TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጠ/ሚ ዶክተር አብይ⬆️

ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር #አብይ_አህመድ በበርሊን ከተማ “G20 COMPACT WITH AFRICA” በተሰኘው ኮንፈረንስ ላይ ተሳተፉ።

ጀርመን የዓመቱ G20 ሰብሳቢነትዋ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለተመረጡ 11 የአፍሪካ አገሮች “COMPACT WITH AFRICA” በሚል በነደፈችው ፕሮግራም ላይ የተገኙት ቻንስለር መርከል የግል ኢንቨስትመንትን ማበረታታት የፈጣንና ቀጣይነት ያለው ዕድገት መሰረት መሆኑን አስምረውበታል።

ጠቅላይ ሚንስትር አብይም በኮንፈረንሱ ላይ ንግግር ያደረጉ ሲሆን: በኢትዮጵያ በቅርቡ ይፋ የተደረገውን የፕራይቬታይዜሽን ፖሊሲ ጨምሮ ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት እየተደረገ ያለውን ጥረት ገልጸው ጀርመንን ጨምሮ የG20 አገሮች ወደ አገራችን መጥተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ፕሮግራም ከተመረጡ የተመረጡ ን የጀርመኗ ቻንስለር በንግግር የከፈቱ ሲሆን ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድን ጨምሮ የ11 የአፍሪካ
አግእራት መሪዎች ንግግር አድርገዋል።

ምንጭ፦ አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠ/ሚ ዶክተር አብይ⬆️

ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር #አብይ_አህመድ በበርሊን ከተማ የኦስትሪያ የፌደራል ቻንስለር የሆኑትን ክቡር ሚ/ር ሰባስቲያን ኩርዝን አነጋገሩ::
ሁለቱ መሪዎች በሁለቱ አገሮች የጋራ ጉዳዮች ላይ የተወያዩ ሲሆን ቻንስለት ኩርዝ በቪየና ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ደግሞ በአዲስ አበባ ጉብኝት እንዲያደርጉና የሁለቱን አገሮች ግኑኝነት ወደላቀ ደረጃ ለማድርስ ሁለቱም መሪዎች የጉብኝቱን ግብዣ ተቀብለዋል።

ምንጭ፦ አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጀርመን ለምትገኙ‼️

በነገዉ እለት ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር #ዐብይ_አህመድ በፍራንክፉርት «ኮሜርስ አሬና» በተባለዉ ስቴዲየም ከኢትዮጵያዉያንና ትዉልድ ኢትዮጵያዊያን ጋር ይገናኛሉ። ተሳታፍዎቹ ከጀርመን ብቻ ሳይሆን ከተለያዩ የአዉሮጳ አገራት በዝግጅቱ ላይ ይታደማሉ። በዚህ ዝግጅት በግምት 25 ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐብይ እንደሚያቀርብ ይጠበቃል። ወደፊት የኢትዮጵያ ጉዞም ወሳኝ በአዉሮጳ ዉስጥ
በርካታ ኢትዮጵያዉያን ምሁራን እና የፖለቲካ አዋቂዎች በመኖራቸዉና አንድ አንዶች ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር ፊት ለፊት መወያየት ባለመቻላቸዉ ብዙዎችን አስኮርፎአል። የፓሪስ ፈረንሳይና የበርሊን ጀርመን ጉብኝት በዋናነት በሁለት አገሮች የሚደረግ መንግስታዊ ጉዳይ መሆኑን የፍራንክፉርት ጉብኝት አስተባባሪ ድያቆን ዳንኤል ክብረት ተናግረዋል። ይሁን እንጅ በነገ እለት በፍራንክፉርት ከኢትዮጵያዉያንና ትዉልድ ኢትዮጵያዊያን ጋር ለመገናኘት ተጨማሪ ቀን መያዙን ድያቆን ዳንኤል ገልፀዋል።

በነገዉ ሥነ-ስረዓት ላይ ታዳሚዎች ምን ማድረግ እንዳለባቸዉም እንደ #ማሳሳብያ የሚከተሉትን ነጥቦች ዝርዝረዋል፤

- የፍተሻዉን ጊዜ በጣም ለማሳጠር ትልልቅ ሻንጣዎችን ይዞ ከመምጣት ታዳሚዎች መቆጠብ ይኖርባቸዋል።

- ቀጠሮዉን አክብሮ በግዜ መገኘት አስፈላጊ ነዉ።

- ሕጻናትና ልጆችን የያዙ ቤተሴቦች የሕጻናት መቀመጫ ጋሪዎቻቸዉ የሚሆኑበት የተወሰነ ቦታ ተዘጋጅቶአል። ቦታዉ ግን ይህን ያህል ብዙ አይደለም።

- ከሕፃናት ምግብ በስተቀር ምግብ ይዞ ወደ ስታድዮም መግባት አይቻልም። በአንጻሩ ምግብ መጠጥ መሸጫ ቦታ በቂ ተዘጋጅቶአል።

ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ስም በህብረተሰቡ ላይ ስጋት የደቀኑ ታጣቂዎች እጃቸውን ሊሰበስቡ ይገባል ብለዋል የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ለማ ለገርሳ።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦነግ መግለጫ‼️

“ያለ አግባብ ለሚጠፋው የሰዉ ሕይወትና ንብረት ተጠያቂነት ልኖር ይገባል”

የኦሮሞ ነጻነት ግንባርና የኢትዮጵያ መንግስት ስምምነታችንንና በሕዝቡ ዉድ መስዋዕትነት የተግኘዉ የለዉጥ ሂደት በኣስተማማኝ መልኩ ስር በመስደድ ስኬታማ እንድሆን በማድረጉ ሂደት ላይ የሚሰራ ኣንድ የጋራ ኮሚቴ መስርተን እየተንቀሳቀስን እንገኛለን። በዚህ የጋራ ኮሚቴ አመካይነትም በቋሚነትና በቀጣይነት ተገናኝተን እየተመካከርን በመስራት ላይም እንገኛለን።

ይህንን ሂደት የሰዉ ሕይወት መስዋዕትነትን በማይጥይቅ መልኩ፣ በሀገርና በሕዝብ ንብረት ላይም ጉዳትን በማያስከትል ሁኔታ፣ እንድሁም፣ ያለምንም ጥድፍያና ወከባ ጊዜ ወስደን በመመካከርና በቀና መንፈስ አብረን በመስራት ማሳካት እንደሚቻል የድርጅታችን የኦነግ ጽኑዕ እምነታችንና ኣቋማችንም ነዉ።

ይሁን እንጂ በመንግስት ኣንዳንድ ኣካላትና ግለ-ሰቦች እንድሁም በኢሕአዴግ በቀጣይነት የሚካሄዱብን ኣፍራሽ ፕሮፓጋንዳዎችና ገደብ ያጡ ሸርና ደባዎች የሕዝቡንና የሀገርን ሰላም የሚጎዱ ስለመሆናቸዉ በግልጽ የሚታይ ሓቅ ነው። ስለሆነም እንደነዚህ ኣይነቶቹን ሸርና ደባዎች፣ እንድሁም ኣፍራሽ ፕሮፓጋንዳዎች በሚመለከታቸዉ ኣካላት ኣስፈላጊ ክትትልና ቁጥጥር ተደርጎባቸዉ ማስቆም እንደሚገባ እስከዛሬ ስናስገነዝብ ቆይተናል። ይህንን ያደረግነው ተስማምተን የገባንበትን የሰላምና የእርቅ ሂደት በስኬት ለማጠናቀቅ ይረዳ ዘንድ መሆኑን ማስገንዝብ እንወዳለን። ይህ ደግሞ ለሕዝብና ለሃገር ሰላምና ደህንነት በቅንነት ከማሰብም እንደሆነ ልታወቅ ይገባል።

ይህ በንድህ እንዳለ ምክንያቱን በትክክል ለመረዳት አዳጋችና አስቸጋሪ በሆነብን ሁኔታ የኢትዮጵያ መንግስት ሃገር በጠላት የተወረረች ይመስል ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ የጦር ሠራዊቱን በሕዝባችን ላይ በማዝመት ሰላማዊ ሰዎችን መግደልና የሰዎችን ንብረት መዝረፍ ዛሬም ድረስ ቀጥሎበታል። ካለፉት ሁለት ቀናት ጀምሮ በቄሌም ወለጋና በጉጂ ዞን ኣከባቢዎች እየተፈጸሙ ያሉት ሁኔታዎች ለዚህ ጉልህ ማስረጃ ናቸዉ። ይህ ሁኔታ ደግሞ ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖር፣ ክቡር የሰዉ ህይወት ያለ ኣግባብ እንድጠፋ፣ እንድሁም የሕዝብና የሃገር ንብረት እንድወድም፣ ኣልፎ ተርፎም ሕዝቡ በስጋት፣ በጥርጣሬና በፍርሃት ድባብ ስር እንድኖር እያደረገ ይገኛል።

ኣሁን ባለዉ ሁኔታ በጦርነትና በሓይል መፍትሔ ልገኝለት የሚችል ችግር እንደሌሌና ለሕዝብም ሆነ ለሃገር ከጦርነት የሚገኝ ትርፍ ወይም ጥቅም እንደሌሌ ኦነግ በጽኑዕ ያምናል። በሕዝቡ ትግልና መስዋዕትነት በተግኘዉ የለዉጥ ሁኔታ ላይ እንቅፋት ልሆንና የሕዝቡን ተስፋ ልያጨልም የሚችል ይህ ኣሳዛኝ ኣካሄድ በኣስቸኳይ እንድቆምም እንጠይቃለን። ይህ ኣካሄድ በሚያስከትለዉ ኣደጋ ለሚደርስ የሰዉ ህይወት መጥፋት፣ እንድሁም በሕዝብና በሃገር ንብረት ላይ ለምደርስ ዉድመት ሃላፊነት/ተጠያቂነት ልኖር እንደሚገባም ኦነግ ኣጥብቆ ያሳስባል።

ድል ለኦሮሞ ሕዝብ !

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር
ጥቅምት 30, 2018

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጀግኒት አለመች፣ አቀደች፣ እሳካች‼️

“ጀግኒት አለመች፣አቀደች አሳካች” በሚል መሪ ቃል የሚከናወነውን ሀገራዊ የህብረተሰብ #ንቅናቄ ዝግጅትን አስመልክቶ ዘጠኙ ሴት ሚኒስትሮችና የሁለቱ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤና ምክትል አፈ ጉባኤ በተገኙበት ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።

ከሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ሴቶች የሚሳተፉበት ሀገር አቀፍ የሴቶች #የሰላም_ኮንፈረንስ የፊታችን ጥቅምት 26 ቀን 2011 ዓመተ ምህረት እንደሚካሄድም ተገልጿል።

በመግለጫው ላይ ንግግር ያደረጉት የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር ወይዘሮ ያለም ፀጋይ ፥ ኮንፈረንሱ በሀገሪቱ ውስጥ ዘላቂ ሰላም በማረጋገጥ፤ የሴቶችና ህፃናትን የአደጋ ተጋላጭነት በመቀነስ መብትና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ እና ሴቶች ሰላም መከበር ያላቸውን አበርክቶ ለማሳደግ ነው ብለዋል።

እንዲሁም የሴቶችና ህፃናትን ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ በየአከባቢው ሴቶች ለሰላማቸው ጠንክረው እንዲሰሩ ለማድረግም ነው ብለዋል።

ንቅናቄው በሀገሪቱ የሴቶችን ጥንካሬ ከተተኪነት በላይ ራሳቸው ለተሻለ ነገር የሚያበቁ እና ብቁ ትውልድ የሚያፈሩ መሆናቸውን ለማሳየት ያስችላል ተብሏል።

በአሁን ሰዓት ሴቶች በሀገሪቱ ልማትና እድገት ላይ በየደረጃው እየተወጡ ያለው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በማሳወቅና በማሳየት ክብርና እውቅና ማግኘት እንዲችሉ ያደርጋል ነው የተባለው።

ከንቅናቄው በኋላ የሴቶች የልማት ጥምረት ይመሰረታል የተባለ ሲሆን፥ ይህም በሴቶችና ህፃናት ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ አካላት ለማጠናከር፣ በዘላቂ ሰላም ማረጋግጥና ሴቶች በልማቱ ያላቸው ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ዙሪያ የራሱ ድርሻ እንደሚኖረው ተጠቁሟል።

ሀገሪቱ ዴሞክራሲ እንዲሰፍንና በሀገሪቱ የተጀመረውን ለውጥ ለማፋጠንም ንቅናቄው አስተዋፅኦው የጎላ ይሆናል ተብሏል።

በኮንፈረንሱ ለሚኒስትሮቹ አሁን ያለውን የሚኒስትሮች ቁጥር ለማስቀጠል ምን ታስቧል ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል፥ ብዙ አቅም ያላቸው ሴቶች እንዳሉና ንቅናቄው እስከ ወረዳ ድረስ የሚካሄድ በመሆኑ አቅም ያላቸውን ሴቶች ወደ ከፍተኛ የስልጣን እርከኖች ማምጣት ይቻላል ብለዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
#update ሰሞኑን በምዕራቡ የኦሮሚያ ክፍል ዋና መንገዶችን ጭምር #የዘጋ እና እንቅስቃሴን #የገደበ የተቋውሞ ሰልፍ ተደርጓል፡፡ ሰልፈኞቹ መንግሥት ኦነግን በኃይል ለመማስፈታት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ እንቃወማለን ብለዋል፡፡

ኦነግ በበኩሉ በሥምምነቱ ሒደት ላይ እየሰራ መሆኑኑን ገለፆ፣ መንግሥት ለምን በመሃል ጦር እንዳሰማራ አልገባንም ብሏል፡፡

ምንጭ፦ VOA አማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia