TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዛሬ ጀምሮ ወደ ሩሲያ ርዕሰ ከተማ ሞስኮ #የቀጥታ በረራ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ #ተወልደ_ገብረማሪያም በቆዳ ስፋቷ የአለም ግዙፍ ሀገር ወደ ሆነችው ሩሲያ የሚጀመረው የበረራ ዝግጅት መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡ አዲሱ የቀጥታ በረራ አገልግሎትም እጅግ ዘመናዊ በሆነው 787 ድሪምላይነር አውሮፕላን በሳምንት ለሶስት ቀናት እንደሚሰጥ ጠቁመዋል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

የኦነግ መሪዎች እና የኢፌዴሪ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት #ድርድር እና #ውይይት እያካሄዱ ነው። በምዕራብ ኦሮሚያ የተፈጠረው ችግር በአጭር ጊዜ ውስጥ #መፍትሔ እንደሚያገኝ ሁለቱም ወገኖች ቃል ገብተዋል። ውይይቱ የሚካሄደው በዝግ ስብሰባ ሲሆን ከውይይቱ ማብቃት በኋላ ለህብረተሰቡ #መግለጫ ይሰጣል ተብሏል።

ምንጭ፦ Afendi Muteki
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ፕሬዚዳንት #ሳህለወርቅ ወደ ደቡብ ሱዳን አቀኑ። ፕሬዘደንቷ ወደ ደቡብ ሱዳን ያቀኑት ባለፈው መስከረም በአዲስ አበባ የተፈረመውን የደቡብ ሱዳን የሰላም #ስምምነት ለማብሰር በተዘጋጀው ስነስርዓት ላይ ለመሳተፍ ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐቢይ_አህመድ ከአለም ባንኩ ፕሬዝዳንት #ጂም_ዮንግ_ኪም ጋር በጀርመን መከሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጀርመን በርሊን ከተካሄደው የቡድን 20 አባል አገራት ስብሰባ የጎንዮሽ ግንኙነት ነው ከአለም ባንኩ ፕሬዝዳንቱ የተወያዩት፡፡ የአለም ባንክ ለኢትዮጵያ ልማት በተለያየ መልኩ ድጋፎችን የሚያደርግ ተቋም መሆኑ ይታወቃል፡፡

ምንጭ፡- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ​ዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ድጋፍና ብድር አጸደቀ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከ379 ሚሊዮን ብር በላይ የግብርና ታክስ ውዝፍ ዕዳ ያለባቸው የ18 ግብር ከፋዮች 10 ቤትና ዘጠኝ ተሽከርካሪዎችን በመሸጥ ለመንግስት ገቢ ለማድረግ #እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የአዲስ አበባ ገቢዎች ባለስልጣን አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፍራንክፈርት⬆️ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የጀርመን ጉብኝታቸውን በመቀጠል ፍራንክፈርት ገብተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፍራንክፈርት "አንድ ሆነን እንስራ ነገን እንገንባ" በሚል መርህ የተዘጋጀው መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው ከኢትዮጵያውያን ጋር ይወያያሉ፡፡ በዝግጅቱ ላይ ከመላው አውሮፓ የተውጣጡ ከ20 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፦ etv ብሩክ ያሬድ (ከጀርመን ፍራንክፈርት)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቀጥታ ስርጭት! በአሁን ሰዓት በጀርመን ፍራንክፈርት እየተደረገ የሚገኘውን ዝግጅት በተለያዩ የሀገር ውስጥ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች መከታተል ትችላላችሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የማህበራዊ ሚድያ ህግ በቬትናም‼️

ቬትናም የማህበራዊ ሚዲያዎችን አጠቃቀም የሚቆጣጠር የሳይበር ሕግ #ልታፀድቅ መሆኑን የሀገሪቱ የደህንነት ሚኒስትር አስታውቋል።

ይህ የሳይበር ሕግም በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚለቀቁ #ሀሰተኛ መረጃዎችን ፣የሽብር ድርጊቶችንና መሰል ተግባራትን ለመቆጣጠር ያስችላል ተብሏል።

ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች በሀገራቸው ያለውን የስራ ፈጠራ ሁኔታን ከማበረታታት ይልቅ ሀገራቸውን የደህንነት ስጋት ውስጥ እየከተቱ በመሆኑ ፥ድርጊቱን ለመከላከልም የሳይበር ህግ ማውጣት ተገቢ መሆኑን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

የሀገሪቱ ህግ አውጪ አካላት በበኩላቸው፥ በማህበራዊ ሚዲያዎች በተለይም በፌስብክና ጎግል አይነት መተግበሪያዎች ላይ ከፍተኛ
የሆነ የአጠቃቀም ህግ ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ማህበራዊ ሚዲያዎችን ተጠቅመው የሀገሪቱን መንግስተና ዜጎች መረጃ የሚመዘብሩ አካላትን ለመቆጣጠርም የሳይበር ሕጉ ሁነኛ #መፍተሄ ነው ተብሏል።

ሰለሆነም የሀገሪቱን የሳይበር ደህንነት ለማስጠበቅ የሳይበር ሕጉ በሚቀጥለቀው ዓመት ተግባራዊ እንደሚሆን ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

ይህ ህግም በቬትናም በስፋት አግልግሎት ላይ የዋሉት ፌስቡክና ጎግል በሀገር ውስጥ ተጠሪ መስሪያ ቤት እንዲከፍቱ የሚያስገድድ ነው።

ከዚህ በተጨማሪም ድርጅቶቹ የተጠቃሚዎችን መረጃ በተገቢ ሁኔታ የማስቀመጥና አላስፈላጊ መረጃዎችን የማስወገድ ሃላፊነትም ይሰጣቸዋል ነው የተባለው።

የሳይበር ሕጉ ዜጎች የማህበራዊ ሚዲያን እንዳይጠቀሙ የሚያግድ ሳይሆን ህጉንና ደንቡን ተከትለው በስርዓት እንዲጠቀሙ የሚያስችል ነው ተብሏል።

ምንጭ፦reuters.com
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በድጋሚ ትኩረት ለቴፒ‼️

የክልሉ መንግስት እንዲሁም የፌደራሉ መንግስት በቴፒ ያለውን ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጠው ለTIKVAH-ETH የተላኩ መልዕክቶች ያስረዳሉ። ሁኔታዎችን አሁን ካሉበት ወደሌላ ደረጃ ሳይሸጋገሩ መንግስት መፍትሄ ሊያበጅ እንደሚገባ ተጠቁሟል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀሰት ነው‼️አቶ ተወልደ ገብረማርያም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ #አልተባረሩም ስራ ላይ ናቸው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia