TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ድንገተኛ የእሳት አደጋ በጅማ‼️

በጅማ ከተማ የተነሳ #ድንገተኛ የእሳት ቃጠሎ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን የጅማ ከተማ ወረዳ አንድ ፖሊስ ጽህፍት ቤት አስታወቀ።

ንብረትነቱ የሦስት ሰዎች የሆነ አንድ ህንጻ መሳሪያ መሸጫ ሱቅ በእሳቱ ሙሉ ለሙሉ ቢወድምም ወደሌላ ከመዛመቱ በፊት በቁጥጥር ስር መዋሉን በጽህፍት ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ምክትል ሳጅን ሀዊ አልይ ለኢዜአ ተናግረዋል።

እንደምክትል ሳጅን ሀዊ ገለጻ የእሳት ቃጠሎው የተከሰተው ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ በሚካሄድበትና በተለምዶ “አረቦች ተራ” እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

የእሳት ቃጠሎው የተከሰተው ከትላንት በስቲያ ሌሊት 8፡00 አካባቢ ሲሆን ህብረተሰቡና የከተማው የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከያ ጽህፈት ቤት እሳቱን ለማጥፋት ባደረጉት ርብርብ ከሌሊቱ 10፡00 ሰዓት አካባቢ እሳቱን በቁጥጥር ስር ለማዋል ተችሏል፡፡

ምክንያቱ ለጊዜው ባልተወቀ ምክንያት በተከሰተው የእሳት አደጋ 2 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ንብረት መውደሙን ተናግረዋል፡፡

ሳጂን ሀዋ እንዳሉት እሳት በተነሳበት አካባቢ በርካታ ሱቆች የሚገኙ ቢሆንም እሳቱን ለመቆጣጠር ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ በተደረገ ርብርብ እሳቱ ወደሌሎች ሱቆች ሳይዘመት በቁጥጥር ስር ለማዋል ተችሏል፡፡

ፖሊስ በአሁኑ ወቅት የአደጋውን መንስኤ በማጣራት ላይ እንደሚገኝም የገለጹት ምክትል ሳጂን ሀዊ ህብረተሰቡ በእዚህ በኩልም ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በእሳት አደጋው ንብረታቸው ከወደመባቸው ሦስት ሰዎች መካከል አቶ አብዱራህማን ከማል በእሳት ቃጠሎው ንብረታቸው ሙሉ ለሙሉ መውደሙንና በእዚህም ሀዝን እንደተሰማቸው ገልጸዋል።

“ሌሊት 10፡15 አካባቢ በቦታው ስደርስ የእሳት አደጋ መከላከያ አባላት ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን እሳቱን ሲያጠፉና ወደሌላ ሱቅ እንዳይዛመት ጥረት ሲያደርጉ ተምልክቻለሁ” ብለዋል፡፡

“እኔ ሱቄን ዘግቼ ወደ ቤቴ የሂድኩት ምሽት 12፡00 ሰዓት አከባቢ ነው፤ በወቅቱ መብራት እንዳጠፋሁም አስታውሳለሁ” ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ምንጭ፦ ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ ጆቦ ቀበሌ በተሽከርካሪ ላይ ትላንት በተደረገ #ድንገተኛ_ፍተሻ 90ሺህ የአሜሪካ ዶላር መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር አስቻለው ዓለሙ እንደገለጹት ዶላሩ የተያዘው ከአዲስ አበባ ወደ አዳማ ሲጓዝ በነበረ የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3- 5124 ኦሮ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ውስጥ ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ‼️

ጥር 17 አፄ #ቴዎድሮስ_ግቢ በ6 የተማሪ መኖሪያ ህንፃዎች በተደረገ #ድንገተኛ ፍተሻ፦

•395 ያልታደሰ፣ ሃሰተኛ እና ፎቶ የሌለው መታወቂያ ተይዟል።

•ከተማሪ መኖሪያ ክፍሎች ጩቤ፣ ድንጋይ፣ ብረት እና ዱላ ተገኝቷል።

•አንድ ተማሪ 9 ሲም ካርድ፤ ሌላ አንድ ተማሪ 7 ሲም ካርድ ይዘው ተገኝተዋል።

•8 ተማሪዎች አካውንት ላይ እያንዳንዳቸው ከ30 ሺ ብር እስከ 86 ሺ ብር ተገኝቷል።

•መታወቂያ ያልያዙ 37 ተማሪዎች ተይዘዋል።

•በቀን ጥር 16/2011 ዓ.ም. 3 ተማሪዎች 4 ጀሪካን ዘይት ጫካ ውስጥ ይዘው እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል፤ 3 ተማሪዎች ሴቶች ህንፃ ሲገቡ ተይዘዋል።

🔹ተጠርጣሪዎች ላይ ተገቢው ማጣራት እየተደረገ ይገኛል፤ በቅርቡ #እርምጃ ተወስዶ #ይፋ ይደረጋል ተብሏል።
.
.
ትምህርት የተቋረጠባቸው አፄ ቴዎድሮስ እና አፄ ፋሲል ግቢዎች ከሰኞ ጥር 20 ጀምሮ ተማሪዎች ትምህርት እንዲጀምሩ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል። ትምህርት የማይጀምሩ ተማሪዎች ግቢውን #ለቀው እንዲወጡ #ጥብቅ_ማሳሰቢያ ተላልፏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር የሴፍቲና ሲኬዩሪቲ ዲፓርትመንት ባለሙያዎች በባቡሩ ላይ #ድንገተኛ የእሳት አደጋ ቢከሰት እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል የሚያሳይ ልምምድ አካሄዱ። በልምምዱ የእሳት አደጋ ተከላካይ ሰራተኞችና የፖሊስ አባላት ተሳትፈዋል።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 21/2011 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ መንግስት “የጤፍ ባለቤት ነኝ” ያለውን የሆላንድ ድርጀት በዓለም አቀፉ የግልግል ፍርድ ቤት ሊከስ ነው።
.
.
በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ ሁለት አርሶ አደሮች በኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር "ኦነግ ታጣቂዎች" መገደላቸውንና አንድ አርሶ አደር መቁሰሉን የአከባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
.
.
በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር የሴፍቲና ሲኬዩሪቲ ዲፓርትመንት ባለሙያዎች በባቡሩ ላይ #ድንገተኛ የእሳት አደጋ ቢከሰት እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል የሚያሳይ ልምምድ አካሂደዋል።
.
.
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት የቀጠለውን የሚኒስትርና ተጠሪ መስሪያ ቤቶችን የ100 ቀን እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መርተዋል።
.
.
የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፓሬሽን/ሜቴክ/ይቅርታ መጠየቅና #እርቅ ማውረድ ካለበት አካል ጋር ሁሉ እንደሚያደርግ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀነራል #አህመድ_ሀምዛ አስታውቀዋል።
.
.
በሰቆጣ ከተማ ሦስት #ፓኪስታናውያን በሕገ ወጥ የሞባይል ሽያጭ ተሰማርተው እጅ ከፈንጅ ተይዘዋል።
.
.
በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ሰርተፍኬት፣ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ፣ የልደትና ሞት ሰርተፍኬት እንዲሁም የጋብቻ እና ፍቺ ሰርተፍኬቶች በዲጂታል ሰርተፍኬት ሊቀየሩ ነው ተብሏል።
.
.
ኢ/ር #ታከለ_ኡማ ቦሌ አራብሳ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የፈረሰውን መስጂድ በመጎብኘት የአከባቢውን የሙስሊም ማህበረሰብም አነጋግረዋል፡፡
.
.
#የፌዴራል_መንግሥት አመራሮች የድሬዳዋ ነዋሪዎችን በከተማዋ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ አወያይተዋል፡፡
.
.
በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና በማህበራዊ ፍትህ ላይ ያተኮረ የመጀመሪያውን አረንጓዴ የፖለቲካ ፓርቲ (Green Party) ለማቋቋም ጊዜያዊ አስተባባሪ ፓርቲ መሰየሙን ዋዜማ ራድዮ ዘግቧል።
.
.
ከሳውዲ አረቢያ ጋር በተደረገው የሁለትዮሽ ስምምነት መሰረት በህጋዊ መንገድ ለሚሄዱ ሰራተኞች የቪዛ አገልግሎት መሰጠት መጀመሩን የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል።
.
.
ግምታዊ ዋጋው 400 ሺህ ብር የሚያወጣ የባህርዛፍ አጠና ያለምንም ህጋዊ ሰነድ ከአገር ሊወጣ ሲል #በጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።
.
.
ከጥር 19 እስከ 21 ለተከታታይ ሦስት ቀናት #በሀዋሳ_ከተማ ሲካሄድ የቆየው የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ 4ኛ ድርጅታዊ ጉባዔውን ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበሩን በመምረጥ ተጠናቋል።
.
.
ከጭናግሰን ከተማ የማርያምን ክብረ በዐል አክብረው ይመለሱ በነበሩ ምዕመናን ላይ ወጣቶች መንገድ መዝጋታቸውን ተከትሎ #በጅግጅጋ_ከተማ ተፈጥሮ የነበረው ግጭት መረጋጋቱ ታውቋል። በግጭቱ የ2 ሰው ህይወት አልፏል።
.
.
ቀዳማዊት እመቤት #ዝናሽ_ታያቸው የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ለተከታተሉበት የጎንደሩ ጻዲቁ ዮሐንስ 1ኛ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤት የኮምፒዩተር ድጋፍ አድርገዋል፡፡
.
.
#በድሬዳዋ_ከተማ የትራንስፖርትና የግብይት #አድማ ለማድረግ ያቀዱ ነዋሪዎች ከድርጊታቸው ይቆጠቡ ዘንድ #የምስራቅ_ዕዝ_ጠቅላይ_መምሪያ አስጠነቅቋል።
.
.
አቃቤ ሕግ የቀድሞ #የሜቴክ የስራ #ሀላፊዎች በነበሩት ሻለቃ #ክንደያ_ግርማይና ሌተናል ኮሎኔል #አሰፋ_ዮሐንስ ላይ ክስ መስርቷል።
.
.
የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) በዚህ ሳምንት ሐሙስ በይፋ ትጥቅ ይፈታል።
.
.
በቅርቡ በመንግስት እና ኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) መካከል በአምቦ በተደረገው ስምምነት መሠረት እርቁን ተግባራዊ ለማድረግ የተመረጠው የቴክኒክ ኮሚቴ ሥራውን በተግባር መጀመሩን የቴክኒክ ኮሚቴው አባል አቶ #ጀዋር_መሀመድ አስታውቀዋል።
.
.
ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ #ዝናሽ_ታያቸው ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የህክምናና የኢንፎርሜሸን ቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልና ለሁለት ትምህርት ቤቶች ድጋፍ አድርገዋል።
.
.
#የኢፌዲሪ_አየር_ሃይል በሶማሊያ ከባይደዋ በስተምስራቅ 75 ኪሎ ሜትር ላይ ቡርሃይቤ በተባለ የአልሻባብ ይዞታ ላይ ጥር 16 ቀን 2ዐ11 ዓ.ም ድብደባ በመፈፀም ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረሱን የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
.
.
ሰሞኑን በድሬዳዋ ከተማ የተከሰተዉን #አለመረጋጋት ተከትሎ የከተማዉ ፖሊስ ኮሚሽን 308 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አዉሎ ምርመራ እያካሄደ ነዉ፡፡

ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ፣ etv፣ fbc፣ VOA፣ ኢዜአ፣ ኢ.ፕ.ድ፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት፣ የጠ/ሚ ፅ/ቤት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ አብመድ
.
.
ሰላም እደሩ!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢ/ር ታከለ ኡማ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አስተዳደር #ድንገተኛ የስራ ምልከታ አደረጉ፡፡ ኢ/ር ታከለ ኡማ በክ/ከተማው ስር ባሉ ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን የጎበኙ ሲሆን ከተጠቃሚዎች፣ ከክ/ከተማው አመራሮች እና ሰራተኞች ጋርም ተነጋግረዋል፡፡

Via @MayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የአሚር ኑር ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት በአረፋ በአል ዋዜማ በተደረጉ #ድንገተኛ ፍተሻዎች ልዩ ስሙ #ዱክበር በተባለ አካባቢ አንድ የቱርክ ስሪት EKOL.P29 #ሽጉጥ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ከወረዳው ፖሊስ ያገኝነው መረጃ ያመለክታል።

Via AD/#TIKVAH_ETH

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Monkeypox (Europe) የዝንጀሮ ፈንጣጣ በአውሮፓ ሀገራት እጅግ በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ ነው ተብሏል። የዓለም ጤና ድርጅት የአውሮፓ ኃላፊ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሶስት እጥፍ መጨመሩን አሳውቀዋል። እንደ አሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (CDC) መረጃ እስካሁን በዓለም ደረጃ ከ5,000 የሚበልጡ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ኬዞች ከ51 ሀገራት ሪፖርት የተደረጉ…
#Monkeypox

(Africa)

የአፍሪካ የጤና ባለስልጣናት በአህጉሪቱ ውስጥ የዝንጀሮ ፈንጣጣ እየተስፋፋ መምጣቱን በመጠቆም እንደ #ድንገተኛ ሁናቴ እያስተናገዱት መሆኑን ገልፀዋል።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት የሚታዩትን የፍትሃዊነት ችግሮች ለማስወገድ የበለፀጉ ሀገራት ውስን የክትባት አቅርቦቶችን እንዲያካፍሉም ጠይቀዋል።

እስካሁን ባለው በአፍሪካ 1,800 የሚጠጉ የዝንጀሮ ፈንጣጣ የተጠረጠሩ ኬዞች ያሉ ሲሆን ከ70 በላይ ሰዎች እንደሞቱ ተነግሯል ፤ ነገር ግን በላብራቶሪ ምርመራ የተረጋገጠው 109 ኬዝ ብቻ ነው ተብሏል።

ለበሽታው ምርመራ የሚያስፈልጉ የላብራቶሪ ምርመራ ገብአቶች እጦት እና ደካማ የሆነ የክትትል ስርዓት ብዙ ኬዞች ሳይታወቁ እንዲቀሩ እያደረገ እንደሆነ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በተለምዶ ሰይጣን ቤት ወይም ፒራሚድ አዲስ እና ባስ አዲስ ክለብ ታሸጉ ፤ 68 ሰዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስነዋሪ ድርጊት እና ትውልድን በሚጎዳ ስራ ላይ የተሰማሩና ሲጠቀሙ የተገኙ 68 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማው አስተዳደር አሳውቋል።

ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በተደረገ #ድንገተኛ_ፍተሻ በተለምዶ #ሰይጣን_ቤት ወይም #ፒራሚድ_አዲስ እና #ባስ_አዲስ_ክለብ በማህበረሰቡ ተቀባይነት የሌላቸው አፀያፊ ድርጊቶች ሌሎች ህገወጥ ተግባራት ሲፈፅሙ በመገኘታቸው ቤቶቹ መታቸጋቸው ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ እና የሠላምና ፀጥታ ቢሮ በጋራ በመሆን ትላንት ከምሽቱ 4:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት ባደረጉት ድንገተኛ ፍተሻ ነው ህገወጥ ተግባራት ሲፈጸምባቸው የተገኙት የምሽት ቤቶች እንዲታሸጉ የተደረገው።

በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ ፦

- ከ100 በላይ የሺሻ ዕቃዎች ፣
- በርካታ መዋሰሎች፣
- ከ6 በላይ ሀሺሽ የያዙ እቃዎች እንዲሁም በወቅቱ በቦታው የነበሩ ከ68 በላይ የሚሆኑ ተጠቃሚዎችን እና ወጣቱን በዚህ እኩይ ድርጊት ላይ እንዲሳተፍ ሲያደርጉ የቆዩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማው አስተዳደር ገልጿል።

ነዋሪዎች በየአከባቢያቸው አዋኪና ከማህበረሰቡ ወግና ባሕል ያፈነገጡ አስነዋሪ ድርጊቶች ላይ ወጣቱ እንዲሳተፍ የሚያደርጉ ምሽት ቤቶችንና ግለሰቦችን በማጋለጥ ሀላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

#MayorOfficeofAddisAbaba

@tikvahethiopia
#ICS

የሕዝብ ተ/ም/ቤት የሕግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ፤ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎትን የ9 ወር አፈጻጸም ትላንት ገምግሟል።

ኮሚቴው ከዚህ ግምገማ በፊት ማለትም ሚያዚያ 3/2016 ላይ #ድንገተኛ ምልከታ አድርጎ ነበር።

ቋሚ ኮሚቴው ምን አለ ?

- ምንም እንኳ የተጀመሩ ሥራዎች ጥሩና ተስፋ ሰጪ ቢሆኑም በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ችግሮችን እና የተገልጋይን ቅሬታ መፍታት አልተቻለም።

- ተገልጋዮች አገልግሎት ለማግኘት ብለው በሚደርስባቸው እንግልትና ስቃይ ምክንያት በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከፍተኛ ቅሬታ እንደሚያቀርቡ በድንገተኛ ምልከታ መመልከት ተችሏል።

- በዋና መ/ ቤቱ ተገልጋይ በተቋሙ ሠራተኞች ፦
➡️ #መሰደብ
➡️ #መመናጨቅ
➡️ #መገፍተር_ጭምር የሚደርስበት በመሆኑ ተገልጋይ በሥነ ምግባር መስተናገድ አለበት።

- በአዲስ አበባ " ካሳንቺስ አካባቢ " የሚገኘዉ የውጪ ዜጎች አገልግሎት ተቋም የሚሰጠው አገልግሎት ኢትዮጵያን የማይመጥን፣ ምቹ ያልሆነ እና የንጽህና ጉድለት ያለው ነው። ይህ መታረም አለበት።

- ዋናው መስሪያ ቤት ለአገልግሎት ምቹ ያልሆነ፣ ሕንፃው የቆየ እና አስፈላጊዉን የማሻሻያ ጥገና ያላገኘ ነው። ሕንፃው ከተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ባህሪ ጋር የማይጣጣም ስሪት ያለው ነው።

- በዋና መስሪያ ቤት ያለው መጨናነቅ እንዲቀንስ በአዲስ አበባ ከተማ ከአምስት ያላነሱ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች እንዲከፈቱ የመፍትሔ ሃሳብ ቢሰጥም አልተፈጸመም። በተለይ በአዲስ አበባ ቅርንጫፍ የማስፋፋት ሥራዎች መሠራት አለበት።

- የደላላ ሰንሰለት በመለየት ማቋረጥ ያስፈልጋል።

- አሁንም ከደላሎች ጋር የሚመሳጠሩ የተቋሙ #ሠራተኞች በመኖራቸው ትኩረት ሰጥቶ መሥራት አለበት።

- የሠራተኛ ባጅ አለመኖሩም ሊታሰብበት ይገባል።

በምክር ቤቱ የተገኙት የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ለተነሱት ጉዳዮች ምላሽ ሰጥተዋል።

ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/EPA-04-27-2 #EPA

@tikvahethiopia