TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በአዲስአበባ ሰሞኑን እየታየ ካለው አፈሳ ጋር ተያይዞ የአዲስአበባ ፖሊስ ኮምሽነር ሜጀር ጄኔራል #ደግፌ_በዲ የሰጡት መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች፡-

▪️በአዲስአበባ በሰሞኑ ግጭቶች 28 ሰዎች ሞተዋል፣

▪️በአብዛኛው ሰዎች የሞቱት ከሆስፒታል በተገኘ መረጃ መሰረት በድብደባ ነው፣

▪️7 ያህሉ በጸጥታ ኃይሎች የተገደሉ ሲሆን አምስቱ የሞቱት በቂርቆስ አካባቢ ነው፣ አንዱ በስህተት የተገደለ ነው፣ አጥፊው ተይዟል፣

▪️በርካታ ሰዎች ብንይዝም አብዛኛውን እየመከርን፣ እያስተማርን ለቀናል፣በአሁኑ ሰዓት 1 ሺ 204 ሰዎች በጦላይ
በእስር ላይ ይገኛሉ፣

▪️174 ያህሉ በሕግ የሚጠየቁ ናቸው፣ ቀሪዎቹ ተገቢው ትምህርት ተሰጥቷቸው ይለቀቃሉ፣

▪️ባንኮችን ለመዝረፍ ተሞክሯል፣ ቤቶች፣ ሱቆች ተደብድበዋል፣ መኪኖች ተቀጥቅጠዋል፣

▪️1 ሺ 459 ሺሻ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወስዷል፣

▪️31 ሰዎች ከቁማር ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ውለዋል፣

▪️94 የማስቃሚያ ቤቶች ተይዘዋል፣

▪️በአ/አ ሕገወጥነት፣ዘረፋ እየተስፋፋ ነው፣ መኪናም ጭምር በጠራራ ጸሐይ ይዘረፋል፣

▪️ከክልል ጭምር የተደራጁ (ከጎንደር፣ ከደሴ፣ ከአርባምንጭ) ቡድኖች አ/አ ውስጥ እየዘረፉ ነው፣

▪️25 ጊዜ የዘረፈ ግለሰብ ተይዟል፣

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሚዘጉ መንገዶች⬇️

የመስቀል በዓል በሰላም እንዲከበር #አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ወደ ስራ መግባቱን – የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽን ኮሚሽነር #ደግፌ_በዲ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች፣ የመንግስት ባለስልጣናት የውጪ ሀገር ቱሪስቶች የሚታደሙበት የደመራ በዓል በሰላም እንዲከበር ፓሊስ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን ተናግረዋል።

በዓሉ በሰላም እንዲከበር ኮሚሽኑ ከሌሎች የፀጥታ አካላት እና ከእምነቱ ተቋም ጋር #በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ነው ኮሚሽነሩ የተናገሩት፡፡

ህብረተሰቡ እንደዚህ ቀደሙ የዘንድሮ የመስቀል በዓለል በሰላም እንዲከበር ህብረተሰቡ ለፀጥታ አካላት እያደረገ ያለውን #ድጋፍ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል።

ኮሚሽነሩ የበዓሉ ታዳሚዎች ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ እንደሚኖርና ወደ በዓሉ አዋኪ ነገሮችን ይዞ መምጣት እንደማያስፈልግ የገለፁ ሲሆን፥ ለዚህም የህብረተሰቡ ትብብር ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

በመስቀል አደባባይ የሚካሄደውን የደመራ ፕሮግራም ተጀምሮ አስከሚጠናቀቅ እና የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር የሚዘጉ መንገዶች
የሚከተሉት ናቸው፦

▪️ከቦሌ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ወይም ኦሎፒያ

▪️ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኒያለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው
መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያ

▪️ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ወደ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር መታጠፊያ

▪️ከቸርችር ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ
ከተክለ ሀይማኖት ፣ ጥቁር አንበሳ ፣ ኢሚግሬሽን የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ የኋላ በር

▪️ከተክለ ሀይማኖት፣ በሜትሮሎጂ ፣ጥቁር አንበሳ፣ ኢ.ቢ.ሲ የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት በር

▪️ከጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ
ከሳሪስ፣ በጎተራ ፣ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ መሾለኪያ

▪️ከጦር ኃይሎች ፣ ልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ፣ ሜክሲኮ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለገሃር ጉምሩክ አካባቢ ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች መንገዶቹ ዝግ መሆናቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል።

በአመራጭነትም የሚከተሉትን መንገዶች መጠቀም እንደሚቻልም ተገልጿል።

▪️ከቦሌ በመስቀል አደባባይ ወደ 4ኪሎ መሄድ የሚፈልጉ ቦሌ- ወሎ ሰፈር- ኦሎፒያ- ኡራኤል- ካሳንችስ-አራት ኪሎ

▪️ከቦሌ ፣ በመስቀል አደባባይ ወደ ጦር ኃይሎች መሄድ የሚፈልጉ ቦሌ- ወሎ ሰፈር- ጎተራ ቀለበት መንገድ – ቄራ – ሳር ትንባሆ ሞኖፖል- ሜክሲኮ አደባባይ- ጦር ኃይሎች

▪️ከሜክሲኮ፣ በለገሃር ፣ በመስቀል አደባባይ ወደ 22 መገናኛ መሄድ የሚፈልጉ ሜክሲኮ አደባባይ- ዲአፍሪክ ሆቴል ሳር ቤት ብሄራዊ ቲያትር- ኢትዮጵያ ሆቴል – ፍል ውሃ – ብሄራዊ ቤተ-መንግስት- ካሳንቺስ- ኡራኤል– በ22 መገናኛ

▪️ከሜክሲኮ በለገሃር በአዲስ አበባ ስታዲዬም መሄድ የሚፈልጉ በለሃር መብራት – በአዲሱ ቂርቆስ መንገድ – ርቼ – በቅሎቤት-ጎተራ ወይም
በለሃር መብራት – በአዲሱ ቂርቆስ መንገድ – ጎፋ ማዞሪያ – ጎተራ

▪️ከፒያሳ ፣ በአምባሳደር ፣ ጊዮን ሆቴል ወደ ጎተራ መሄድ የሚፈልጉ አምባሳደር ቲያትር- ፍል ውሃ- ካሳንቺስ- ኡራኤል ቤ/ክር-አትላስ ሆቴል- ወሎ ሰፈር ጎተራ መሆናቸው ታውቋል።

ጥቆማ ለመስጠትም የሚያስችሉ ስልክ ቁጥሮች . 991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እንዲሁም፦

011- 1 -11- 01 – 11 ፣
011- 1- 26- 43- 59 ፣
011- 1- 01- 02- 97፣
011-8-69-88-23 ፣ 011-8-69-90-15 ፣ 011-5-54-36-81 ፣ 011-5-54 -36-78 ፣ 011-5-54 -38 -04 መጠቀም እንደሚቻል ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወጣቶቹ በዚህ ሳምንት ይለቀቃሉ‼️

ከአዲስ አበባ ተወስደው ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ የሚገኙ የአዲስ አበባ ወጣቶች በሳምንቱ መጨረሻ እንደሚለቀቁ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ብርጋዲየር ጄኔራል #ደግፌ_በዲ ለቢቢሲ ገለፁ።

ወጣቶቹ የተያዙት "በጎዳና ላይ ንብረት ሲያወድሙና ሁከት ሲፈጥሩ ነው" ያሉት ኮሚሽነሩ መጀመሪያ ከተያዙት ተጣርቶ አሁን በማሰልጠኛ ያሉት 1174 እንደሆኑ ገልፀዋል።

እሳቸው እንደሚሉት የፈፀሙት ተግባር በህግ የሚያስጠይቃቸው ቢሆንም መታነፅ እንዳለባቸው በማመን ለዚህም ከቤተሰብና ከማህበረሰብ ቀጥሎ ሃላፊነት ያለበት መንግስት በመሆኑ ይህን ተግባሩን እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

"ማነፅ ብቻ ሳይሆን የወጣቶቹን ማንነት በመገንዘብ ስራ የሌለው ስራ እንዲሰራ፣ ተማሪውም ትምህርቱን እንዲቀጥል ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ነው እነዚህ ልጆች ላይ ስራ እየሰራን ያለነው"ብለዋል ኮሚሽነሩ።

ይህን ለማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ የሚመለከታቸው ትብብር ላይ መሆናቸውንም ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊሶች ወጣቶችን በቡድን ሲደበድቡ የሚያሳይ ቪዲዮ ስለመለቀቁ ለኮሚሽነሩ ከBBC ጥያቄ ተነስቶላቸው ነበር።

ምንም እንኳ እሳቸው ተንቀሳቃሽ ምስሉን ባይመለከቱትም ቦታው ተገልፆ ትክክለኛ መረጃ ከደረሳቸው ተግባሩን በፈፀሙት አካላት ላይ ተጣርቶ #እርምጃ እንደሚወሰድ ገልፀዋል።

መሳለሚያ ሞቢል አካባቢ ለግንቦት ሰባት መሪዎች አቀባበል ሲደረግ ሰንደቅ አላማ በመስቀልና ባነሮችን በመለጠፍ ይንቀሳቀስ ነበር።

ያሳደጉትና የክርስትና ልጃቸው በአመፅ ሳይሆን የግንቦት ሰባት መሪዎች አቀባበል ላይ ባደረገው ተሳትፎ ከዚያም የቡራዮውን ግድያ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣቱ መታሰሩን አቶ ዘመነ ሞላ ለቢቢሲ ይገልፃሉ።

ከዚህ ውጭ ልጃቸው ሰላማዊ እንደሆነም ያስረዳሉ። ያሳደጉት ልጃቸው ወጣት ፍስሃ ደምስ የ25 ዓመት ወጣት ሲሆን እናቱ እንደሌለችና የሚኖረው ከአቅመ ደካማ አያቱ ጋር እንደነበር አቶ
ዘመነ ይናገራሉ።

እሳቸው እንደገለፁት የታሰረው ወደ ቤቱ የሚወስድ መንገድ ላይ አመሻሽ ላይ ነው። መጀመሪያ ወደ ተወሰደበት ፖሊስ ጣቢያ ሄደው ሲጠይቁ ጦላይ መወሰዱን መስማታቸውንና ከዚያ በኋላ ያለ ምንም መረጃ ቤተሰብ ስቃይ ላይ እንዳለ ይገልፃሉ።

የአዲስ አበባ ወጣቶች ጅምላ የመገናኛ ብዙሃንና የማህበራዊ ሚዲያ ርእሰ ጉዳይ ሆኖ ሰንብቷል። በማህበራዊ ሚዲያው የአዲስ አበባ ወጣቶች ይፈቱ የሚል ዘመቻም በመካሄድ ላይ ነው።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል የአዲስ አበባ ወጣቶችን በጅምላ አስሮ ስልጠና ማስገባት የህግ አግባብነት እንደሌለው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የህግ ባለሙያና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ፕሮጀክት ፕሮጀክት አስተባባሪ የሆነችው ሶሊያና ሽመልስ መንግስት እነዚህን ወታደሮች አስሮ ወደ ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ በመላኩ የጣሳቸው ህጎች አሉ ትላለች።

"ተግባሩ በትንሹ አራት የህገ መንግስቱን አንቀፆች ይጥሳል።የታሰሩ ሰዎች መብት፣ የተከሰሱ ሰዎች መብት ፣ የተጠረጠሩ ሰዎች መብትና ከዚያም ጋር ተያይዞ መደረግ የሚገባቸው ነገሮች በትንሹ አንድ አራት የህገመንግስቱ አንቀፆች ተጥሰዋል። የወንጀል ስነስርዓት ህጉንም ብንመለከት እዚያ ላይም የተጣሱ ነገሮች አሉ" ትላለች።

እሷ እንደምትለው በመሰረተ ሃሳብ ደረጃ መንግስት ሰዎችን ሰብስቦ ካሰረ ያሰረበትን ምክንያት ፍርድ ቤት አቅርቦ ፍቃድ መጠየቅ ይኖርበታል። በወሰደው እርምጃ የቀማው የግለሰቦችን ነፃነት በመሆኑ ይህን ደግሞ ያለ ፍርድ ቤት ፍቃድ ማድረግ አይቻልም።

ስለዚህም ግለሰቦቹን ፍርድ ቤት አለማቅረብ፣ የተከሰሱበትን ምክንያት አለማወቃቸውን እንዲሁም የዋስትና መብታቸውን መነፈጋቸው በሃይማኖትና በዘመድ መጎብኘት አለመቻላቸውን የመሰሉ ነገሮች ሲታዩ በእርምጃው ብዙ የመብት ጥሰቶች እንዳሉ ታስረዳለች።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ⬇️

በአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ወረራን ጨምሮ #ህገ_ወጥ ተግባራት እየተበራከቱ መምጣታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን እና ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት አመራሮች እና ባለ ድርሻ አካላት ዛሬ ተወያይተዋል።

በውይይቱ ወቅት የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሜጀር ጄኔራል #ደግፌ_በዲ፥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከተማዋ ህገ ወጥ የመሬት ወረራና ተግባር እየተበራከተ መምጣቱን ተናግረዋል።

ከመሬት ወረራው ባሻገርም የኮንትሮ ባንድ ንግድ እና ህገ ወጥ የመንገድ ላይ ንግድ መበራከቱንም ነው የተናገሩት።

ይህን ለመከላከልና የህግ የበላይነትን ለማስፈንም ህብረተሰቡን በማሳተፍ ውጤታማ ስራ ሊያሰራ የሚያስችል እቅድ አዘጋጅቶ ወደ ተግባር መግባት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

ለወንጀሉ መስፋፋት መንስኤ በሆኑ ጫት ማስቃሚያ፣ ሺሻ ማስጨሻ እና ቁማር ማጫወቻዎች ላይ ልዩ ትኩረት ይሰጣል ያሉት ኮሚሽነሩ፥ የተደራጁ ወንጀለኞች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የአስተዳደሩ ደንብ ማስከበር አገልግሎት ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ ኮሚሽነር ፍስሃ ጋረደው በበኩላቸው፥ ደንብን የማስከበር ስራ ለተቋማት ብቻ የሚተው ስራ አለመሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህ አንጻርም ህብረተሰቡና ባለ ድርሻ አካላት ህግን ከማስከበር አኳያ ሁለቱ ተቋማት እያደረጉት ላለው ጥረት እገዛ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ኮሚሽኑ እና ጽህፈት ቤቱም በከተማዋ እየተስተዋለ ያለውን ህገ ወጥ ተግባር ለመከላከል የሚያደርጉትን ጥረት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መግለጻቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ለጣቢያችን የላከው መግለጫ ያመላክታል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia