TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57.1K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#USA #ETHIOPIA

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ዛሬ ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር በስልክ መምከራቸውን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።

ውይይቱ የነበረው በሰሜን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በሚደረገው ጥረት ዙሪያ እንደነበር ተገልጿል።

አንቶኒ ብሊንከን ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል እና በጎራባቹ አፋር እና አማራ ክልሎች ያለውን ያልተገደበ የሰብአዊ ድጋፍ እና መሰረታዊ አገልግሎቶችን ወደ ነበረበት ለመመለስ እየሰራ ያለውን ጥረት እውቅና መስጠታቸው ተመላክቷል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፤ የውጭ ኃይሎችን ከትግራይ ምድር ማስወጣትና አብሮም የትግራይ ኃይሎችን ትጥቅ ማስፈታት የሚለው ጨምሮ የፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት በአስቸኳይ ተግባራዊ ማድረግን እንዳሰመሩበት ተሰምቷል።

ብሊንከን ፤ ሀገራቸው አሜሪካ የአፍሪካ ህብረት የስምምነት አፈፃፀም የክትትል እና ማረጋገጫ ዘዴን ጨምሮ በአጠቃላይ ህብረቱ የሚመራውን ሂደት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል።

በደቡብ አፍሪካ ፤ ' ፕሪቶሪያ ' በዘላቂነት ግጭት እንዲቆም የተፈረመው ስምምነትን ለማስፈፀም በኬንያ ኖይሮቢ በተፈረመው ስነድ ፤ የትግራይ ኃይሎች የከባድ መሳሪያ ትጥቅ አፈታት የውጭ ኃይሎችና ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ውጭ ያሉ ኃይሎች ከክልሉ መውጣት ጋር በአንድ ግዜ እንደሚፈፀም ይገልጻል።

@tikvahethiopia
#BekeleGerba #USA🇺🇸

አቶ በቀለ ገርባ በአሜሪካ ሀገር #ጥገኝነት መጠየቃቸውን አሳወቁ።

ለረዥም ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በግል እና በፓርቲ ደረጃ ተሳታፊ የነበሩት የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ፓርቲ ተቀዳመ ምክትል ፕሬዜዳንት አቶ በቀለ ገርባ በፓርቲያቸው የነበራቸውን ተሳትፎ አብቅተው በአሜሪካ ጥገኝነት መጠየቃቸውን ለቢቢሲ አማርኛ ክፍል ተናገሩ።

አቶ በቀለ ፤ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ " በሰላማዊ መንገድ ለመታገልም ሆነ በግል በነጻነት መኖር " አሳሳቢ በመሆኑ በሄዱበት አሜሪካ ጥገኝነት መጠየቃቸውን ገልጸዋል።

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል የሆኑት አቶ በቀለ፣ በውጭ አገር ሆነው ሥልጣኑን ይዘው መቀጠጣለቸው ጠቃሚ ስላልሆነ እራሳቸውን ከፓርቲው ለማግለል መወሰናቸውን ተናግረዋል።

አቶ በቀለ ገርባ ፤ ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ ተፈጥሮ የነበረውን ሁከት ተከትሎ በቁጥጥር ሥር ውለው ለ18 ወራት በእስር ላይ ቆይተው ከተለቀቁ በኋላ ወደ አሜሪካ ተጉዘዋል። አሜሪካ ከሄዱ 1 ዓመት ከሶስት ወር ሆኗቸዋል።

አቶ በቀለ ከእስር ከወጡ በኋላ ወደ አሜሪካ ሲጓዙ ዓላማቸው የእርሳቸውን ከእስር መለቀቅ ሲጠይቅ ለነበረው የዳያስፖራ ማኅብረሰብ ምስጋና ለማቅረብ ነበር።

ነገር ግን አሜሪካ በቆዩባቸው ያለፉት 15 ወራት በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ በመቀየሩ " ወደዚያ አገር መመለሱ አስፈላጊ መስሎ አልታየኝም "  በማለት እዛው ጥገኝነት መጠየቃቸውን እና ከፓርቲው ኃላፊነትም እራሳቸውን ማግለላቸውን ለቢቢ አማርኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል ገልጸዋል።

More - https://telegra.ph/BBC-08-28-2

@tikvahethiopia
#USA

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሐመር ከነሐሴ 22 እስከ ጳጉሜ 3 ድረስ በኬንያ  እና በኢትዮጵያ ቆይታ እንደሚያደርጉ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።

በናይኖቢ እንዲሁም በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከሀገራቱ ባለስልጣናት፣ ከአፍሪካ ህብረት፣ ከልማት ድርጅት ባለስልጣን እና ሌሎች ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር ይነጋገራሉ ተብሏል።

ሐመር በአዲስ አበባ በሚያደርጉት ቆይታ፣ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ያሉትን ግጭቶች በድርድር እንዲቋጩ እና ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት እንዳይደርስ እና ከለላ እንዲያገኙ ግፊት ያደርጋሉ ተብሏል።

ሐመር፣ በሱዳን ቀውስ እና ጦርነቱን ለማስቆም እየተደረጉ በሚገኙ ቀጠናዊና ዓለማቀፋዊ ጥረቶች ላይም ከአካባቢዉ አገራት፤ ከአፍሪቃ ኅብረትና ከኢጋድ መሪዎች ጋር እንደሚመክሩ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ገልጿል።

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመድ ከዚህ ቀደም በተለይም በትግራይ ከነስቶ ወደ አፋር እና አማራ ክልል የተስፋፋውን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲበጅለት በተደጋጋሚ ወደ ኢትዮጵያ እና ጎረቤት ሀገራት መምጣታቸው የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA #USA

ዓለም አቀፍ ለጋሾች ያቆሙት የምግብ ርዳታ ይቀጥል ዘንድ በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና በአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን መካከል የስልክ ውይይት ተደረገ።

የሚኒስቴር መ/ቤቱ ቃል አቀባይ ማት ሚለር እንዳሳወቁት ብሊንከን ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር የስልክ ውይይት አድርገዋል።

በዚህ ውይይት ወቅትም ፤ ዓለም አቀፍ ለጋሾች ያቆሙት የምግብ ርዳታ ይቀጥል ዘንድ ፣ የሰብአዊ ሁኔታ ቁጥጥር ተሻሽሎ ስለሚቀጥልበት አሠራር ላይ ተወያይተዋል።

በተጨማሪ አንተኒ ብሊንከን፣ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል ያለው ሁኔታ " አሳስቦኛል "  ሲሉ ተናግረዋል።

በሁለቱ ክልሎቹ ያሉትን ችግሮች #በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት፣ የፖለቲካ ውይይትንና የሰብአዊ መብቶች መከበር አስፈላጊነትን አጽንዖት ሰጥተውበታል።

እውነተኛ ፣ ታማኝ እና ሁሉን አካታች የሽግግር ፍትሕ ሒደትን ለመፍጠር እየተከናወነ ያለውን ሥራ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመልካም እንደተቀበሉት ተጠቁሟል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከንና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ፣ በአፍሪካ ቀንድ ስለሚታየው የጸጥታ ተግዳሮት፣ እንዲሁም አንዲት፣ ሰላማዊት እና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለማየት ያላቸውን የጋራ ግብ አስመልክቶም እንደተወያዩ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤትን ዋቢ በማድረግ ቪኦኤ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#USA #Israel

የአሜሪካው ፕሬዜዳንት #ጆ_ባይደን እስራኤል ገብተዋል።

ባይደን በእስራኤል ቆያታቸው ጦርነቱ ከዚህም በላይ ከፍቶ እንዳይስፋፋ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ያደርጋሉ ተብሏል።

የአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት ቃል አቀባይ ፕሬዝዳንት ባይደን የቀጠለውን ጦርነት #ዓላማን በተመለከተ ለኔታንያሁ ከበድ ያሉ ጥያቄዎችን እንደሚጠይቋቸው ገልጸዋል።

ባይደን በቅድሚያ ይሄዳሉ ተብሎ የነበረው ወደ ዮርዳኖስ ነበር።

በዛም ከአረብ ሀገራት መሪዎች ጋር ይመክራሉ ተብሎ ነበር። ነገር ግን ከአሜሪካ ከተነሱ በኃላ የአረብ ሀገራት መሪዎች ከባይደን ጋር እንደማይገናኙ እና የነበረውም ስብሰባ መሰረዙ ተሰምቷል።

አሜሪካም ፕሬዜዳንቷ ወደ ዮርዳኖስ እንደማይሄዱና ይህም " የጋራ ውሳኔ " መሆኑን ገልጻለች።

" በእናተ አልተፈፀመም " - ባይደን

ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን እስራኤል በሆስፒታሉ ላይ ጥቃት አልፈፀመችም ብለዋል።

እስራኤል የሚገኙት ጆ ባይደን በጋዛ በሚገኘው " አል አህሊ ባፕቲስት ሆስፒታል " ላይ ፍንዳታ የተፈፀመው በእስራኤል ሳይሆን " በሌላኛው ቡድን " ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ባይደን ለእስራኤሉ ጠ/ሚ ኔታንያሁ ፤ " ትናንትና በጋዛ ሆስፒታል በደረሰው ፍንዳታ በጣም አዝኛለሁ " ያሉ ሲሆን " ባየሁት መሰረት፣ የተደረገው በሌላው ቡድን ይመስላል ፤ እንጂ በአንተ (እስራኤል) አይደለም " ሲሉ ተናግረዋል።

እስራኤል ፤ በሆስፒታሉ ላይ ለደረሰው ጥቃት ያልተሳካ " የኢስላሚክ ጂሃድ " ቡድን ሮኬት ነው ያለች ሲሆን " ሃማስ " እንዲሁም " የፍልስጤም ኢስላሚክ ጂሃድ " ድርጅት ጥቃቱ የተፈፀመው በእስራኤል ነው ብለዋል።

" የፍልስጤም ኢስላሚክ ጂሃድ " የእስራኤል ክስ ሀሰተኛ እና ምንም መሰረት የሌለው እንዲሁም ከጭፍጨፋው ተጠያቂነት ለማምለጥ ጣቷን በእስላሚክ ጂሃድ እና ፍልስጤማውያን ላይ የጠቆመችበት የተለመደ የሀሰት እና ቅጥፈት ፈጠራዋ ነው ብሏ

More + @BirlikEthiopia
#USA

" ፕሬዜዳንት በሆንን በአንድ ሳምንት ውስጥ ቲክቶክን እናግዳለን " ያለቱ የሪፐብሊካን እጩዎች !

የአሜሪካ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ በ2024 ይካሄዳል።

የሪፐብሊካን የፕሬዜዳንታዊ እጩዎች ቢሮ በገቡ በመጀመሪያው ሳምንት " #ቲክቶክ " የተሰኘውን መተግበሪያ እንደሚያግዱ ገልጸዋል።

እጩዎቹ ሰሞኑን በነበረ ክርክር መድረክ ላይ ነው ይህን የገለፁት።

እጩዎች የቻይናን መረጃ መሰብሰብን ለመዋጋት አንዴ ፕሬዜዳንት ሆነው ወደ ነጩ ቤተመንግስት ይግቡ እንጂ " ቲክቶክ" ን እስከወዲያኛው እንደሚያግዱት ገልጸዋል።

ክሪስ ክርስቲ የተባሉ የሪፐብሊካን እጩ ምን አሉ ?

እኚህ እጩ " ቲክቶክ " መረጃዎችን ከመሰብሰብ ባለፈ በመላው ሀገሪቱ ውስጥ ያሉ የወጣት አሜሪካውያንን አእምሮ እየበከለ ነው ብለዋል። " ይህንን የሚያደርጉት ደግሞ ሆን ብለው ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

" ቲክቶክ " በአልጎሪዝሙ አሰቃቂ፣ ያልተገቡ፣ ከፋፋይ፣ አፍራሽ ፣ የወጣቶችን አእምሮ የሚበክሉ ጉዳዮችን ከፍተኛ ደረጃ ወደ ተጠቃሚው እንዲገፋ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

ይህም ቻይና አሜሪካንን ለመከፋፈል ይበልጥ እየተጠቀመችበት ያለ ተግባር ነው ሲሉ ከሰዋል።

የሪፐብሊካኑ ሰው የቀድሞው ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ በስልጣን ዘመናቸው " ቲክቶክን ማገድ " በተመለከት ብዙ ሲናገሩ እንደነበር ነገር ግን መተግበሪያውን ማገድ ሲገባቸው ያን አለማድረጋቸው የሚያስወቅስ እንደሆነ ገልጸዋል።

እሳቸው ፕሬዜዳንት ሆነው በመጡ በመጀመሪያው ሳምንት ቲክቶክን እንደሚያግዱ አሳውቀዋል።

ሮን ዴሳንቲስ የተባሉ እጩ ደግሞ " የአሜሪካን ህዝብ ለመጠበቅ ስንል ቲክቶክን የማገድ እርምጃ እናሳያችኃለን " ብለዋል። ፕሬዜዳንት ሆነው ሲመጡም ይህንን እንደሚያደርጉትን ገልጸዋል።

ቲም ስኮት የተባሉት እጩ ፤ " እኛ ማድረግ ያለብን ቲክቶክን ማገድ ነው ፤ አለቀ !! " ብለዋል።

በቀድሞው ፕሬዝደንት ትራምፕ ቲክቶክን ለማገድ ሁለት ጊዜ ሲሞከር አይተናል ያለቱ ስኮት ፤ ነገርግን በፌደራል ፍርድ ቤቶቻችን እንዳይፈፀም ተደርጓል ሲል አስታውሰዋል።

ቲክቶክን ማገድ ካልተቻለ በመተግበሪያው ላይ ያለውን የቻይናን ተፅእኖ መኖር እንደወዲያኛው #ማስወገድ ነው ብለዋል።

ባይትዳንስ የተሰኘው ኩባንያ ንብረት የሆነው " ቲክቶክ " ከዚህ ቀደም በተለይም ግላዊ መረጃን በመበዝበዝ እና ከቻይና መንግሥት ጋር የተቆራኘ ነው በሚል ከፍተኛ ወቀሳ ሲደርስበት ነበር ፤ ኩባንያው የቻይና መንግሥት መረጃውን እንደማያገኝበትና ቻይና ያለው ቲክቶክ ከሌላው ዓለም ፈፅሞ የተለየ መሆኑን ደጋግሞ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቲክቶክ ለምንድነው ሀገራት " ቲክቶክ " ን ለማገድ እየተንቀሳቀሱ ያሉት ? ከቅርብ ወራት ወዲህ አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ ካናዳ ያሉ የህግ አውጪዎች ከፀጥታ እና ደህንነት ስጋት ጋር በማያያዝ ግዙፉን የአጫጭር ቪድዮዎች ማጋሪያ " ቲክቶክ " ን ለማገድ / ለመገደብ የሚያደርጉትን ጥረት ማጠናከራቸውን ኒውዮርክ ታይምስ አስነብቧል። ዋይትሃውስ እኤአ በፌብሩዋሪ 27 የፌዴራል  ኤጀንሲዎች አፕሊኬሽኑን ከመንግሥት…
#USA #TikTok

" ወጣቶችን ቲክቶክ እንዳይጠቀሙ የሚገድብ ረቂቅ ህግ እንደሚወጣ አሳውቃለሁ ... አለቀ !! " - ግሌን ያንግኪን

በአሜሪካ የቨርጂኒያ ግዛት ገዥ ግሌን ያንግኪን ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ሰዎች " ቲክቶክ "ን እንዳይጠቀሙ የሚገድብ ረቂቅ ህግ እንደሚወጣ አሳወቁ።

ያንግኪን ፤ " ቲክቶክ " የማህበራዊ ሚዲያ መድረክ ለህጻናት ልጆቻችን አእምሮአዊ ጤንነት እጅግ ጎጂ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የሪፐብሊካኑ ሰው ወደዚህ እርምጃ እንደሚመጡ ያሳወቁት ባለፈው አመት ቲክቶክን ከማንኛውም የመንግስት ኤሌክትሪክ መሳሪያዎች እና ዋይፋይ #ካገዱ በኋላ ነው።

ያንግኪን ፤ በአጠቃላይ ማህበራዊ ሚዲያ በልጆቻችን ላይ ከባድ እና ቀጣይነት ያለው አሉታዊ ተጽእኖዎች እያሳደረ ነው ብለዋል።

ከነዚህም ውስጥ ፦
- የማህበራዊ ክህሎታቸው እንዲያጡ ፣
- በሳይበር አማካኝነት የማዋረድ፣ ስድብና ሌላም ጎጂ ድርጊት እንዲደርስ፤
- የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር እንዲስፋፋ አሉታዊ ተፅእኖ እያሳደረ መሆኑ አመላክተዋል።

በመሆኑም " ወጣቶችን ቲክቶክ እንዳጠቀሙ የሚገድብ ረቂቅ ህግ እንደሚወጣ አሳውቃለሁ ... አለቀ !! " ሲሉ ገልጸዋል።

" ቲክቶክ " ን ልጆች እንዳይጠቀሙ ከሚያግደው ረቂቅ በተጨማሪ ልጆች ከማህበራዊ ሚዲያ ግብይት እና መረጃዎቻቸውን ከመጠቀም እና ከመሸጥ የሚከላከሉ ህጎች እንደሚያወጡ ገልጸዋል።

የቨርጂንያው ገዥ " ሱስ አስያዥ " ብለው ከጠሯቸው የማህበራዊ ሚዲያ የማርኬቲንግ ስልቶች ልጆችን እና ታዳጊዎችን ለመጠበቅ የሚረዱ ረቂቆችን ይፋ እንደሚያደርጉ የተናገሩ ቢሆንም " መቼ ? " የሚለውን አልገለፁም።

በአሜሪካ እንደ አጠቃላይ እስካሁን " ቲክቶክ " ባይታግደም፤ እንቅስቃሴዎች ስለመኖራቸው ግን ተደጋጋሞ ተነግሯል።

በተለይም በርካታ የሪፐብሊካን ዕጩዎች በቀጣይ ምርጫ አሸንፈው ፕሬዜዳንት መሆን ከቻሉ በአጭር ጊዜ መተግበሪያውን ለማገድ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በተለያዩ ግዛቶች ደግሞ ከደህንነት እንዲሁም ወጣቶችን ከመጠበቅ ጋር በተያያዘ " ቲክቶክ " ከመንግሥት የኤሌክትሪክስ መሳሪያዎች ፣ ከዩኒቨርሲቲዎች፣ ኮሌጅ ካምፓሶች ዋይፋይ እንዲታገድ ተደርጓል።

" ቲክቶክ " ባለቤት የሆነው የቻይናው ባይትዳንስ ኩባንያ በተለያየ ጊዜ የሚነሳበትን ወቀሳ ውድቅ ሲያደርግ መቆየቱ እየሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
#USA #Election

" ስደተኞች የሀገራችንን ደም እየበከሉ ነው " - ዶናልድ ትራምፕ

ሪፐብሊካንን በመወከል ለፕሬዝዳንትነት የሚወዳደሩት ዶናልድ ትራምፕ ስደተኞች " የሀገራችንን ደም እየበከሉ ነው " በማለት ተናገሩ።

ትራምፕ ይህ ያሉት #ከሜክሲኮ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች በሚገቡበት " ኒው ሃምሻየር " ግዛት ባደረጉት የምርጫ ቅስቀሳ ላይ ነው።

ትራምፕ ለ4 አመት የስልጣን ዘመን በድጋሚ የሚመረጡ ከሆነ ህገወጥ ስደትን እንደሚያስቆሙ እና በህጋዊ ሰደተኞች ላይ ደግሞ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርጉ ተናገረዋል።

ትራምፕ ለደጋፊዎቻቸው ስደተኞች ከደቡብ አሜሪካ በተጨማሪ #ከአፍሪካ፣ ከእስያ እየመጡ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

" ከሁሉም የዓለም ክፍል ወደ ሀገራችን የፈሰሱ ነው " ሲሉ አክለዋል።

ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው መስከረም ወር " ናሽናል ፐልስ " ከተባለው የቀኝ ዘመም ዌብሳይት ባደረጉት ቃለ ምልልስ ስደተኞች " ደማችንን እየበከሉት ነው " የሚል ተመሳሳይ ንግግር አሰምተው ነበር።

በወቅቱ ይህ የትራምፕ ንግግር " ዘረኝነት እና ጥላቻ " የሚያንጸባርቅ ነው የሚል ትችት አስነስቶ ነበር።

የያሌ ፕሮፌሰር እና በዘረኝነት ጉዳይ መጸሀፍ ያሳተሙት ጆናታን ስታንሊ ትራምፕ ቋንቋውን አሁንም ደግመው መጠቀማቸው አደገኛ ነው ብለዋል።

ፕሮሬሰሩ እንደተናገሩት ትራምፕ " የጀርመኖች ደም በጅዊሾች እየተበከለ ነው " የሚለውን የሂትለር ንግግር ያስተጋባ ነው ሲሉ ተችተውታል።

ስታሊ" ትራሞፕ ይህ ቃል በሁሉም የድጋፍ ሰልፎች ላይ እየደገሙት ነው። አደገኛ  የሆኑ ንግግሮችን መደጋገም እንዲለመዱ ያደረጋል " ብለዋል።

ፕሮፌሰሩ እንደተናገሩት ይህ በአሜሪካ የሚኖሩ ስደተኞችን ስጋት ላይ እንዲወድቁ ያደርጋል።

ባለፈው ጥቅምት ወር የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ቃል አቀባይ ስቴቨን ቹንግ እንዲህ አይነት ቃላት በመጽሀፍ፣ በዜና እና በቴሌቪዥን የተለመድ ናቸው በማለት በትራምፕ የቀረበውን ትችት " ትርጉም የለሽ " ሲሉ አጣጥለውት ነበር።

Credit - AL AIN News

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#IGAD ዛሬ በኡጋንዳ፣ ኢንቴቤ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት (ኢጋድ) መሪዎች ስብሰባ ይደረጋል። ስብሰባው ትኩረት ከሚያደርግባቸው ጉዳዮች አንዱ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረው ውጥረት ነው። ሌላው የሱዳን ጦርነት ነው። ለኢጋድ የመሪዎች ስብሰባ እስካሁን ድረስ በታወቀው ፦ የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር የጅቡቲው ፕሬዜደንት ኢሳሜል ኦማር ጌሌህ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት…
#USA #IGAD

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ካምፓላ እና አዲስ አበባን ይጎበኛሉ ተብሏል።

ማይክ ሐመር መጀመሪያ ካምፓላ ገብተው በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ እንዲሁም በሱዳን ጦርነት ላይ በሚመክረው የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) መሪዎች ስብሰባ ላይ ይሳተፋሉ።

ከዛም ወደ ኢትዮጵያ፣ አዲስ አባባ ይመጣሉ።

ልዩ መልዕክተኛው በአዲስ አበባ ቆይታቸው፦

" - ከኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በተለይ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ስላለው ግጭት ውይይት ያደርጋሉ።

- በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ያሉትን ግጭቶች አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ይወያያሉ።

- ሰላማዊ ሰዎች እንዲጠበቁ እንዲሁም ሰብዓዊ መብት እንዲከበር ጥሪ ያቀርባሉ።

- ከአንድ ዓመት በፊት በስምምነት የተቋጨውን የትግራይ ጦርነት ተከትሎ የሚከናወነውን ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታት፣ ተሃድሶ እና ማሰናበትን በተመለከተ እንዲሁም ተጎጂዎችን መሠረት ስላደረገው የሽግግር ፍትህ ሂደት ይወያያወሉ። " ሲል የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አሳውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ቢቢሲ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤትን ዋቢ አደርጎ ካሰራጨው ዘገባ ነው የወሰደው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EHRC የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በአማራ ከልል ምዕራብ ጎጃም ዞን መርዓዊ ከተማ በ20/05/2016 ዓ.ም በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እና በታጣቂ ቡድኖች መካከል በነበረ ግጭት ከፍተኛ የሆኑ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች መፈጸማቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች እንደደረሱት ባወጣው መግለጫ አሳውቋል። በእዚህ ግጭት ምክንያት በመርዓዊ ከተማ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ እንደነበር…
#USA #ETHIOPIA #MERAWI

በአማራ ክልል መርዓዊ ከተማ ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ በማድረግ ግድያ የፈጸሙ ላይ ምርመራ ተደርጎ ለፍርድ እንዲቀርቡ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጠየቁ።

አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ በኤምባሲው የX ገጽ ላይ ባወጡት መልዕክት በመርዓዊ ከተማ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ በሚመለከት የወጡ ሪፖርቶች የአሜሪካ መንግሥትን እንደሚያሳስበው ገልጸዋል።

አምባሳደር ማሲንጋ፣ የክስተቱን አሳሳቢነት ከመግለጻቸው ባሻገር " የግድያውን ፈጻሚዎች ለሕግ ለማቅረብ " ገለልተኛ የሰብዓዊ መብት ተቆጣጣሪዎች ምንም ገደብ ሳይደረግባቸው ወደ ሥፍራው እንዲንቀሳቀሱ እንዲፈቀድላቸው እንዲሁም በግድያው ዙሪያ ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

በአገሪቱ ባሉት የአማራ እና የኦሮሚያ ክልሎችን ጨምሮ በሌሎችም ቦታዎች ላይ " በመንግሥት እና ከመንግሥት ውጪ በሆኑ ኃይሎች በተመሳሳይ የመብት ጥሰቶች እና ጥቃቶችን መፈጸማቸውን የሚያመልክቱ በርካታ የሚረብሹ ሪፖርቶች " እየወጡ መሆናቸውንም አምባሳደሩ ጠቅሰዋል።

" ኃይል ሳይሆን ውይይት ብቸኛው አማራጭ ነው"ም ሲሉ አሳውቀዋል። #USEmbassy #BBC

@tikvahethiopia