የኤች አይ ቪ መከላከያ መድሃኒት‼️
የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ምንስቴር የኤች አይ ቪ መከላከያ መድሃኒት በሙከራ መልክ መስጠት እንደሚጀምር አስታወቀ። ከቫይረሱ ነፃ ለሆኑ ሰዎች የሚሰጠዉ ይኽው መድሃኒት በእንክብል መልክ በቀን አንድ ጊዜ የሚወሰድ ይሆናል።
በምንስቴር መስሪያ ቤቱ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ቡድን መሪ ወይዘሮ ምርቴ ጌታቸዉ ለDW እንደገለፁት መከላከያ መድሃኒቱ በሙከራ መልክ በቅርቡ መሰጠት ይጀምራል። ህክምናዉ የሚሰጠዉ ከኤች አይ ቪ ነፃ ለሆኑ ነገር ግን ለቫይረሱ #ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ነዉ።
እንደ ወይዘሮ ምርቴ የመከላከያ መድሃኒቱ ሙከራ የሚጀመረዉ የኤች አይ ቬ ስርጭት ከፍተኛ በሆነባቸዉ 15 የሀገሪቱ ክፍሎች ሲሆን በተመረጡ የመንግስት የጤና ተቋማትና USAID የተባለዉ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅት በገንዘብ በሚደግፋቸዉ የጤና ማዕከላት በነፃ ይሰጣል።
የመከከላከያ ህክምናዉ ከአሁን ቀደም ደቡብ አፍሪካን በመሳሰሉ የበሽታዉ ስርጭት ከፍተኛ በሆነባቸዉ ሀገራት ተሞክሮ አስተማማኝ ዉጤት መገኘቱን የገለፁት ወይዘሮ ምርቴ ፤ያማለት ግን ሌሎች በሽታዉን ለመከላከል የሚደረጉ የጥንቃቄ ዘዴዎችን ይተካል ማለት እንዳልሆነ አሳስበዋል።ስለሆነም ህክምናዉ ከሌሎች የመከላከያ ዘዴዎች ጎን ለጎን የሚሰጥና የጊዜ ገደብም ያለዉ ነዉ ብለዋል።
መድሃኒቱ ከመሰጠቱ በፊት የኤች አይቪ ምርምራ ማድረግን የሚጠይቅ ሲሆን ምርመራዉም በየ 3 ወሩ የሚቀጥል ይሆናል ነዉ ያሉት። የሙከራ ህክምናዉ በሚጀመርባቸዉ የጤና ተቋማት የሚገኙ የጤና ባለሙያዎችም በዝርዝር ስለሚያከናዉኗቸዉ ስራዎች የተለዬ ስልጠና መዉሰዳቸዉን ሀላፊዋ አመልክተዋል።
የሙከራ ስራዉ ሲጠናቀቅም የተገኘዉን ዉጤት መሰረት በማድረግ በመደበኛነት በየጤና ተቋማቱ መድሃኒቱን መሰጠት እንደሚጀመር ሀላፊዋ ገልፀዋል።
የመከላከያ መድሃኒቱ ሲጀመር ኤች አይ ቬ ኤድስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረገዉ ጥረት እንዳይቀዛቀዝና መዘናጋት እንዳይፈጠርም ተጨማሪ ሥራዎች ለመሥራት ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ማቀዱን ሀላፊዋ ጨምረዉ አመልክተዋል።
«ሚዲያ ላይ በደንብ «አዌርነስ» መፍጠር፣ ንቃተ ህሊናን የማሳደግ ስራዎችን መስራት ፣ይህንን መጀመር ማለት ሙሉ በሙሉ ነፃ እንሆናለንና እንደፈለግን እንሆናለን ማለት እንዳልሆነ፣ በደንብ መስራት ይኖርብናል።እንግዲህ ለወደፊት የምንሰራዉና አንዱ እቅዳችን ዉስጥ ያስገባነዉ ዋና ተግባር ነዉ።»
ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ከኤችአይቪ / HIV #የሚያድን አዲስ መድሃኒት ተገኝቷል ?
አጭር ምላሽ ፦ #አልተገኘም
ሰሞነኛው የPrEP ጥናት ጉዳይ ሰፊ መነጋገሪያ ሆኗል።
ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ያወጡትን ዘገባ ሰዎች በተለይም በርካታ ተከታይ ያላቸው የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በተሳሳተተ መንገድ ሲረዱትም ተስተውሏል።
አንዳንዶች በሞያው ውስጥ የሌሉና በቂ ግንዛቤ የሌላቸው " ኤችአይቪ / HIV አዲስ መድሃኒት እንደተገኘለት " አድርገው ሲያጋሩም ነበር።
እውነታው ግን HIVን #የሚያድን መድሃኒት ተገኘ አልተባለም።
ከሰሞኑን በእንግሊዝ ሀገር የተደረገው ጥናት ለHIV #ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ከመያዛቸው በፊት የሚወስዱት መድሃኒት ላይ ትኩረት ያሰረገ ነው። ይህ አሰራር አዲስ ሳይሆን ቀድሞም የነበረ ነው።
የጤና ባለሞያዎች ምን አሉ ?
(ዘሪሁን ግርማ,MPH)
ማህበርሰቡ ማዋቅ ያለበት ነገር ቢኖር PrEP በHIV ከታያዝን በኃላ እንደማያገለግል ነው።
የPrEP መድሃኒት በHIV ሳንያዝ ቀድሞ የሚሰጥ የራሱ #መመሪያ ያለዉ ሲሆን የምሰጠዉም ለምሳሌ በHIV ለመያዝ በጣም ተጋላጭ ለሆኑ ሠዎች እንደ ግብረስጋ ግንኙነትን በማድረግ ገቢ የሚያገኙ ሠዎች ፣ ለአስገድዶ መደፈር ለተጋለጡና የመሳሰሉት ናቸው።
PrEP ምንድን ነው ?
PREP፣ ወይም ቅድመ-መጋለጥ ፕሮፊላክሲስ፣ በቫይረሱ የመያዝ ከፍተኛ ተጋላጭነት ባላቸው ግለሰቦች ላይ የHIV ኢንፌክሽን አደጋን ለመቀነስ የሚያገለግል ነው።
በHIV #መከላከል ስትራቴጂዎች ውስጥ ጠቃሚ መንገድ ነው
PrEP እንዴት ይሰራል ?
PrEP የሚሰራው የHIV ቫይረስ በሰውነት ውስጥ ዘላቂ የሆነ ኢንፌክሽን እንዳይፈጥር በመከላከል ነው።
መድሃኒቱ ቫይረሱ ወደ ጤናማ ሴሎች እንዳይገባ እና እንዳይበከል የሚያግድ እንቅፋት ይፈጥራል።
ቫይረሱ እንዲባዛ እና እንዲሰራጭ አስፈላጊ የሆነውን reverse transcriptase የሚባል ኢንዛይም እንዳይሰራ ይከለክላል። ይህንን ኢንዛይም በመዝጋት፣ PrEP ቫይረሱ በሰውነት ውስጥ እራሱን እንዳይፈጥር እና የHIV ኢንፌክሽን እንዳይፈጠር ለመከላከል ይረዳል።
ወቅታዊ ጥናቶች በPrEP ዙሪያ ምን ይላሉ ?
በቅርብ ጊዜ የተደረጉ ጥናቶች የPrEPን ውጤታማነት በገሃዱ ዓለም ውጤቶች አሳይተዋል።
በእንግሊዝ በ24,000 ተጠቃሚዎች ላይ የተደረገ ጥናት PrEP በኤችአይቪ የመያዝ እድልን በ86% ቀንሷል።
እነዚህ ውጤቶች በተከታታይ እና በትክክል ጥቅም ላይ ሲውሉ የPrEPን የHIV ስርጭትን ለመከላከል ያለውን ውጤታማነት ያሳያሉ።
ጥናቱ ስለ PrEP የገሃዱ ዓለም ውጤታማነት ማረጋገጫ ይሰጣል እና ይህን የመከላከያ መድሃኒት በቀላሉ ማግኘት አስፈላጊ መሆኑን ያስገነዝባል።
* * * * *
" የኤችአይቪ (HIV) መድሀኒት ተገኘ የሚል አውድ ያለው አዘጋገብ አሳሳች ነው " - ዶ/ር አሳልፍ
ዶ/ር አሳልፍ ፤ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " የኤችአይቪ (HIV) መድሀኒት ተገኘ " የሚል አውድ ያለው አዘጋገብ #አሳሳች ነው ብለዋል።
ፒአርኢፒ " Pre-exposure prophylaxis" ማለት ለኤችአይቪ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች (commercial sex workers, health professionals ... etc) ከመጋለጣቸው በፊት / ለቫይረሱ በተጋለጡ በጥቂት ሰዓታት/ቀናት ውስጥ የሚወስዱት እስካሁንም በተለያዩ አማራጭ መድሃኒቶች ይተገበር የነበረ መከላከያ መንገድ እንጂ ኤችአይቪን የሚያክም (curative ህክምና) አይደለም ሲሉ አስገንዝበዋል።
" ጥናቱም እንደዛ አይልም " ብለዋል።
@tikvahethiopia