ሰበር ዜና‼️
የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች የነበሩት አቶ #መዓሾ_ኪዳኔ_ዓለሙ እና አቶ #ሀዱሽ_ካሳ_ደስታ በቁጥጥር ስር ዋሉ። ከፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው ግለሰቦቹ በከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል ተጠርጥረው ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።
ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች የነበሩት አቶ #መዓሾ_ኪዳኔ_ዓለሙ እና አቶ #ሀዱሽ_ካሳ_ደስታ በቁጥጥር ስር ዋሉ። ከፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው ግለሰቦቹ በከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል ተጠርጥረው ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።
ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች የነበሩት አቶ #መዓሾ_ኪዳኔ እና አቶ #ሀዱሽ_ካሳ ዛሬ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10 የወንጀል ችሎት ቀርበዋል።
ተጨማሪውን፦ https://telegra.ph/በከፍተኛ-የሰብዓዊ-መብት-ጥሰት-ወንጀል-የተጠረጠሩት-አቶ-መዓሾ-ኪዳኔና-አቶ-ሀዱሽ-ካሳ-ዛሬ-ፍርድ-ቤት-ቀረቡ-12-10
ተጨማሪውን፦ https://telegra.ph/በከፍተኛ-የሰብዓዊ-መብት-ጥሰት-ወንጀል-የተጠረጠሩት-አቶ-መዓሾ-ኪዳኔና-አቶ-ሀዱሽ-ካሳ-ዛሬ-ፍርድ-ቤት-ቀረቡ-12-10
Telegraph
በከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል የተጠረጠሩት አቶ መዓሾ ኪዳኔና አቶ ሀዱሽ ካሳ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች የነበሩት አቶ መዓሾ ኪዳኔ እና አቶ ሀዱሽ ካሳ ዛሬ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10 የወንጀል ችሎት ቀርበዋል። በፍርድ ቤቱ በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከፍተኛ አመራር ናቸው የተባሉት አቶ መዓሾ ኪዳኔና አቶ ሃዱሽ ካሳ፥ ጠበቃ ለማቆም አቅም የለንም ማለታቸውን ተከትሎ መንግስት…
#Update የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች የነበሩት አቶ መዓሾ ኪዳኔ ዓለሙ እና አቶ #ሀዱሽ ካሳ ደስታ ላይ ፍርድ ቤቱ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቀደ። ትላንት በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ጉዳያቸው የታየው በሰብዓዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩት አቶ መዓሾ እና አቶ ሀዱሽ ላይ ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ ፖሊስ ጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸዋል። ተጠርጣሪዎቹ ትናንት ፍርድ ቤት በቀረቡበት ወቅት በግላቸው ጠበቃ አቁመው ለመከራከር አቅም የሌላቸው መሆኑን ገልጸው መንግስት ጠበቃ እንዲያቆምላቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል። ፖሊስ በበኩሉ ተጠርጣሪዎቹ በቂ ሃብትና ንብረት ያላቸው በመሆኑ በግል ጠበቃ አቁመው መከራከር እንዳለባቸው ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል። በመሆኑም ለምርመራ የተሰጠው የጊዜ ቀጠሮ ከመድረሱ በፊት የተጠርጣሪዎቹን ሀብት ንብረት የሚያሳይ ማስረጃ ለታህሳስ 8 ቀን 2011 ዓ.ም ፖሊስ እንዲያቀርብ ታዟል። የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች የነበሩት አቶ መዓሾ እና አቶ ሀዱሽ በከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ባለፈው ቅዳሜ ህዳር 29 ቀን 2011 ዓ.ም መሆኑ ይታወሳል።
ምንጭ፦ ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia