹ 7 ብር ከ50 ሳንቲም፣

በእሲያና መካከለኛው ምስራቅ- በደቂቃ 8 ብር ከ63 ሳንቲም የነበረው 7 ብር ከ19 ሳንቲም፣

ሰሜን አሜሪካ- 8 ብር ከ63 ሳንቲም የነበረው 7 ብር ከ17 ሳንቲም፣

ደቡብ አሜሪካ- 10 ብር ከ29 ሳንቲም የነበረው 7 ብር ከ36 ሳንቲምና

ኦሺኒያ ደሴቶች- 23 ብር የነበረው 8 ብር ከ95 ሳንቲም ሆኖ ነው ቅናሽ የተደረገው።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በኦሮሚያ ክልሎች አጎራባች አካባቢዎችን የጸጥታ ችግር ለመፍታት #ኮማንድ_ፓስት ተቋቁሞ ወደ ስራ ገባ።
የኮማንድ ፖስቱ አባል አቶ ሰይፈዲን ሐሩን ፥ ኮማንድ ፖስቱ የፌደራል፣ የሁለቱ ክልሎች መንግሥታት፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊትና ፌዴራል ፖሊስ ያቀፈ ነው፡፡ኮማንድ ፖስቱ የተቋቋመው በክልሎቹ አጎራባች አካባቢዎች የመሸገውን የታጠቀ ኃይል በመቆጣጠር የኅብረተሰቡን #ደህንነት ለማስጠበቅ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

Via~fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የአድራሻ ለውጥ...

Addis Abeba city Infrastructure structure coordination and construction building Permit authority.
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክፍለ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ 120 የቀበሌ ቤቶችና 64 ሼዶች ለችግረኞች ተላለፉ። ከ200 በላይ የሚሆኑ የህብረተሰቡ ክፍሎችን በማሳተፍ የተገኙ ጥቆማዎች የማጥራት ስራ እንደተሰራ የክፍለ ከተማው የስራ ሀላፊዎች ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia