TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57.1K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Djibouti #DrAbdelaHamdok #IGAD

የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር እና የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር አብደላ ሀምዶክ በ38ኛው የኢጋድ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ጅቡቲ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ጅቡቲ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ አቀባበል ተቀብለዋቸዋል።

የኢጋድ ስብሰባ ነገ ይጀምራል።

በኢጋድ ስብሰባ ላይ ዶ/ር አብይ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ለአባል ሀገራት መሪዎች ሪፖርት እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያን ውስጣዊ ጉዳይ ጨምሮ የኬንያ እና ሶማሊያ አለመግባባት ዋነኛ የውይይት አጀንዳዎች ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የደቡብ ሱዳን የሰላም ሂደት የደረሰበትን ሁኔታ እንደሚዳሰስ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል ኢጋድ እየሰጠ ያለውን የወረርሽኙ የሁለተኛ ዙር ምላሽ በማስመልከት ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ ፦ ኢጋድ፣ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ፣ አል ዓይን
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#IGAD #SUDAN

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የጠሩትን ስብሰባ ሱዳን ተቃወመች።

የሱዳን የውጭ ጉዳይ መ/ቤት ኢጋድ በጠራው ስብሰባ ላይ ሀገሪቱ እንደማትሳተፍ እና እንደማይመለከታት አስታውቋል።

ሱደን ስብሰባውን የተቃወመችው ስብሰባው መጠራት ያለበት በወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር በሱዳን እንጅ በዋና ፀሀፊው ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ እንዳልሆነ ገልጻለች።

የኢጋድ ሊቀመንበር ዶ/ር ወርቅነህ የፕሬዝዳንቶች ጉባዔ ጠርተው የነበረ ቢሆንም፤ ይህንን ስብሰባ ሱዳን እንደማትሳተፍ ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አሊ ሳዲቅ ተናግረዋል።

የኢጋድን ስብሰባ ከወቅቱ ሊቀመንበር ከሱዳን ውጭ ማንም መጥራት እደማይችልም ነው ያስታወቀው። ከዚህ በተጨማሪም በተጠራው ጉባዔ ላይ ሱዳን አጀንዳ መሆን እንደሌለባትም ነው የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያስታወቀው።

የወቅቲ የኢጋድ ሊቀመንበር ሱዳን ስትሆን ይህንንም ሲመሩ የነበሩት የቀድሞው የሀገሪቱ ሽግግር መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ነበሩ።

አሁን ላይ ሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ባይኖራትም የወቅቱ ሊቀመንበር፤ የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር አብደል ፈታህ አልቡርሃን እንደሆነ አስታውቃለች።

የሱዳን ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዛሬ በሱዳን ከኢጋድ ልዑክ መሪ ጋር ተገናኝተዋል ተብሏል።

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም ውሳኔ አሳለፈ። መንግስት ባወጣው መግለጫ ፤ በአሁኑ ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች የሰብዓዊ እርዳታን ፍለጋ ወደአጎራባች ክልሎች እየተጓዙ መሆኑን አመልክቷል። እነዚህ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታው ከቀያቸው ሳፈናቀሉ ባሉበት እንዲርሳቸው ቢደረግ እንግልታቸውን እንደሚቀንስ በጽኑ እንደሚያምን አሳውቋል። በመሆኑም በከፍተኛ…
#AU #IGAD

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር የሆኑት ሙሳፋቂ መሃመት የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም መወሰኑን እንደሚያደንቁ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት የበትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦትን ለማድረስ የወሰነው ውሳኔ ይደነቃል ብለዋል።

በተጨማሪ ፤ የትግራይ ክልላዊ መንግስት ለሰብዓዊነት ተብሎ ግጭት ለማቆም የተላለፈውን ውሳኔ ለመመልከት እና በአስቸኳይ ግጭት ለማቆም ማወጁን እንደሚያደንቁ ገልፀዋል።

ለጋሾች እና የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች በትግራይ ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የሚያደርጉትን ድጋፍ በእጥፍ እንዲያሳድጉም ጥሪ አቅርበዋል።

ሊቀመንበሩ ፤ ሁሉን አቀፍና በድርድር በሚመጣ የተኩስ አቁም ላይ ሁሉም ወገን እንዲደርስ ህብረቱ ጥረቱን እንደሚቀጥል አሳውቀዋል።

በህብረቱ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዜዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ከሁሉም ወገን እና ባለድርሻ አካላት ጋር በመስራት ግጭቱን በፍጥነት ለመቋጨት የጀመሩትን ጥረት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ሊቀመንበሩ አሳውቀዋል።

በሌላ በኩል የኢጋድ ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ማቆሙን አድንቀዋል ፤ የትግራይ ክልል መንግስትም ውሳኔው ንለማክበር እና ግጭት ለማቆም በመወሰን ምላሽ በመስጠቱ አድንቀዋል።

ለትግራይ ክልል እና ሌሎች በድርቅና በምግብ እጦት ለተጎዱ ክልሎች ሰብዓዊ እርዳታ በተጠናከረ መልኩ እንዲደረግ ዓለም አቀፍ አጋሮች የቻሉትን ሁሉ ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ሁሉም ወገኖች ብሄራዊ ውይይት ጨምሮ ለዘላቂ ሰላም መስፈን ሁሉንም የሰላም አማራጮችን እንዲጠቀሙ ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UN #EU የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የትግራይ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ግጭት በአስቸኳይ ለማቆም እና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት መዘጋጀቱን ማሳወቁን በደስታ እንደሚቀበሉት ገልፀዋል። በተጨማሪ የትግራይ ክልላዊ መንግስት በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር ለሚደረገው የሰላም ሂደት ፍቃደኛ መሆኑን አበረታተዋል። ጉተሬዝ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት እና…
#IGAD #ETHIOPIA

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ዛሬ ባወጡት መግለጫ በኢትዮጵያ ግጭት ውስጥ ያሉ ወገኖች በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር ወደ ድርድር ጠረጴዛ ለመመለስ ጠንካራ ፈቃደኝነት በማሳየታቸው መደሰታቸውን ገልፀዋል።

የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ መንግስት በኢትዮጵያ በሁሉም አካባቢዎች ያሉ ቅሬታዎችን በውይይት እና ሁሉን አካታች በሆነ የፖለቲካ ሂደት ለመፍታት ያለውን ያልተቋረጠ ቁርጠኝነት በማንሳትም ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ሁሉም ወገኖች ይህን አጋጣሚ እንዲጠቀሙ ተማጽነዋል።

ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የትግራይ ክልል መንግስት ትላንት ያወጣውን መግለጫ፤ በኢትዮጵያ መንግስት ከዚህ ቀደም ሲቀርቡ ከነበሩት ተመሳሳይ ጥሪዎች ጋር የተስማማ መሆኑን በመግለፅ አበረታተዋል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት እና የትግራይ ክልል መንግስት ሰላም ያሳዩአቸውን ጥረቶች በትዕግስት እና በጠንካራ ቁርጠኝነት እንዲቀጥሉበት አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ የፌደራል መንግስት እና በትግራይ ክልል ያሉ ባለስልጣናት ያልተፈቱ ጉዳዮችን ለመፍታት በግንኙነታቸው ላይ መተማመን እንዲገነቡ እንዲሁም ለሰላም ያሳዩአቸውን ጥረቶች በትዕግስት እና በጠንካራ ቁርጠኝነት እንዲቀጥሉበት ጥሪ አቅርበዋል።

ኢጋድ በአፍሪካ ህብረት መሪነት ለሚካሄደው የሰላም ሂደት ያለውን ድጋፍ በድጋሚ አረጋግጧል።

@tikvahethiopia
#IGAD

ዛሬ በኡጋንዳ፣ ኢንቴቤ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት (ኢጋድ) መሪዎች ስብሰባ ይደረጋል።

ስብሰባው ትኩረት ከሚያደርግባቸው ጉዳዮች አንዱ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረው ውጥረት ነው።

ሌላው የሱዳን ጦርነት ነው።

ለኢጋድ የመሪዎች ስብሰባ እስካሁን ድረስ በታወቀው ፦

የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር የጅቡቲው ፕሬዜደንት ኢሳሜል ኦማር ጌሌህ

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሙሐሙድ

የደቡብ ሱዳን ፕሬዜዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል መሪ መሃመድ ሃምዳን ደጋሉ ካምፓላ ይገኛሉ።

#Sudan : የሱዳንን ብሔራዊ ጦር የሚመራው የሱዳን መንግሥት ኢጋድ የተፋላሚውን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል አዛዥ በስብሰባው እንዲሳተፉ መጋበዙ ‘የሃገሪቱን ሉላዊነት ጥሷል’ በሚል ውንጀላ ከኢጋድ ጋር ያለውን ግንኙነት አቋርጧል።

የኢጋድ አባል ሀገራት እነማን ናቸው ?
🇪🇹 ኢትዮጵያ
🇰🇪 ኬንያ
🇺🇬 ኡጋንዳ
🇸🇩 ሱዳን
🇩🇯 ጅቡቲ
🇪🇷 ኤርትራ
🇸🇸 ደቡብ ሱዳን
🇸🇴 ሶማሊያ ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#IGAD ዛሬ በኡጋንዳ፣ ኢንቴቤ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት (ኢጋድ) መሪዎች ስብሰባ ይደረጋል። ስብሰባው ትኩረት ከሚያደርግባቸው ጉዳዮች አንዱ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረው ውጥረት ነው። ሌላው የሱዳን ጦርነት ነው። ለኢጋድ የመሪዎች ስብሰባ እስካሁን ድረስ በታወቀው ፦ የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር የጅቡቲው ፕሬዜደንት ኢሳሜል ኦማር ጌሌህ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት…
#USA #IGAD

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ካምፓላ እና አዲስ አበባን ይጎበኛሉ ተብሏል።

ማይክ ሐመር መጀመሪያ ካምፓላ ገብተው በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ እንዲሁም በሱዳን ጦርነት ላይ በሚመክረው የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) መሪዎች ስብሰባ ላይ ይሳተፋሉ።

ከዛም ወደ ኢትዮጵያ፣ አዲስ አባባ ይመጣሉ።

ልዩ መልዕክተኛው በአዲስ አበባ ቆይታቸው፦

" - ከኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በተለይ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ስላለው ግጭት ውይይት ያደርጋሉ።

- በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ያሉትን ግጭቶች አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ይወያያሉ።

- ሰላማዊ ሰዎች እንዲጠበቁ እንዲሁም ሰብዓዊ መብት እንዲከበር ጥሪ ያቀርባሉ።

- ከአንድ ዓመት በፊት በስምምነት የተቋጨውን የትግራይ ጦርነት ተከትሎ የሚከናወነውን ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታት፣ ተሃድሶ እና ማሰናበትን በተመለከተ እንዲሁም ተጎጂዎችን መሠረት ስላደረገው የሽግግር ፍትህ ሂደት ይወያያወሉ። " ሲል የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አሳውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ቢቢሲ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤትን ዋቢ አደርጎ ካሰራጨው ዘገባ ነው የወሰደው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#IGAD ዛሬ በኡጋንዳ፣ ኢንቴቤ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት (ኢጋድ) መሪዎች ስብሰባ ይደረጋል። ስብሰባው ትኩረት ከሚያደርግባቸው ጉዳዮች አንዱ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረው ውጥረት ነው። ሌላው የሱዳን ጦርነት ነው። ለኢጋድ የመሪዎች ስብሰባ እስካሁን ድረስ በታወቀው ፦ የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር የጅቡቲው ፕሬዜደንት ኢሳሜል ኦማር ጌሌህ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት…
#IGAD

" ... ማንኛውም #ስምምነት ወይም #ዝግጅት በሶማሊያ ፌዴራላዊ መንግስት #ፈቃድ መሆን አለበት " - ኢጋድ

የምሥራቅ አፍሪካ ልማት በየነ መንግሥታት (ኢጋድ) ዛሬ ኡጋንዳ ኢንቴቤ ውስጥ አስቸኳይ የመሪዎች ስብሰባውን አድርጎ ነበር።

ይህ አስቸኳይ ስብሰባ የኢጋድ መስራቿ ኢትዮጵያን ጨምሮ የኤርትራ እና የሱዳን መንግሥት ተወካዮች / መሪዎች ባልተገኙበት የተካሄደ ነው።

ስብሰባው ትኩረት ያደረገው ስለ ወቅታዊው የኢትዮጵያ እና ሱማሊያ ግንኙነት ጉዳይ እንዲሁም ስለ ሱዳን ጦርነት ነው።

ከኢጋድ አባል ሀገራት የትኞቹ መሪዎች ተገኙ ?

🇩🇯 የጅቡቲ ፕሬዜዳንት ኢማኤል ኦማር ጌሌህ (ስብሰባውን የመሩት እሳቸው ናቸው/ የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር ናቸው)
🇰🇪 የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ
🇸🇴 የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ
🇸🇸 የደቡብ ሱዳን ፕሬዜዳንት ሳልቫኪየር ማያርዲት
🇺🇬 የኡጋንዳ ፕሬዜዳንት ዩዌሪ ካጉታ ሙሴቬኒ ተገኝተው ነበር።

ሌሎችስ እነማን ተገኙ ?

- የኢጋድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ፤
- የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃማት
- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ የሱዳን የግል መልዕክተኛ ራምታኔ ላምራ፣
- የሳውዲ አረቢያ መንግሥት ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋሌድ አልኩራጂ
- የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች / #UAE የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ካሊፋ ሻሂን አል ማራርት
- የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አኔታ ዌበር፤
- #የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር፤
- የአረብ ሀገራት ሊግ ረዳት ዋና ፀሀፊ ሆሳም ዛኪ
- የኢጋድ ምክትል ሥራ አስፈፃሚ መሐመድ አብዲ ዋሬ
- የደቡብ ሱዳን የኢጋድ ልዩ መልዕክተኛ እና የሱዳን የሰላም ሂደት የኢጋድ ተወካይ አምባሳደር እስማኤል ዋይስ
- የኢጋድ የቀይ ባህር፣ የኤደን ባህረ ሰላጤ እና የሶማሊያ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር መሀመድ አሊ ጉዮ
- #በቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የምስራቅ አፍሪካ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቱትኩ ኢናም
- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ቺክ ኮንዴ ተገኝተው ነበር።

ኢጋድ ከስብሰባው በኃላ ባወጣው መግለጫ ምን አለ ?

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግኙነት መካከል የተፈጠረው ሁኔታ በእጅጉ እንደሚያሳስበው ገልጿል።

በዋነኛ መርህነት የሶማሊያ ሉዓላዊነት ፣ አድነት እና የግዛት አንድነት ሊከበር ይገባል ሲል አረጋግጧል። ማንኛውም ተሳትፎ ይህንን መርህ ባከበረ መልኩ ሊሆን ይገባል ብሏል። ማንኛውም #ስምምነት ወይም #ዝግጅት በሶማሊያ ፌዴራላዊ መንግስት #ፈቃድ መሆን አለበት ብሏል።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በመካከላቸው ያለውን ውጥረት በማርገብ በምትኩ ገንቢ የሆነ ውይይት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

ኢትዮጵያ ስብሰባው ላይ ለምን አልተገኘችም ?

ኢትዮጵያ ከዛሬው የአስቸኳይ ስብሰባ ቀደም ብላ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል " በተደራራቢ መርሃ ግብር " ምክንያት በዚህ ስብሰባ ላይ መገኘት እንዳማትችል ለጂቡቲ የውጭ ጉዳይና አለም አቀፍ ትብብር እና ኢጋድ በድብዳቤ አሳውቃለች።

ኢጋድ ከጠራው ጉባኤ ቀደም በሎ ከተያዘ መርሃ ግብር ጋር የሚጋጭ በመሆኑ እና የተቀመጠውም ጊዜ አጭር በመሆኑ በስብሰባው ላይ መገኘት እንደሚያስቸግራት በዚሁ ደብዳቤ አሳውቃ ነበር።

ነገር ግን " ኢጋድ በሚመራበት ደንብ መሰረት " በተለዋጭ ቀን ለመወያየት ዝግጁ መሆኗን አሳውቃቸዋለች።

(ሙሉ የኢጋድ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia