TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UpateSport በስፔን አገር አቋራጭ ውድድር ሰለሞን ባረጋ አሸንፎ ሲገባ የተነሳው ፎቶግራፍ በአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የአመቱ ምርጥ ፎቶ እጩ ሆነ። ፎቶግራፈሩን ፍሊክስ ሳንቼዝ አትሌት ሰለሞን ባረጋ መልካም እድል ሲል ተመኝቶለታል።

@tseegab @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update በሰብአዊ መብት ጥሰት፣ በሙስናና የተደራጀ ሌብነት ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎችን #ብሔርን መሰረት ተደርጐ እርምጃ እየተወሰደ ነው በሚል የሚሰጡ አስተያየቶች የተሳሳቱ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ ገልፀዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ🔝ተማሪዎች ከፌደራል ከመጡ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር ውይይት እያደረጉ ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ኢትዮጵያ ውስጥ በአገር አቀፍ ደረጃ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚደረግ ውይይትና ድርድር የሚመራበት ህግ /rule of engagment/ ሊዘጋጅ እንደሆነ ተሰምቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from Afriwork (Freelance Ethiopia) (Semegn)
More than 50 jobs per week in different fields. Join this group to get projects, part time and full time jobs. @freelance_ethio
አሳዛኝ ዜና‼️

በቻይና አንድ የኬሚካል ፋብሪካ ላይ በደረሰ #ፍንዳታ 22 ሰዎች ሞቱ
በቻይና በኬሚካል ፋብሪካ ላይ በደረሰ ፍንዳታ 22 ሰዎች ሲሞቱ 22 የሚሆኑት ጉዳት ተርሶባቸዋል።

ፍንዳታው የተከሰተው በቻይና ሰሜናዊ የሂቤ ግዛት በሚገኝ ስፍራ ውስጥ ሲሆን በዚሁ አደጋ ሀምሳ የሚሆኑ ተሸከርካሪዎች ወድመዋል፡፡

በኬሚካል ፍንዳታው በአካባቢው ዓየር ላይ የጠቆረ ጭስ እና ነበልባል በማስከተል ለብክለት መንስኤ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

እንደ ሀገሪቱ መንግስት ባለስልጣናት ገለፃ 50 ያህል የእሳት አደጋ መከላከያ መኪኖች በማሰማራት ቃጠሎውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረት ማድረጋቸውን ጠቁመዋል፡፡ 

የሀገሪቱ የዜና አውታር እንደዘገበው ፍንዳታው ነኬቢ የሻንዩ ኬሚካል ኢንዱስትሪ እኩለ ለሊት ላይ መከሰቱን ጠቁማል፡፡

ከቤጂንግ ሰሜን ምዕራብ 156 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ጂንግጂካኩ በአውሮፓውያን አቆጣጠር በ2022 የሚካሄደውን ኦሎምፒክ ውድድር ለማስተናገድ ዝግጅት ላይ እንደነበረችም ነው የተጠቆመው፡፡
የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ እንደሚገኝም ነው የአካባቢው ባለስልጣናት ያስታወቁት፡፡

ቻይና ባለፉት ሶስት አስርት አመታት ከፍተኛ እድገት ካዝመዘገቡ ሀገራት ተርታ የምትመደብ ሲሆን በማእድን ማውጫዎች፣ በኢንዱስትሪና ፋብሪካዎቿ አካባቢ ያለውን ደህንነት ሁኔታ የበለጠ ለማሻሻል እየሰራች መሆጓንም ነው የሀገሪቱ ባለስልጣናት የተናገሩት፡፡

በ2015 ነሀሴ ወር በቲያንጂ ወደብ ከተማ የኬሚካል መጋዘን ፍንዳታ ተከስቶ 165 ሰዎች መሞታቸው ሚታውስ ነው ሲል አልጀዚራ በድረገጹ አስነብቧል።

ምንጭ፦ አልጀዚራ(ena)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ጀግና ልጇን አጣች!

ኢትዮጵያ ሆይ! ~ ብርታቱን፤ ጽናቱን ይስጥሽ!

የቤቴል ቲቺንግ ሆስፒታል መሥራች እና ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር #ይገረሙ_አስፋው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል። እሳቸው በሀገራችን የብዙ ነገር ጀማሪ ናቸው።

አሁን ላይ ብዙ ሆስፒታሎች ለማድረግ የሚጥሩት እንደ አይቪኤፍ (መውለድ የማይችሉ ሰዎች እንዲወልዱ የሚያደርግ ህክምናን) ሆስፒታሉ የራሱን ኦክሲጅን በራሱ ጊቢ ውስጥ እንዲያመርት ማደረግ፣ ዘመናዊ የሆስፒታል ቆሻሻ አወጋገድ፣ የግል የህክምና ትምህርት፣ የቲችንግ ሆስፒታል ኮንሴፕት፣ የህክምና ቁሶችን በራስ ማስመጣት እና የሌሎችም ብዙ ተፅእኖ ፈጣሪ ሥራዎች ጀማሪ ነበሩ።

ለአገር እና ለሕዝብ የሰሩት ዶ/ር ይገረሙ የወለዱት ልጅ ባይኖራቸውም የሚያሳደጓቸው ብዙ ልጆች ነበሩ።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን፣ ማ.እ

TIKVAH-ETH በዶክተር ይገረም ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለወዳጅ ቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኦዴፓ እና ኦዴግ ተዋሀዱ‼️

በአቶ #ሌንጮ_ለታ የሚመራው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ODF) ከኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ( ODP) ጋር መዋሃዱ እየተነገረ ነው።

ይኸው የሁለቱ ፓርቲዎች ውህደት በዛሬው ዕለት ለህዝብ #ይፋ እንደሚደረግም ተሰምቷል።

የአርትስ ቴሌቪዥን ምንጮች እንደጠቆሙት የሁለቱን ፓርቲዎች ውህደት በተመለከተ የፓርቲዎቹ አመራሮች አቶ ለማ መገርሳ እና አቶ ሌንጮ ለታ ዛሬ ከቀትር በኋላ በኦሮሚያ ፕሬዚዳንት ቢሮ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) መከፋፈል በኋላ የቀድሞ አመራሩ አቶ ሌንጮ ለታ አሁን ከኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) ጋር ሊዋሃድ መሆኑ የተነገረውን የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) መስርተው መንቀሳቀስ መጀመራቸው ይታወሳል።

በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ወደሃገር ቤት ከገቡት የፖለቲካ ፓርቲዎች ቀዳሚውም ይኸው የአቶ ሌንጮ ፓርቲ ኦዴግ ነው።

በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ከመንግስት ጋር በተደረገ ድርድር ትጥቅ ፈትቶ በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ በመወሰን ወደኢትዮጵያ መግባቱም አይዘነጋም።

ምንጭ፦ አርትስ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ እና የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ተዋህደው አብረው ለመስራት የሚያስችላቸውን የጋራ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡

@Tsegabwolde @tikvahethiopiA
ደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ🔝ዛሬ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ እና የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ሊቀመንበር ኦባንግ ሜቶ በደብረ ብርሀን ዩኒ ቨርሲቲ ፕብሊክ ሌክቸር ሠጥተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia