TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አስቸኳይ ጥቆማ ለፖሊስ📌

በአዲስ አበባ ዙሪያ #አንፎ ከአስፓልቱ ጀርባ - ከቀራንዮ እስከ አሸዋ ሜዳ ያሉት የውስጥ ሰፈሮች ጥብቅ ጥበቃ እና ቁጥጥር እንዲሁም አሰሳ ሊደረግባቸው ይገባል።

በአካባቢው ዝርፊያ እና ግድያ እየፈፀሙ ያሉት አካላት ቀን እምብዛም የማይታዩ ሲሆን(እንደውንም አንዳንዶቹ እዛው ያሉ ናቸው) ምሽት ከ2:00 በኋላ ግን ጠጥተው እና ሰክረው አሰቃቂ ወንጀል የሚፈፅሙ ናቸው።

እነዚህ የተደራጁ አካላት የታጠቁ እና በልዩ ሁኔታ #በቅንጅት የሚንቀሳቀሱ እንደሆነ ከነዋሪዎች ለመስማት ችያለሁ።

አሰቃቂ ወንጀሎችን የሚፈፅሙት አካላት ፖሊስ ሲመጣ እየተሰሩ ባሉ ቤቶች የሚሸሸጉና ፖሊስ ከአካባቢው ሲሄድ ወጥተው ወንጀል የሚፈፅሙ ናቸው።

ፖሊስ በአካባቢዎቹ በየሰዓቱ እየወጣ ከሚሄድ ለቀናት አሰሳ እና ክትትል እንዲያደርግ ነዋሪዎች ጠቁመዋል።

አንድ እዛው አካባቢ የሚኖር ወዳጄ እንደነገረኝ ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱት አካላት በእርግጠኝነት ከጀርባቸው አንዳች ተልዕኮ የተሰጣቸው ቀን ዝም ብለው ምሽቱን ሰዎችን የሚያሰቃዩ ናቸው ብሎኛል። መንግስት ወንጀለኞችን ከመቆጣጠር በተጨማሪ የችግሩን ምንጭ ጠንቅቆ ተረድቶ ህግ ማስከበር ይኖረበታል ሲል ገልጾልኛል። በተጨማሪ በአካባቢው ፖሊስ ምላሽ ህዝቡ ደስተኛ አንዳይደለ ተናግሮ ፖሊሶች ህግ እንዲያስከብሩ ቢደረግ ጥሩ መሆኑን አንስቷል።

ሌላው ጥቆማ📌

አንፎ ከአስፓልት ወደ ውስጥ ባሉት መንደሮች በቂ ፖሊስ የለም ያሉትም ችግሩን ለመፍታት ሲሞክሩ አልተስተዋለም። የፀጥታ አካላትን ሁኔታ መንግስት ሊከታተል ይገባል። የፌደራል እና የመከላከያ ሰራዊት በበላይነት የአካባቢው ደህንነት ሊያስጠብቁ ይገባል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሚዘጉ መንገዶች⬇️

የመስቀል በዓል በሰላም እንዲከበር #አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ወደ ስራ መግባቱን – የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽን ኮሚሽነር #ደግፌ_በዲ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች፣ የመንግስት ባለስልጣናት የውጪ ሀገር ቱሪስቶች የሚታደሙበት የደመራ በዓል በሰላም እንዲከበር ፓሊስ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን ተናግረዋል።

በዓሉ በሰላም እንዲከበር ኮሚሽኑ ከሌሎች የፀጥታ አካላት እና ከእምነቱ ተቋም ጋር #በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ነው ኮሚሽነሩ የተናገሩት፡፡

ህብረተሰቡ እንደዚህ ቀደሙ የዘንድሮ የመስቀል በዓለል በሰላም እንዲከበር ህብረተሰቡ ለፀጥታ አካላት እያደረገ ያለውን #ድጋፍ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል።

ኮሚሽነሩ የበዓሉ ታዳሚዎች ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ እንደሚኖርና ወደ በዓሉ አዋኪ ነገሮችን ይዞ መምጣት እንደማያስፈልግ የገለፁ ሲሆን፥ ለዚህም የህብረተሰቡ ትብብር ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

በመስቀል አደባባይ የሚካሄደውን የደመራ ፕሮግራም ተጀምሮ አስከሚጠናቀቅ እና የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር የሚዘጉ መንገዶች
የሚከተሉት ናቸው፦

▪️ከቦሌ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ወይም ኦሎፒያ

▪️ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኒያለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው
መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያ

▪️ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ወደ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር መታጠፊያ

▪️ከቸርችር ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ
ከተክለ ሀይማኖት ፣ ጥቁር አንበሳ ፣ ኢሚግሬሽን የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ የኋላ በር

▪️ከተክለ ሀይማኖት፣ በሜትሮሎጂ ፣ጥቁር አንበሳ፣ ኢ.ቢ.ሲ የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት በር

▪️ከጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ
ከሳሪስ፣ በጎተራ ፣ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ መሾለኪያ

▪️ከጦር ኃይሎች ፣ ልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ፣ ሜክሲኮ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለገሃር ጉምሩክ አካባቢ ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች መንገዶቹ ዝግ መሆናቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል።

በአመራጭነትም የሚከተሉትን መንገዶች መጠቀም እንደሚቻልም ተገልጿል።

▪️ከቦሌ በመስቀል አደባባይ ወደ 4ኪሎ መሄድ የሚፈልጉ ቦሌ- ወሎ ሰፈር- ኦሎፒያ- ኡራኤል- ካሳንችስ-አራት ኪሎ

▪️ከቦሌ ፣ በመስቀል አደባባይ ወደ ጦር ኃይሎች መሄድ የሚፈልጉ ቦሌ- ወሎ ሰፈር- ጎተራ ቀለበት መንገድ – ቄራ – ሳር ትንባሆ ሞኖፖል- ሜክሲኮ አደባባይ- ጦር ኃይሎች

▪️ከሜክሲኮ፣ በለገሃር ፣ በመስቀል አደባባይ ወደ 22 መገናኛ መሄድ የሚፈልጉ ሜክሲኮ አደባባይ- ዲአፍሪክ ሆቴል ሳር ቤት ብሄራዊ ቲያትር- ኢትዮጵያ ሆቴል – ፍል ውሃ – ብሄራዊ ቤተ-መንግስት- ካሳንቺስ- ኡራኤል– በ22 መገናኛ

▪️ከሜክሲኮ በለገሃር በአዲስ አበባ ስታዲዬም መሄድ የሚፈልጉ በለሃር መብራት – በአዲሱ ቂርቆስ መንገድ – ርቼ – በቅሎቤት-ጎተራ ወይም
በለሃር መብራት – በአዲሱ ቂርቆስ መንገድ – ጎፋ ማዞሪያ – ጎተራ

▪️ከፒያሳ ፣ በአምባሳደር ፣ ጊዮን ሆቴል ወደ ጎተራ መሄድ የሚፈልጉ አምባሳደር ቲያትር- ፍል ውሃ- ካሳንቺስ- ኡራኤል ቤ/ክር-አትላስ ሆቴል- ወሎ ሰፈር ጎተራ መሆናቸው ታውቋል።

ጥቆማ ለመስጠትም የሚያስችሉ ስልክ ቁጥሮች . 991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እንዲሁም፦

011- 1 -11- 01 – 11 ፣
011- 1- 26- 43- 59 ፣
011- 1- 01- 02- 97፣
011-8-69-88-23 ፣ 011-8-69-90-15 ፣ 011-5-54-36-81 ፣ 011-5-54 -36-78 ፣ 011-5-54 -38 -04 መጠቀም እንደሚቻል ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia