TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጥብቅ ማሳሰቢያ⬇️

"...ከምንም በላይ የግልና የቡድን ጥቅሞቻችሁን #ሰላማዊ በሆነ መንገድ ማስጠበቅ እየቻላችሁ በተለያዩ ወንጀሎችና ሰላምን የማደፍረስ #እኩይ ተግባራት ላይ ለመሰማራት #የምታስቡ አካላት ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ እያሳሰብኩ በማንኛውም የህዝብን ፀጥታ #በሚያደፈርሱና ህዝብን ከህዝብ #በሚያጋጩ ህገወጥ ተግባራት ላይ ተሰማርቶ የተገኘ እንዲሁም ለእንደዚህ አይነት ህገወጥ ተግባራት በምንም መልኩ ትብብር ያደረገ አካል ላይ ህግን ተከትሎ አስፈላጊውን #እርምጃ ለመውሰድ መንግስት #ቁርጠኛ እንደሆነ በጥብቅ ለማሳወቅ እወዳለሁ፡፡"

◾️◾️ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ◾️◾️

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በድጋሚ...#ጥብቅ ማሳሰቢያ⬇️

"...ከምንም በላይ የግልና የቡድን ጥቅሞቻችሁን #ሰላማዊ በሆነ መንገድ ማስጠበቅ እየቻላችሁ በተለያዩ ወንጀሎችና ሰላምን የማደፍረስ #እኩይ ተግባራት ላይ ለመሰማራት #የምታስቡ አካላት ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ እያሳሰብኩ በማንኛውም የህዝብን ፀጥታ #በሚያደፈርሱና ህዝብን ከህዝብ #በሚያጋጩ ህገወጥ ተግባራት ላይ ተሰማርቶ የተገኘ እንዲሁም ለእንደዚህ አይነት ህገወጥ ተግባራት በምንም መልኩ ትብብር ያደረገ አካል ላይ ህግን ተከትሎ አስፈላጊውን #እርምጃ ለመውሰድ መንግስት #ቁርጠኛ እንደሆነ በጥብቅ ለማሳወቅ እወዳለሁ፡፡"

◾️◾️ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ◾️◾️

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ‼️

ጥር 17 አፄ #ቴዎድሮስ_ግቢ በ6 የተማሪ መኖሪያ ህንፃዎች በተደረገ #ድንገተኛ ፍተሻ፦

•395 ያልታደሰ፣ ሃሰተኛ እና ፎቶ የሌለው መታወቂያ ተይዟል።

•ከተማሪ መኖሪያ ክፍሎች ጩቤ፣ ድንጋይ፣ ብረት እና ዱላ ተገኝቷል።

•አንድ ተማሪ 9 ሲም ካርድ፤ ሌላ አንድ ተማሪ 7 ሲም ካርድ ይዘው ተገኝተዋል።

•8 ተማሪዎች አካውንት ላይ እያንዳንዳቸው ከ30 ሺ ብር እስከ 86 ሺ ብር ተገኝቷል።

•መታወቂያ ያልያዙ 37 ተማሪዎች ተይዘዋል።

•በቀን ጥር 16/2011 ዓ.ም. 3 ተማሪዎች 4 ጀሪካን ዘይት ጫካ ውስጥ ይዘው እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል፤ 3 ተማሪዎች ሴቶች ህንፃ ሲገቡ ተይዘዋል።

🔹ተጠርጣሪዎች ላይ ተገቢው ማጣራት እየተደረገ ይገኛል፤ በቅርቡ #እርምጃ ተወስዶ #ይፋ ይደረጋል ተብሏል።
.
.
ትምህርት የተቋረጠባቸው አፄ ቴዎድሮስ እና አፄ ፋሲል ግቢዎች ከሰኞ ጥር 20 ጀምሮ ተማሪዎች ትምህርት እንዲጀምሩ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል። ትምህርት የማይጀምሩ ተማሪዎች ግቢውን #ለቀው እንዲወጡ #ጥብቅ_ማሳሰቢያ ተላልፏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥብቅ ማሳሰቢያ‼️

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር #በነገው ዕለት ምንም ዓይነት የሠላማዊ ሰልፍ ሆነ ስብሰባ እናድርግ የሚል #ጥያቄ አልቀረበለትም።

በመሆኑን በማህበራዊ ሚዲያ ተጠራ የተባለው ሰልፍ በከተማ አስተዳደሩ ይሁን በፖሊስ ኮሚሽኑ እውቅና የሌለው ነው።

ስለሆነም #ሰልፍ_እንወጣለን በሚል በህብረተሰቡ ላይ የፀጥታ ችግር ለመፍጠር የሚፈልጉ አካላት ከተግባራቸው እንዲታቀቡ ኮሚሽኑ #ጥብቅ_ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

ይህን ተላልፎ በሚገኙ አካላት ላይም የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል አስፈላጊውን ህጋዊ #እርምጃ_የሚወስድ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ATTENTION

በኳታር ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን!

(የኢትዮጵያ ኤምባሲ - ዶሃ)

- በኳታር የፊት መሸፈኛ መጠቀም አስገዳጅ ህግ ሆኗል።

- የአገሪቱ የሚኒስትሮች ም/ቤት ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ማንኛውም ሰው በተለያየ ምክንያት ከመኖሪያ ቤቱ ሲወጣ የፊት መሸፈኛ መጠቀም ይኖርበታል።

- ውሳኔው ከፊታችን እሁድ ግንቦት 09 ቀን 2012 ዓ.ም /Sunday May 17/2020/ ጀምሮ የጸና ይሆናል።

- ህጉ ብቻውን ሆኖ መኪና የሚያሽከረክር ግለሰብን አይመለከትም።

- ህጉን ተላልፎ የሚገኝ ግለሰብ እስከ ሶስት ዓመት እስር ወይም እስከ 200,000 የኳታር ሪያል ይቀጣል።

በኳታር የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን የሀገሪቱ መንግስት የሚያወጣቸውን ህጎች በአግባቡ በመተግበር ራሳችሁንና ቤተሰባችሁን ከበሽታው እንድትጠብቁ ብሎም ከህግ ተጠያቂነት ነጻ እንድትሆኑ #ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ጥብቅ_ማሳሰቢያ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሀገሪቱ አሁን ባለችበት የፀጥታ ሁኔታ በምንም አይነት ምክንያት "ርችት መተኮስ" የተከለከለ መሆኑን በጥብቅ አሳስቧል።

ይህን መልዕክት በመተላለፍ ርችት ሲተኩስ የተገኘ ግለሰብ በህግ የሚጠየቅ መሆኑን አስታውቋል።

@tikvahethhiopiaBot @tikvahethiopia
#ጥብቅ_ማሳሰቢያ

በመስቀል በዓልም ሆነ በልዩ ልዩ ምክንያቶች ርችት መተኮስ በጥብቅ መከልከሉን የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ አሳውቋል።

ከዚህ ቀደም ፖሊስ ያስተላለፈውን መልዕክት በመተላለፍ ርችት የተኮሱ ግለሰቦች ተይዘው በፍርድ ቤት በዋስ መለቀቃቸውን ፖሊስ ገልጿል፡፡

ጳጉሜ 5/2013 ዓ/ም ለመስከረም 1/2014 ዓ.ም አጥቢያ ከሌሊቱ 11 ሰዓት በአዲስ ከተማ ክ/ ከተማ ልዩ ቦታው ሩፋኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ ሦስት ግለሰቦች የ2014 አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ርችት ሲተኩሱ ተይዘው ምርመራ ተጣርቶባቸው እያንዳንዳቸው በ4ሺ ብር ዋስ ተለቀው ጉዳይቸው በፍርድ ቤት በመታየት ላይ የሚገኝ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውሷል፡፡

በተመሳሳይ በቦሌ ፣ በቂርቆስ እና በየካ ክፍለ ከተሞች ርችት ሲተኩሱ የተገኙ ግለሰቦች ጉዳይም በምርመራ ሂደት ላይ እንደሚኝም ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል፡፡

በበዓላት ወቅት የሚተኮሱ ርችቶችን ሽፋን በማድረግ ሰላምን የማደፍረስ ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች የሚፈነዱና ተቀጣጣይ ነገሮችን ሊጠቀሙ ስለሚችሉ ይህ ደግሞ የፀጥታ ስጋቶችን እንደሚፈጥሩ ፖሊስ አስገንዝቧል።

ፖሊስ የህገ-ወጦቹን ድርጊት ለመከላከል እንዲቻል መስከረም 16 ቀን 2014 ዓ/ም በሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓልም ሆነ በልዩ ልዩ ምክንያቶች ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ተቋም ከሚመለከተው አካል ፍቃድ ሳያገኝ ርችቶችን መተኮስ እንደማይችል ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ተገቢውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፤ የዲጂታል ባንክ አግልግሎት ሙሉ በሙሉ መጀመሩን ገለጸ። ባንኩ ፤ በሲስተም ችግር ምክንያት ፦ - በቅርንጫፎች፥ - በኢንተርኔት ባንኪንግ፥ - በሞባይል ባንኪንግ፥ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሞ እንደነበር አስውሷል። በቅርንጫፍ እና በኤቲኤም የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀደም ብለው መጀመራቸውን ገልጾ አሁን ደግሞ በዲጂታል የሚሰጡ የባንክ አገልግሎቶች…
#Update #CBE #NBE

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ትላንት ባጋጠመው ችግር የደንበኞች መጉላላትን ጨምሮ የደረሱ #ጉዳቶች ስለመኖራቸው ተነግሯል።

ጉዳቶቹ ምርመራ ተደርጎ ወደፊት ለህብረተሰቡ ይገለጻሉ ነው የተባለው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መጋቢት 7 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንክ  ስርዓት ላይ ያጋጠመውን ችግርና የአገልግሎት መቋረጥ በተመለከተ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል።

" ባንኮች በሥርዓቶቻቸዉ ላይ በየጊዜዉ የደህንነት ፍተሻ እንዲሁም የማሻሻያ ሥራዎችን ያከናዉናሉ " ያለው ብሔራዊ ባንክ ፤ " በሥርዓቶቹ ላይ በሚከናወን ለዉጦችና ፍተሻዎች የባንኮች አገልግሎት አልፎ አልፎ ሊቋረጥ ይችላል " ብሏል።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በትናንትና ዕለት የተከሰተዉ የአገልግሎት መቋረጥ ከዚሁ ጋር የተያያዘ መሆኑን #አረጋግጫለሁ ሲል ገልጿል።

ችግሩ ከተከሰተበት ሰዓት አንስቶ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የባንኩን እና የደንበኞቹን ደህንነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ ክትትል ሲያደርግ እንደቆየና በተደረገው ርብርብ አገልግሎቶች እንዲመለሱ መደረጉን ጠቁሟል።

ብሔራዊ ባንክ በዚሁ መግለጫ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባጋጠመው ችግር #ጉዳቶች እንደደረሱ ጠቁሟል።

ስለ ጉዳቶቹ በዝርዝር ያለው ነገር ባይኖርም አስፈላጊው ምርመራ ተደርጎ ወደፊት ለህዝብ ይገለጻል ብሏል።

በተፈጠረው ችግር የደንበኞች መጉላላትም መከሰቱን አመላክቷል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በፋይናንስ ተቋማት ላይ በየጊዜዉ ክትትልና ቁጥጥር እንደሚያደርግ አመልክቶ በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ያሉ በሁሉም የፋይናንስ ተቋማት የሚገኙ የፋይናንስ ሥርዓቶች ደህንነቸዉ የተጠበቀ ነው ብሏል።

" ህብረተሰቡ ያለምንም ስጋት የፋይናንስ አገልግሎቶችን መጠቀም መቀጠል ይችላል " ሲል አሳውቋል።

የፋይናንስ ተቋማትም የሥርዓቶቻቸዉን ደህንነትና ቀልጣፋነት ይበልጥ ለማሳደግ የቴክኖሎጂ ተለዋዋጭ ባህርይ በማየት በቀጣይነት መሥራት እንደሚኖርባቸዉ #ጥብቅ_ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

@tikvahethiopia