TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
61.7K photos
1.56K videos
216 files
4.28K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AI

በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰሩ የታዳጊ ሴቶች የእርቃን ምስሎች ስፔን ውስጥ ከፍተኛ ድንጋጤ የፈጠሩ ሲሆን ፖሊስ ምርመራ ላይ ነው።

በደቡባዊ ስፔን ውስጥ የምትገኘው አልመንድራሌሆ ከተማ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰሩ የታዳጊ ሴቶች እርቃን ምስሎች ከእነርሱ እውቅና ውጭ በማኅበራዊ ሚዲያ ከተዘዋወሩ በኋላ ድንጋጤ ውስጥ ገብታለች ሲል ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

እርቃን ምስሎቹ የተሰሩት ሙሉ ልብስ ለብሰው የተነሱትን የታዳጊዎቹን ፎቶ በመጠቀም ነው።

በርካታ ምስሎቹ የተወሰዱትም ከታዳጊዎቹ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች ነው።

ምስሎቹ ከተወሰዱ በኋላም አንድ ግለሰብ እርቃኑን ምን እንደሚመስል የሚያሳይ ምናባዊ ምስል የሚፈጥር መተግበሪያ በመጠቀም የታዳጊዎቹ ምስል እርቃን እንዲቀር ተደርጓል።

እስካሁን ዕድሜያቸው በ11 እና በ17 ዓመት መካከል የሚገኙ 20 ታዳጊ ሴቶች፣ የዚህ ድርጊት ሰለባ መሆናቸውን በመግለጽ በደቡብ ምዕራብ ግዛቷ ባዳጆዝ ውስጥ በምትገኘው አልመንድራሌሆ ከተማ እና አቅራቢያው ሪፖርት አድርገዋል።

በማኅበራዊ ሚዲያ የተጋሩት ሐሰተኛ የእርቃን ምስሎች በታዳጊ ሴቶቹ ላይ የተለያዩ ተፅዕኖዎችን አሳድረዋል።

የተወሰኑ ታዳጊዎች ከቤታቸው ለመውጣት እንደተሳቀቁ ተነግሯል።

ይህ ጉዳይ ወደ አደባባይ የወጣው ከታዳጊዎቹ ሴቶች መካከል የአንዷ እናት በሆነችው የማሕጸን ሐኪም ማሪያም አል አዲብ ምክንያት ነው።

አዲብ ማኅበራዊ ሚዲያዋን በመጠቀም ባወጣችው መልዕክት ምክንያት ጉዳዩ የስፔን ሕዝብ መነጋጋሪያ መሆን ችሏል።

አዲብ ታዳጊ ሴቶችንና ወላጆችን ለማረጋጋት ስትል በማኅበራዊ ሚዲያ ባጋራችው ቪዲዮ " የወጡት የAI ምስሎች የተፈጠሩት በበጋ ወቅት ቢሆንም ጉዳዩ ወደ አደባባይ የወጣው በቅርብ ቀናት ነው " ብላለች።

" ምን ያህል ሕጻናት ምስሎቹ እንደነበራቸው አናውቅም። ምስሎቹ የወሲብ ፊልም በሚጫንባቸው ገጾች ላይ ተጭነው እንደሆነም አናውቅም ነበር። ይህ ሁሉ ስጋት ነበረብን " ብላለች።

በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰሩ የታዳጊ ሴቶች እርቃን ምስሎችን ባማውጣት የተጠረጠሩ ታዳጊዎች ዕድሜያቸው ከ12 እስከ 14 የሚደርስ ነው።

ፖሊስ ድርጊቱን እየመረመረ ሲሆን ምስሎቹን በመፍጠር ሒደት ውስጥ አሊያም በማኅበራዊ ሚዲያዎቹ #ዋትስአፕ እና #ቴሌግራም በማጋራት ተሳትፈዋል ያላቸውን ቢያንስ አስራ አንድ የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ታዳጊ ወንዶችን መለየቱን አስታውቋል።

መርማሪዎች ታዳጊ ወንዶቹ ሐሰተኛ ምስሎችን በመጠቀም ታዳጊ ሴቶቹን #በማስፈራራት ማግኘት የፈለጉት ነገር ስለመኖሩ ለማወቅ ምርመራ እያካሄዱ ነው።

#BBC

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

(ለተማሪዎች እና ለወላጆች)

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለ2 ወር የሚቆይ የAI ሰመር ካምፕ የስልጠና መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጀቱን ገልጿል።

በስልጠናው መርሃ ግብር ላይ መሳተፍ የሚችሉት የመጀመሪያ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆኑ ናቸው።

ተማሪዎቹ ስልጠናውን በሳምንት ለ4 ቀናት መከታተል የሚችሉ መሆን አለባቸው።

ለተከታታይ 2 ወራት ለሚሰጠው ስልጠና ፍላጎት ያላቸው ታዳጊዎች ከዛሬ ጀምሮ እስከ ግንቦት 07/2016 ባሉት ተከታታይ ቀናት መመዝገብ ይችላሉ።

ስልጠናው የሚያተኩርባቸው ፦
➡️ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መሰረታውያን፣
➡️ ሮቦቲክስ፣
➡️ ፕሮግራሚንግ፣
➡️ ማሽን ለርኒንግ
➡️ ኢንተርኔት ኦፍ ቲንግስ (IoT) እንደሆኑ ተገልጿል።

በስልጠናው መሳተፍ የሚፈልጉ አመልካቾች ፦

👉 forms.gle/9B79pzGLdo84W2LY8

👉 https://www.aii.et/summer-camp-registration-form-for-student/ ላይ መመዝገብ ይችላሉ።

በተጨማሪ እውቀትና ክህሎታቸውን ለተማሪዎች በማካፈል በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ትውልዱን ለመገንባት ዕድሉን የሚፈልጉ አሰልጣኞች ፦

👉 www.aii.et/ethiopian-ai-summer-camp-2024-application-form-trainer-for-summer-camp/

👉 forms.gle/P2vAoZuWT7JgYQtT6 ላይ መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

#AI #ETHIOPIA

@tikvahethiopia
#AI

" AIን ስነምግባር በተሞላበት መንገድ ለመጠቀም እንድንችል፣ የአጠቃቀም ፖሊሲና መመሪያ ያስፈልገናል፡፡ AIን አትጠቀም ብሎ መከልከል መፍትሔ አይሆንም " -ዶ/ር ደረጄ እንግዳ

የቻይናው ሁዋዌ ተክኖሎጂስ፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት / AI ቴክኖሎጂን በትምህርት ዘርፍ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የሚመክር ስበሰባ በትላንትናው ዕለት አካሂዶ ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተከታተለው በዚህ የውይይት በመድረክ የAI ቴክኖሎጂን በተለይም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለማስፋፋት የተለያዩ ችግሮች መኖራቸውን ተነስቷል።

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕረዝደንት የሆኑት ዶ/ር ደረጄ እንግዳ ፦
- በገጠርም ሆነ በከተማ ኤአይን ለመጠቀም የመሰረተልማት አለመስፋፋት፤
- የሰለጠነ የሰው ሀይል እጥረት፤
- የተሰጥኦ ማነስ፤
- የሰለጠነ የሰው ሀይል ፍልሰት ተግዳሮት መሆኑን አንስተዋል።

" አሁን ከቴክኖሎጂው እያገኘን ያለነው ጥቅም ምናልባትም ከጎግል የተለየ አይደለም ከዚያ ባሻገር ልንጠቀምበት ይገባል " ሲሉ ጠቁመዋል።

" በትምህርት ዘርፉ በዩኒቨርሲቲዎች ያሉንን መምህራን ማሰልጠንና ማብቃት አለብን " ያሉት ዶ/ር ደረጄ " AIን ስነምግባር በተሞላበት መንገድ ለመጠቀም እንድንችል፣ የአጠቃቀም ፖሊሲና መመሪያ ያስፈልገናል፡፡ AIን አትጠቀም ብሎ መከልከል መፍትሔ አይሆንም " ብለዋል።

" ስርዓተ ትምህርታችንን/ካሪኩለሙን መከለስ አለብን፣ ስርዓተ ትምህርቱ ራሱ ለዚህ የሚያመች አይደለም፡፡ ባለፉት ሶስትና አራት አመታት በኤአይ ዘርፍ ብዙ ለውጦት ቢኖሩም ይህንን ወደ ትምህርት ስርዓቱ ማካተት አልተቻለም፡፡ አንዱና ትልቁ እንቅፋት እሱ ነው " ሲሉ ነው የገለጹት።

ተማሪዎቻችንን የምንመዝንበት መንገድም ዳግም መታየት አለበት ያሉት ፕረዚዳንቱ " ብዙ ፈተናዎች አሉን፣ ግን ይህንን ተቋቁመን ወደፊት መግፋት አለብን፡፡ ኤአይን ለማስፋፋት በጣም ግዙፍ የሆነ ኢንቨስትመንት ይፈልጋል፣ ትልቅ የአስተሳሰብ ለውጥም ያስፈልጋል " ነው ያሉት።

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕረዝደንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ በበኩላቸው ኤአይን በመጠቀሙ ሒደት የቁጥጥር ስርዓት መዘርጋት እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።

በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ያለውን የኤአይ አጠቃቀምን ስናስብ፣ ባልተገባ መንገድ የመጠቀሙ ነገርም አብሮ መታሰብ አለበት ያሉት ዶ/ር ጀማል፣ ይህ በጣም አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል በማለት ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡

ስርዓተ ትምህርቱ በፅንሰ ሀሳብ ላይ የተንጠለጠለ ነው ያሉት ዶ/ር ጀማል ተስጥኦን ማበልፀግ ከህፃናት መጀመር አለበት፡፡ ህፃናትን በኤአይ ዘርፍ ማነሳሳት አስፈላጊ ነው፡፡ ከዛም በትምህርት ቤቶችና በዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ ግንዛቤውን ማስፋት ተገቢነት አለው ሲሉ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@tikvahethiopia
በAI ዘርፍ ተስፋ እና ስጋትን ይበልጥ ያጫረው Veo 3 . . . ለዚህ ዝግጁ ነን ?

ግዙፉ የአለማችን የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጎግል Veo 3 የተሰኘ ቪዲዮ የሚሰራ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ከሰሞኑ ከለቀቀ በኋላ ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል።

የቴክኖሎጂ ኩባንያው አዲስ ያስተዋወቀው Veo 3 በራሱ ቪዲዮ ሰርቶ ድምፅን ከቪዲዮው ጋር የሚያዋህድ ሲሆን ከዚህ በፊት ከነበሩት በጥራት ከፍ ያለ ነው።

መተግበሪያው ከOPEN AI ምርት ከሆነው sora ለየት የሚያደርገው በሰዎች መካከል የሚደረጉትን ንግግሮች እውነት እስኪመስል ድረስ ድምፅና ምስልን በማቀናበር ማቅረቡ ነው።

በዚህ የጎግል አዲሱ ቴክኖሎጂ የተሰሩ ቪዲዮዎች (ከላይ እንዳለው አይነት) ከእውነተኛ ቪዲዮች ለመለየት በሚያዳግት ደረጃ የቀረቡ ሲሆን የቋንቋ አማራጩም ከዚህ ቀደም ከነበሩት እጅጉን የሚሻል ነው ተብሏል።

አሁን ላይ መተግበሪያውን ለመጠቀም የ249.9 ዶላር ወርሃዊ ክፍያ ያስፈልጋል ተብሏል።

በርካታ በVeo 3 የተሰሩ ቪዲዮዎች ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲለቀቁ አብዛኛው ሰው ከእውነተኛ ቪዲዮዎች ለመለየት ሲቸገር ተስተውሏል።

ቴክኖሎጂው ይፋ በሆነ በጥቂት ቀናት በአማርኛ ቋንቋ ተሰርተው የተለቀቁ ቪዲዮዎችን እንኳን ብንመለከት በቀላሉ ለመለየት አስቸጋሪ ሆኗል። ከዚህ ቀደም ድምጽ ላይ የነበሩ ክፍተቶች በአጭር ጊዜ ተሻሽለው እንደቀረቡ ተነግሯል።

ጎግል በተጨማሪ FLOW የተሰኘ የተለያዩ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መተግበሪያዎችን ያካተተ እና ፊልም ሰሪዎች በፈለጉት መንገድ ፊልማቸውን እንዲሰሩ የሚያግዝ የፊልም መስሪያ መተግበሪያንም ይፋ አድርጓል።

ይህም በዘርፉ ስጋትንም ተስፋንም ይዞ መምጣቱ ተነግሯል።

ተጠቃሚዎች በVeo 3 መስራት የሚፈልጉትን ነገር በፅሁፍ እንደሚያስገቡ የተነገረ ሲሆን መተግበሪያው ከተሰጠው ፅሁፍ በመነሳት እውነተኛ የሚመስል ቪዲዮን ከሰራ በኋላ ትክክለኛ የሚመስሉ ድምፆችን በመጨመር ለተጠቃሚዎች ያቀርባል።

ተጠቃሚዎች የቀረበላቸውን ቪዲዮ ካዩ በኋላ FLOW የተሰኘውን ሌላ የጎግል መተግበሪያ በመጠቀም የካሜራ አንግልና የገፀ ባህሪያትን እንቅስቃሴ መቀየር ይችላሉ ተብሏል።

ወጪን ከመቀነስ አንፃር በ500 ሺህ ዶላር ሊሰራ የሚችልን የመድሃኒት ማስታወቂያ በVeo 3 ከ500 ዶላር ባነሰ ገንዘብ በአንድ ቀን ውስጥ መስራት እንደተቻለ ተሰምቷል።

አንዳንድ ሰዎች ስለ አዲሱ ቴክኖሎጂ " ፈጠራን ይቀንሳል " በሚል ሃሳባቸውን እያንፀባረቁ ሲሆን ተመልካቾች ደግሞ እውነተኛ ቪዲዮ አለመሆናቸውን ለመለየት መቸገራቸው ሌላ ፈተና ነው ተብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከCNBC እና AXIOS ነው ያሰባሰበው።

Video Credit : Ehud Ai Studio

#AI #Google #Gemini

Via @TikvahethMagazine