TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ🔝ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ጋር ያደረጉት ውይይት በፎቶ📸

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ኦነግ አዲስ ፓርቲ አይደለሁም፤ እንደገና መመዝገብ #የለብኝም ሲል ያቀረበውን አቤቶታ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ወድቅ አድርጎታል፡፡ የኦነግ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ ዳባ ግን ግንባሩ በ1983 ዓ.ም በሕግ ስለተመዘገበ አሁን ድጋሚ አይመዘገብም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡ ኦነግ ይህንኑ አቋሙን ለቦርዱ ማሳወቁንም ገልጸዋል- ቃል አቀባዩ፡፡

©wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) ነባር አመራሮችን በወጣቶች ተክቶ  በሀገሪቱ የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ ወደ ክልሉ በማውረድ ለማሳካት እንደሚሰራ የድርጅቱ ሊቀመንበር አስታወቁ፡፡ #በሰመራ ከተማ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የአብዴፓ ድርጅታዊ ኮንፈረንስ የአቋም መግለጫ በማውጣት ትናንት ተጠናቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሹመት‼️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለተለያዮ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች #ሹመት ሰጥተዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መግለጫ መሰረት፦

1.ዶክተር አምባቸው መኮንን፦ የጠቅላይ ሚንስትሩ የመሰረተ ልማትና የከተማ ልማት አማካሪ ሚንስትር

2.አቶ ገብረእግዚአብሔር አርአያ፦ በሚንስትር ዴኤታ ማዕረግ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ

3.አቶ ጫኔ ሽመካ፦ በሚንስትር ዴኤታ ማዕረግ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ

4.አቶ ጫላ ለሚ፦ በሚንስትር ዴኤታ ማዕረግ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ

5.አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ፦ የጠቅላይ ሚንስትሩ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሚንስትር ዴኤታ

6.ብርጋዴል ጄኔራል አህመድ ሀምዛ፦ የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር

7.አቶ ሞቱማ መቃሳ፦ የጠቅላይ ሚንስትሩ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሚንስትር ዴኤታ

8.አቶ ከበደ ይማም፦ የአካባቢ ጥበቃ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር

9.አቶ አዘዘው ጫኔ፦ የጉምሩክ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር

10.አቶ አወል አብዲ፦ የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር

11.አቶ ሙሉጌታ በየነ፦ የጉምሩክ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር

12.ዶክተር ፅጌረዳ ክፍሌ፦ የብሔራዊ ኤች. አይ. ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር

13.ወይዘሮ ያምሮት አንዱዓለም፦ የአርማወር ሐሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር

14.ዶክተር ሚዛን ኪሮስ፦ የኢትዮጵያ ጤና መድህን ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር

15.አቶ ሀሚድ ከኒሶ፦ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር

16.አቶ ከበደ ጫኔ፦ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር

17.ወይዘሮ ምስራቅ ማሞ፦ የጉምሩክ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል።

ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥረት‼️

• በየዓመቱ 100 ሚሊዮን ብር ሲከስር ነበር፡፡

• የባንክ ዕዳውም 2 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡

በቀድሞው ኢህዴን (አዴፓ) በዘላቂ በጎ አድራጎት ወይም ኢንዶውመንት ቁመና ይዞ የተመሠረተው ጥረት ኮርፖሬት 20 ኩባንያዎች አሉት። ከእነዚህ ውስጥ ከሰባቱ በየዓመቱ 100 ሚሊየን ብር አካባቢ ይከስራል።

የጥረት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አምላኩ አስረስ እንደሚሉት በቀደመው አመራር ጥረት 11 ቢሊዮን ብር ጥሬ ሀብት አለው ተብሎ ሪፖርት የተደረገውም ስህተት ነው። የጥረት በአሁኑ ወቅት ያለው ጥሬ ሀብት 5 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ሲሆን 2 ነጥብ 7 ቢሊዮን አካባቢ የባንክ ዕዳ አለበት። ከዚህም በተጨማሪ ካሉት 20 ኩባንያዎች በሰባት ኩባንያዎች በየዓመቱ 100 ሚሊዮን ብር ይከስራል።

ጥረት በትራንስፖርት ዘርፉ የተሠማሩ 500 ተሽከርካሪዎች አሉት እየተባለ ሪፖርት ሲደረግ ቢቆይም በተግባር ያሉት ተሸከርካሪዎች ግን 348 ናቸው። ከዚህ ውስጥ 48ቱ ብቻ ዓመት እስከ ዓመት ይሠራሉ፤ ሌሎቹ የተበላሹ ናቸው። ጥረት ከኪሳራው ለመውጣት አዲስ ፍኖተ ካርታ እያዘጋጀ ሲሆን የመዋቅር እና የአመራር ለውጥም እያደረገ እንደሆነ ዶክተር አምላኩ አስረድተዋል። አጥፊዎችም #በሕግ የሚጠየቁ ይሆናል ብለዋል።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ እናቶችን ያቀፈ 22 አባላት ያሉት #የሰላም_አምባሳደሮች ቡድን መቀሌ ገብቷል፡፡ ቡድኑ ከሁሉም ክልሎች እና ከአዲስ አበባ እና ድሬደዋ የተውጣጣ ነው፡፡ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ደብረ ጺዮን ገብረ ሚካዔል ቡድኑም ሲቀበሉ ባደረጉት ንግግር ለሰላም ተልዕኮ የመጣችሁበት ትግራይ ክልል ሰላማዊ ነው ብለዋል፡፡ ቡድኑ በቆይታው ከተለያዩ ኅብረተሰብ ክፍሎች፣ ከክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ጋር ይወያያል፡፡

©wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትግራይ ክልል‼️

የትግራይ ክልል ለ3 ሺህ 231 ታራሚዎች #ይቅርታ አደረገ። የክልሉ የፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እንዳስታወቀው፥ ይቅርታ ከተደረገላቸው ታራሚዎች መካከል 72ቱ #ሴቶች ናቸው።

ታራሚዎቹ የይቅርታ ህግን ያሟሉ መሆናቸውን ተከትሎ ነው በይቅርታ እንዲለቀቁ መደረጉን የቢሮው ሀላፊ አቶ #ተኪኡ_ምትኩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

ታራሚዎቹ ከህዳር 20 ቀን 2011 ጀምሮም ወደ ህብረተሰቡ እንደሚቀላቀሉም ተመልክቷል።

የክልል መንግስት ባለፈው ዓመት የግንቦት 20 በዓልን ምክንያት ለ2 ሺህ 206 ታራሚዎች ይቅርታ አድርጎ አንደነበር ይታወሳል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል‼️

ባለፈው ሳምንት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ያሶ ከተማ በፈፀመ ጥቃት #ስምንት የአንድ ቤተሰብ አባላት #መገደላቸውን የሟች ቤተሰቦች ለቢቢሲ ተናገሩ።

ህዳር 11 ቀን 2011 ማታ ከሶስት ሰዓት በኋላ ታጣቂዎች የቤተሰብ አባላቱን በጥይት ገድለው ቤታቸውንም እንዳቃጠሉ በጥቃቱ ባለቤታቸውንና የባለቤታቸውን ወንድሞች ያጡት የስምንት ልጆች እናት ወ/ሮ #ልኪቱ_ተፈራ ይናገራሉ።

"መጀመሪያ ተኩስ ከከፈቱብን በኋላ ቤት ውስጥ ጭድ ጨምረው እሳት ለኮሱብን። እኔና ልጆቼ በጓሮ በር በኩል አመለጥን። ሌሎቹ ግን እዚያው ተቃጠሉ" በማለት ሁኔታውን ያስታውሳሉ።

ልጃቸው አቶ ወጋሪ ፈይሳ በመኖሪያ ቤታቸው በወቅቱ ሃያ አንድ የቤተሰብ አባላት እንደነበሩና ቤታቸውም ፖሊስ ጣቢያ አቅራቢያ በመሆኑ ደህንነት ተሰምቷቸው እንደነበር ይናገራል።

ነገር ግን ያልጠበቁት ነገር መከሰቱንና በተፈጠረው ነገርም ህፃናት ልጆች ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ እንዳሉም ይገልፃሉ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙሳ አህመድ ከተማው ውስጥ ግድያ ስለ መከሰቱ መረጃ እንዳላቸው ነገር ግን ዝርዝር ጉዳዮችን እንደማያውቁ ገልፀዋል።

ከጥቃቱ የተረፉ የቤተሰቡ አባላት ሸሽተው የተጠለሉበት አዋሳኝ የምሥራቅ ወለጋ ሃሮ ሊሙ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጋሮማ ቶሎሳ ግድያው ስለመፈፀሙ ማረጋገጫ እንዳላቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።

"አባቴ ፈይሳ ዲሳሳ፣ ወንድሙ ዲንሳ ዲሳሳን ጨምሮ ስምንት የአጎቶቼ ልጆችን አጥተናል። ግድያው በጣም አሰቃቂ ነበር" ይላሉ አቶ ዋጋሪ።

በተመሳሳይ እለት የቤተሰብ አባላቱን ግድያ ጨምሮ በያሶ ከተማ በተፈፀመ ጥቃት አርባ የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸውን ኗሪዎችና የአዋሳኝ ወረዳ አስተዳዳሪው ቢናገሩም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊው አቶ ሙሳ ግን አስር ሰው ብቻ ስለመገደሉ መረጃ እንዳላቸው ይገልፃሉ።

ሆኖም ግን ጉዳዩን በሚመለከት ተጨማሪ መረጃ እንደሚያስፈልጋቸው "መንገድ በመዘጋቱ ነገሮችን በቅርበት ማጣራት አልቻልንም" በማለት ተናግረዋል።

አቶ ሙሳ እንደሚሉት የረቡዕ ጥቃት ከመፈፀሙ ከጥቂት ቀናት በፊት ሁለት የመንግሥት ሰራተኞች ተገድለዋል። አርብ እለትም ደግሞ በካማሼ ሌሎች ሦስት ሰዎች መሞታቸውንም ገልፀዋል።

በያሶ ጥቃቱን የፈፀሙት ታጣቂዎች ከመሆናቸው በዘለለ ስለታጣቂዎቹ እስካሁን ምንም የተረጋገጠ መረጃ እንደሌለ አቶ ሙሳ ይናገራሉ።

'ያፈነገጡ የኦነግ ታጣቂዎች' ለአካባቢው ስጋት እየሆኑ እንደሆነ አቶ ሙሳ ቢናገሩም ያነጋገርናቸው ኗሪዎች እና የአዋሳኝ ወረዳ ሃላፊዎች ግን በአካባቢው #የኦነግ ታጣቂ እንደሌለ ገልፀዋል።

በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ አራት የካማሺ ዞን ሃላፊዎች አሶሳ ከተማ ስብሰባ ቆይተው ወደ ካማሺ በመመለስ ላይ ሳሉ በተከፈተባቸው ተኩስ ህይወታቸው ማለፉን ተከትሎ በተፈጠረ ግጭት ብዙዎች መገደላቸውንና ወደ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ከቀያቸው መፈናቀላቸው ይታወሳል።

በአሁኑ ወቅት ግን ነገሮችን #ለመቆጣጠር በያሶ ከተማ ፌደራል ፖሊስ፤ በካማሽ ደግሞ መከላከያ ሠራዊት እንደገባ አቶ ሙሳ ገልፀዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ አየር መንገድ🛫

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ7ኛ ተከታታይ ጊዜ የአፍሪካ የምርጥ አየር መንገድ ሽልማትን #አሸነፈ

አየር መንገዱ ሞሮኮ ራባት ላይ እየተካሄደ በሚገኘው 50ኛው የአፍሪካ ታላላቅ አየር መንገዶች ማህበር አመታዊ ጉባኤ ላይ አሸናፊ መሆኑ የተበሰረው።

የእውቅናው ሽልማቱ ለአየር መንገዱ በፋይናንስና ትርፋማነት አፈጻጸም ላይ ባሳየው የላቀ ደረጃ ምክንያት እንደተበረከተለት ተነግሯል።

ምንጭ፦ FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport ካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ውጤት፦

ጅቡቲ ቴሌኮም 1-3 ጅማ አባጅፋር
አስቻለው ግርማ
ማማዱ ሲዲቤ
ማማዱ ሲዲቤ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማሳሰቢያ‼️

ወህዴግ በማህበራዊ ሚዲያ በቀን 19/03/2011 ዓ.ም #በወላይታ_ሶዶ ከተማ #ሠላማዊ_ሰልፍ እንደሚያደርግ እየገለፀ ያለ ቢሆንም የዞኑ አስተዳደር አሁን ያለውን #የፀጥታ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ፍቃድ ያልተሰጠ ስለሆነና ነባራዊ ሁኔታን በመገምገም ወደፊት የሚፈቅድ መሆኑ ታውቆ በተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮችም ሆነ አባላት የሚደረገው ቅስቀሳ ተገቢ ያለመሆኑን በመገንዘብ #ጥንቃቄ እንዲደረግ እናሳስባለን፡፡

©Wolaita ZONE Culture, tourisim and Governmental Communication Affairs Office
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ🔝

በኢትዮጵያ የሚገኙ ከሰባ በላይ ፓርቲዎች ለሚቀጥለው #ምርጫ እንዲዘጋጁ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ጥሪ አቀረቡ።

ከፓርቲዎቹ መሪዎች ጋር ዛሬ ውይይት ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ፤ ከቀጣዩ ምርጫ በፊት ቁጥራቸው ወደ አምስት እና ስድስት ዝቅ እንደሚል ተስፋቸውን ገልፀዋል።

ለቀጣዩ ምርጫ ነፃና ፍትሃዊ መሆን የሚያስፈልጉ ዝግጅቶች በጊዜ ካልተጠናቀቁ ምርጫውን ማራዘሙ የግድ አስፈላጊ ሊሆን እንደሚችል የገለፁት ደግሞ፤ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ናቸው።

ምንጭ፦ VOA አማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እውነት ተናግረክ የምታጣው ነገር ቢኖር አጠገብክ ያሉ #ሀሰት ተናጋሪ ሰዎችን ብቻ ነው!!

መልካም ቀን ይሁንልን!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ካራ ቆሬ🔝

በአሁን ሰዓት #ካራ_ቆሬ አካባቢ በተለምዶ ግራር ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ቤቶቻቸው የፈረሰባቸው ነዋሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ እያደረጉ ይገኛሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኤች አይ ቪ መከላከያ መድሃኒት‼️

የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ምንስቴር የኤች አይ ቪ መከላከያ መድሃኒት በሙከራ መልክ መስጠት እንደሚጀምር አስታወቀ። ከቫይረሱ ነፃ ለሆኑ ሰዎች  የሚሰጠዉ ይኽው መድሃኒት በእንክብል መልክ በቀን አንድ ጊዜ የሚወሰድ ይሆናል።


በምንስቴር መስሪያ ቤቱ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ቡድን መሪ ወይዘሮ ምርቴ ጌታቸዉ ለDW እንደገለፁት መከላከያ መድሃኒቱ በሙከራ መልክ በቅርቡ መሰጠት ይጀምራል።  ህክምናዉ የሚሰጠዉ ከኤች አይ ቪ ነፃ ለሆኑ ነገር ግን ለቫይረሱ #ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ነዉ።

እንደ ወይዘሮ ምርቴ የመከላከያ መድሃኒቱ ሙከራ የሚጀመረዉ የኤች አይ ቬ ስርጭት ከፍተኛ በሆነባቸዉ  15 የሀገሪቱ ክፍሎች ሲሆን በተመረጡ የመንግስት የጤና ተቋማትና USAID የተባለዉ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅት በገንዘብ በሚደግፋቸዉ የጤና ማዕከላት በነፃ ይሰጣል።

የመከከላከያ ህክምናዉ ከአሁን ቀደም ደቡብ አፍሪካን በመሳሰሉ የበሽታዉ ስርጭት ከፍተኛ በሆነባቸዉ ሀገራት ተሞክሮ አስተማማኝ ዉጤት መገኘቱን የገለፁት ወይዘሮ ምርቴ ፤ያማለት ግን ሌሎች በሽታዉን ለመከላከል የሚደረጉ የጥንቃቄ ዘዴዎችን ይተካል ማለት እንዳልሆነ አሳስበዋል።ስለሆነም ህክምናዉ ከሌሎች የመከላከያ ዘዴዎች ጎን ለጎን የሚሰጥና የጊዜ ገደብም ያለዉ ነዉ ብለዋል።

መድሃኒቱ ከመሰጠቱ በፊት የኤች አይቪ ምርምራ ማድረግን የሚጠይቅ ሲሆን ምርመራዉም በየ 3 ወሩ የሚቀጥል ይሆናል ነዉ ያሉት። የሙከራ ህክምናዉ በሚጀመርባቸዉ የጤና ተቋማት የሚገኙ የጤና ባለሙያዎችም በዝርዝር ስለሚያከናዉኗቸዉ ስራዎች የተለዬ ስልጠና መዉሰዳቸዉን ሀላፊዋ አመልክተዋል።

የሙከራ ስራዉ ሲጠናቀቅም የተገኘዉን ዉጤት መሰረት በማድረግ በመደበኛነት በየጤና ተቋማቱ መድሃኒቱን መሰጠት እንደሚጀመር ሀላፊዋ ገልፀዋል። 

የመከላከያ መድሃኒቱ ሲጀመር ኤች አይ ቬ ኤድስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረገዉ ጥረት እንዳይቀዛቀዝና መዘናጋት እንዳይፈጠርም ተጨማሪ ሥራዎች ለመሥራት ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ማቀዱን ሀላፊዋ ጨምረዉ አመልክተዋል። 

«ሚዲያ ላይ በደንብ «አዌርነስ» መፍጠር፣ ንቃተ ህሊናን የማሳደግ ስራዎችን መስራት ፣ይህንን መጀመር ማለት ሙሉ በሙሉ ነፃ እንሆናለንና እንደፈለግን እንሆናለን ማለት እንዳልሆነ፣ በደንብ መስራት ይኖርብናል።እንግዲህ ለወደፊት የምንሰራዉና አንዱ እቅዳችን ዉስጥ ያስገባነዉ ዋና ተግባር ነዉ።»

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወላይታ 🕊 ሲዳማ!

የወላይታና የሲዳማ ህዝቦች ሰላም ወዳድ፣ ጠንካራ #ፍቅር ያላቸውና ተለያይተው መኖር የማይችሉ መሆናቸውን አረጋግጠናል ሲሉ የሲዳማና ወላይታ ገለልተኛ አስታራቂ አባቶች ገለጹ፡፡

በህዝቦች መካከል ለዘመናት የቆየው አብሮነትና አንድነት ከጠፋ አገሪቱን ወደሚፈለገው የዕድገት ደረጃ ላይ ማድረስ ስለማይቻል ህዝቡ ሰላምና አብሮነቱን ማጠናከር እንዳለበት አባቶቹ መክረዋል።

በወላይታና ሲዳማ ተወላጆች መካከል ተከስቶ የነበረውን አለመግባባት ወደሰላም ለመመለስ ፈታኝና እልህ አስጨራሽ የእርቅ ሂደት ማለፋቸውን የተናገሩት አስታራቂ አባቶቹ ሁለቱ ህዝቦች ሰላም ወዳድ፣ እርስ በርስ ፍቅር ያላቸውና መለያየት እንደማይችሉ ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል።

የገለልተኛ አስታራቂ ኮሚቴው ሰብሳቢ መጋቢ ጌቱ አያሌው እርቅ ለማውረድ በተደረገው ጥረት በሁለቱ ወንድማማች ህዝብ መካከል ተፈጥሮ የነበረው የጥል ግድግዳ መፍረሱንና በእዚህም ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

“ሁለቱን ህዝብ ለማስታረቅ እልህ አስጨራሽና ፈታኝ ወቅት አልፈናል” ያሉት መጋቤ ጌቱ፣ ሠላምና እርቅ የማይፈልጉ ሁለቱንም ብሄር የማይወክሉ ግለሰቦች በአካልና በማህበራዊ ሚዲያ ስም የማጥፋት፣ የማስፈራራትና ተስፋ የማስቆረጥ ሥራዎችን ቢሰሩም እርቁ በስኬት መጠናቀቁን ገልጸዋል።

ዕርቀ ሰላሙን ለማውረድ ከሁለቱም ብሔር አገር ሸማግሌዎች ጋር ለአራት ወራት የመከሩ ሲሆን በእዚህም ሁለቱም ህዝቦች ሰላም ወዳድ ከመሆናቸው ባለፈ እርስ በርስ የሚፋቀሩና ተለያይተው መኖር የማይችሉ ናቸው።

በህዝቦች መካከል ያለውን አብሮነትና አንድነት በመጠበቅ በአገሪቱ የሚፈለገውን እድገት ለማምጣት ተረባርቦ መስራት እንደሚገባም  አሳስበዋል፡፡

የሃዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አስተዳዳሪ መላከ ምህረት ቆሞስ አባ ጌዲዮን ብርሃን በበኩላቸው መነጣጠል የማይችሉ ሁለቱ ህዝቦች በመታረቃቸው ከማንም በላይ የተለየ ደስታ እንደተሰማቸው ነው የገለጹት።

በእርቅ ሂደት ውስጥ የሲዳማና የወላይታ አገር ሸማግሌዎች ሠላም ለማውረድ ከፍተኛ እገዛ ማድረጋቸውንና የክልሉና የሁለቱ ዞን የመንግስት አካላትም ላሳዩት ቀና ትብብር ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የእርቀ ሠላም ጉባኤው ለኢትዮጵያውንና ህዝብን ለማበጣበጥና የአገሪቱን ሠላም ለማድፍረስ ደፋ ቀና ለሚሉ አካላት ትልቅ ትምህርት የሰጠ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

“ኢትዮጵያውያን ያለንን አብሮነትና አንድነት ካጣን ወደምናስበው የእድገት ደረጃ መድረስ ስለማንችል ቆም ብለን ልናስብ ይገባል” ሲሉም መላከ ምህረት ቆሞስ አባ ጌዲዮን አመልክተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ወጣት ፍቅርና አንድነቱን ጠብቆ በማቆየት ሰላምና ልማቷ የተረጋገጠ አገር ለቀጣይ ትውልድ ማስተላለፍ እንዳለበት አውቆ ለእዚያ መንቀሳቀስ እንዳለበትም መክረዋል፡፡

ከአላህ ዘንድ የተሰጣቸውን ትልቅ ኃላፊነት በስኬት በማጠናቀቃቸው ሀሴት እንደተሰማቸው የገለጹት ደግሞ የደቡብ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንትና የገለልተኛ አስታራቂ ኮሚቴ አባል ሃጂ አህባበብ አባ ጀማል ናቸው፡፡

የሲዳማና የወላይታ አገር ሸማግሌዎች ሰላም የሚሹ ፣ የተጎራበቱ፣ የተጋቡና የተዋለዱ መሆናቸውን ያረጋገጡበት የእርቅ ሂደት መሆኑን የገለጹት ሃጂ አህባበብ፣ ሰላም አንዲወርድ እንደኮሚቴ ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

ለአብሮነትና ለሠላም ቅርብ በሆኑ ህዝቦች መካከል ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የተከሰተው መራራቅና አለመተማመን በአሁኑ ወቅት መፈታቱንና በቀጣይም ለዘላቂ ሰላም በቅንጅት እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

በቅርቡ በሃዋሳና በሶዶ ከተማ የተካሄደው የሁለቱ ህዝቦች የይቅርታና እርቅ ኮንፈረንስ በገለልተኛ አስታራቂ ሽማግሌዎች ላለፉት አራት ወራት የተለያዩ ሂደቶችን ያለፈ መሆኑን ታውቋል፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ዜ.አ
@tsegabwolde @tikvahethiopia