TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አምቦ ዩኒቨርሲቲ🔝

በአምቦ ዩኒቨርሲቲ አዋሮ ካምፓስ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄዳ። ሰልፍ የወጡት ተማሪዎች የአማራ የኦሮሞ ልጆች የሚባል የለም ሁላችንም አንድ ነን፤ እዚህ የመጣንበት አላማ አንድ ነው እሱም ትምህርት ነው ብለዋል። በተጨማሪም ሁላችንም በሰላም መመለሳችንን የምትጠብቅ #ድሀ_እናት ነው ያለችን ሙሉ ሰው ልካ እሬሳ የምትቀበልበት ጊዜ አልፏል እናም ከመቼውም ጊዜ በላይ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ልንጠነቀቅ ይገባል ብለዋል። በአጠቃላይ የተሰጠንን እድል ብናውቅ እንኳን ልንጋደል ቀርቶ ልንፋቀር ጊዜ አይበቃንም ስለዚህ እኛ #ኢትዮጵያ_ነን ሲሉ ገልፀዋል። የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ በቦታው ተገኝቶ ተማሪዎቹን አነጋግሯል።
.
.
ተጨማሪ

በሰልፉ ላይ ከተሰሙት መፈክሮች መሀከል...

🔹እኛ አንድ ኢትዮጵያ፤ አንዲት ሀገር ነን!
🔹እኛ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ አንድ ነን!
🔹ኢትዮጵያ ማደግ የምትችለው በሌብነት ሳይሆን በስራ ነው!
🔹ሌባ እምነት፤ ብሄር የለውም!!

ምንጭ፦ TIKVAH-ETH(አቢቲ)
@tsegabwolde @tikvhethiopia
"እኛ ኢትዮጵያዊያን በፍቅር የተደመርን፤ #በፍቅር ያደግን ሰዎች ነን! አማራ~ኦሮሞ ትላልቅ ብሄሮች ለኢትዮጵያ #ውበት ነን!"

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ(አዋሮ ካምፓስ) ተማሪዎች ዛሬ ባደረጉት የአንድነት ሰልፍ ካሰሙት መፈክር የተወሰደ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዋሮ ካምፓስ🔝የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ተማሪዎቻቸውን #አመሰግኑ። ፕሬዘዳንቱ ተማሪዎቻቸውን ያመሰግነቱ ዛሬ ላደረጉት ከስሜታዊነት የፀዳ ፍፁም ሰላማዊ ሰልፍ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረ ማርቆስ🔝

በደብረ ማርቆስ ከተማ አንድ ግለሰብ ከዛፍ ላይ ወጥቶ #አልወርድም አለ።
በደብረ ማርቆስ ከተማ ቀበሌ 03 ከህዳሴ ጤና ጣቢያ ዝቅ ብሎ በሚገኝ ዛፍ ላይ ወጥቶ ነው ግለሰቡ ‹‹አልወርድም!››ያለው፡፡

ክስተቱ መፈጠሩን ፖሊስ የተመለከተውም ትናንት ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ ነው፡፡ የምሥራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ኢንስፔክተር ጎበዜ ይርሳው ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት እንደተናገሩት ግለሰቡ ‹‹ውረድ!›› ተብሎ ቢለመንም መልስ አልሰጠም፡፡ ፖሊስም ከዛፍ ላይ ያደረውን ግለሰብ ሲጠብቅ አድሯል፡፡ ከዛፉ ላይ ማደሩም አነጋጋሪ ሆኗል።

ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስም ግለሰቡ ከዛፉ አልወረደም። ግለሰቡን ‹‹አውቀዋለሁ›› የሚል ሰውም አልተገኘም፤ ዛፉ ረዥም መሆኑም ማንነቱን በዕይታ ለመለየት አስቸጋሪ አድርጎታል ነው ያሉት ኢንስፔክተር ጎበዜ ይርሳው፡፡

ይህ ለምን እንደሆነ ግን አልታወቀም፤ ምክንያቱንና እውነቱን የሚያውቀው ግለሰቡ ነውና፡፡ ግለሰቡ ደግሞ ይህን አልተናገረም፡፡

ምንጭ፦ የአማራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አምቦ ዩኒቨርሲቲ(ወሊሶ ካምፓስ)🔝ዛሬ በተማሪዎች ሰልፍ ምክንያት የትምህርት ስርዐቱ ተቋርጦ ነበር። የዩኒቨርሲቲው ማነጅመንት ከተማሪዎች ጋር ለመወያያት ለ8:00 ቀጠሮ ይዟል።

©ME(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በትግራይ ደቡባዊ ዞን  #ኮረም ከተማ  ሀገር አቀፍ የአትለቲክስ መንደር ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ግለሰቡ ከዛፍ ላይ ወርዷል‼️

ትናንት ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ ዛፍ ላይ በመውጣት አልወርድም ብሎ የነበረው ግለሰብ አሁን #ወርዷል፡፡ እንደ ፖሊስ መረጃ ግለሰቡ የወረደው በጓደኞች #ልመናና ጥረት ነው፡፡ አሁን ፖሊስ ምርመራ እካሄደበት ነው፡፡ ምክንቱን ግን አላስረዳም፡፡

ምንጭ፦ የአማራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዳማ🔝የምስራቅ ኦሮሚያ አጎራባች ክልሎች #የሰላምና_የእርቅ ኮንፍረንስ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው። የኦሮሚያ፣ ሐረሪ፣ ሱማሌና አፋር ክልሎች የሀይመኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ኡጋዞዎችና የጎሳ መሪዎች የእርቅና የሰላም ኮንፍረንሱ ተሳታፊዎች ናቸው።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቤቾ🔝በቾ ወረዳ የ3D ዜብራ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ሆነች። #ኤርሚያስ_ጌታቸዉ የተባለ ወጣት በህንድ እና ማሌዢያን ሃገራት እየተተገበረ ያለዉንየ 3D ዜብራ ቴክኖሎጂ የበቾ ከተማ ተጠቃሚ እንድትሆን አድርጓታል፡፡ የሴቶች፣ ወጣቶችና ህጻናት ሚኒስቴር እንዳስታወቀዉ የትራፊክ አደጋን በከፍተኛ መጠን ለመቀነስ የሚጠቅመዉን ቴክኖሎጂ ወጣቱና የከተማዋ ትራፊክ ፅ/ቤት በጋር በመተባበር ሰርተዋል፡፡

ምንጭ፦ Arts Tv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ የጉራጌ #የክልል_መዋቅር ጥያቄ መርምሮ በሙሉ ድምጽ አፅድቋል።

ምንጭ፦ Gurage Zone Communication Affairs
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምክትል ጠ/ሚ አቶ #ደመቀ_መኮንን...

"ውድ ተማሪዎች . . . [ቢያንስ ቢያንስ] ለሃገር ክብር በጋራ እንደተዋደቁት፤ ለሃገር ልዕልና በጀግንነት እንደተዋጉት፤ ለሃገር አንድነት ዕድሜ ልካቸውን እንደደከሙት እንዲሁም ለእናት ሃገራቸው ሲሉ በቁርጠኝነት ለውጥ እንዳራመዱት. . .የቀደሙ አያቶቻችን እና አባቶቻችን እንድትሆኑ #እለምናችኋለሁ።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia