TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጠ/ሚ ዶክተር አብይ⬆️

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር #ዐብይ_አህመድ ከExim ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ #ሁ_ሻኦሊን ጋር በትብብር በሚሰሩበት እና በልማት ላይ ግንኛነታቸውን የበለጠ ማጠናከር በሚቻልበት ዙሪያ መወያየታቸውን እና የኢትዮጵያ ብድርን መልሶ ማደራጀት ላይ መስማማታቸን ከጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ሀላፊው አቶ #ፍፁም_አረጋ ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ⬆️

በአዲስ አበባ ሲካሄድ የሰነበተው የኢጋድ ስብሰባ በስኬት #ተጠናቅቋል፡፡ በስብሰባው የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር፣ ሪያክ ማቻርና የሌሎች ቡድኖች መሪዎች የተሻሻለውን የሰላም ስምምነት ፈርመዋል፡፡ የኢጋድ ሊቀመንበር የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር #ዐብይ_አህመድ የስምምነቱን ፈራሚዎች እንኳን ደስ ያላችሁ ማለታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ የትዊተር መልዕክት ለማወቅ ተችሏል።

©ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ⬆️ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር #ዐብይ_አህመድ እና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዘዳንት ክቡር ኦቦ ለማ መገርሳ በትላንትናው የኦህዴድ ድርጅታዊ ጉባኤ የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሁን⬆️ፕሬዘዳንት #ኢሳያስ_አፈወርቂ ለሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል። ፕሬዘዳንቱ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠ/ሚ ዶ/ር #ዐብይ_አህመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፎቶ፦ አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ⬆️የቀድሞው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ኃይለማርያም_ደሳለኝ እና የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #ዐብይ_አህመድ በዛሬው ዕለት ተገናኝተዋል። አቶ ኃይለማርያም በፕሬዘዳንት ኢሳያስ ቅበላ ወቅትም ነበሩ።

ፎቶ፦ አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የርብ ግድብ ምረቃ⬆️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐብይ_አህመድ በርብ ያደረጉት ንግግር፦

• ዛሬ ጠዋት ከጣና ጀምረን ደንቢያ አካባቢና ሊቦከምከም አካባቢ እምቦጭ የሚባል ብቻየን ካልኖርኩ የሚል ጠላት ጎብኝተናል፡፡ የገባኝ ሚስጥር እንደ ጣልያን ርብ ላይ እንደሚሸነፍ ተረድቻለሁ፡፡

• ጠላቶቻችን በዚህች ቅድስት ሀገር ላይ ጦርነት ቢያውጁም አሸንፈው አያውቁም፡፡ እምቦጭንም እናሸንፈዋለን፡፡

• ኢትዮጰያ የአፍሪካ ውኃ ማማ ካስባሏት አካባቢዎች አንዱ ይህ አካባቢ ነው፡፡ ነገር ግን ውኃ፣ ጉልበትና መሬት እያለ አቀናጅተን አልተጠቀምንም፡፡

• እርሻን እንደ ቅርስ ባለማዘመን ከሚተቹ ሀገራት አንዷ ነች፡፡ እያሻሻልን መሄድ ሲገባን ዛሬም አርሶ አደሮች ብዙ ጉልበት እያፈሰሱ ትንሽ ምርት የሚያገኙ ናቸው፡፡

• ይህንን የእልህ የሆነ ዝናብ፣ ፀሐይ፣ እምቦጭ በጋራ እንደምናሸንፍ እንድንችል በጋራ እንድንቆም ይገባል፡፡ አሁን ለኢትዮጵያ የሚያዋጣው መደመር ብቻ ነው፡፡ እንደ እምቦጭ ሁሉም ለእኔ ከሆነ ተያይዞ መጥፋት ነው፡፡

• በግድቡ አገዳ፣ ፍራፍሬ ፣ አትክልት አሳ፣ እያመረቱ መጠቀም ይገባል፡፡ይህንን ግድብ እውን ለማድረግ ሕይወት ጭምር የከፈላችሁ ናችሁና በአግባቡ መጠቀም ይችላል፡፡ የጎንደርን ውብ አካባቢ ቱሪስቶች እንዲጎበኙ ለማድረግ ሁላችንም እንሥራ፡፡

• ስትፈጠርም የዳቦ ቅርጫት የሆነች ኢትዮጵያን ሀብቷን አቀናጅተን እንሥራ፡፡መስኖ ከሀገራዊ ኢኮኖሚው አራት በመቶ ብቻ ነው የሸፈነው፤ ስለዚህ ይህንን ማሻሻል አለብን፡፡ አሁን ተቋቋመው የመስኖ ኮሚሽን ግድብ ጀምረው የሚጨርሱ ተቋራጮችም ስላሉ ድርሻውን ይወጣል፡፡

• የአካባቢው አርሶ አደሮች የሚያስፈልጋችሁን የቴክኖሎጂና የሙያ ድጋፍ ያደርጋል፡፡

• በእምቦጭ ላይ በምናደርገው ዘመቻ በድጋሜ እንገናኛለን፤ እመቦጭ መሆን አያስፈልግም፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
ፎቶ፦ አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጀርመን ለምትገኙ‼️

በነገዉ እለት ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር #ዐብይ_አህመድ በፍራንክፉርት «ኮሜርስ አሬና» በተባለዉ ስቴዲየም ከኢትዮጵያዉያንና ትዉልድ ኢትዮጵያዊያን ጋር ይገናኛሉ። ተሳታፍዎቹ ከጀርመን ብቻ ሳይሆን ከተለያዩ የአዉሮጳ አገራት በዝግጅቱ ላይ ይታደማሉ። በዚህ ዝግጅት በግምት 25 ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐብይ እንደሚያቀርብ ይጠበቃል። ወደፊት የኢትዮጵያ ጉዞም ወሳኝ በአዉሮጳ ዉስጥ
በርካታ ኢትዮጵያዉያን ምሁራን እና የፖለቲካ አዋቂዎች በመኖራቸዉና አንድ አንዶች ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር ፊት ለፊት መወያየት ባለመቻላቸዉ ብዙዎችን አስኮርፎአል። የፓሪስ ፈረንሳይና የበርሊን ጀርመን ጉብኝት በዋናነት በሁለት አገሮች የሚደረግ መንግስታዊ ጉዳይ መሆኑን የፍራንክፉርት ጉብኝት አስተባባሪ ድያቆን ዳንኤል ክብረት ተናግረዋል። ይሁን እንጅ በነገ እለት በፍራንክፉርት ከኢትዮጵያዉያንና ትዉልድ ኢትዮጵያዊያን ጋር ለመገናኘት ተጨማሪ ቀን መያዙን ድያቆን ዳንኤል ገልፀዋል።

በነገዉ ሥነ-ስረዓት ላይ ታዳሚዎች ምን ማድረግ እንዳለባቸዉም እንደ #ማሳሳብያ የሚከተሉትን ነጥቦች ዝርዝረዋል፤

- የፍተሻዉን ጊዜ በጣም ለማሳጠር ትልልቅ ሻንጣዎችን ይዞ ከመምጣት ታዳሚዎች መቆጠብ ይኖርባቸዋል።

- ቀጠሮዉን አክብሮ በግዜ መገኘት አስፈላጊ ነዉ።

- ሕጻናትና ልጆችን የያዙ ቤተሴቦች የሕጻናት መቀመጫ ጋሪዎቻቸዉ የሚሆኑበት የተወሰነ ቦታ ተዘጋጅቶአል። ቦታዉ ግን ይህን ያህል ብዙ አይደለም።

- ከሕፃናት ምግብ በስተቀር ምግብ ይዞ ወደ ስታድዮም መግባት አይቻልም። በአንጻሩ ምግብ መጠጥ መሸጫ ቦታ በቂ ተዘጋጅቶአል።

ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ‹‹የኢትዮጵያ ፓርላማ ነገ ጠዋት 3፡00 ላይ አዲስ ዜና ይኖረዋል፤ጉዳዩን ከፓርላማው ነገ ስሙ፡፡›› - ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐብይ_አህመድ ከፍራንክፈርት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዳዩ ምን እንደሆነ ግን ሳይናገሩ ቀርተዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎንደር‼️ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐብይ_አህመድ ጎንደር ከተማ ገብተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህር ዳር‼️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐብይ_አህመድ፣ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ፕሬዝዳንት ሙሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ለ7 ሚሊዮን ህዝብ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን የ‹‹ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል›› ይመርቁታል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መሪዎቹ ተሸኙ‼️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐብይ_አህመድ ለኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና ለሶማሊያዉ ፕሬዝዳንት መሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ መሀመድ ባሕር ዳር ዓለም አቀፍ አውሮፕላን በመገኘት ሽኝት አደረጉላቸው፡፡ መሪዎቹን የአማራ ክልል ከፍተኛ ስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ባሕር ዳር ዓለም አቀፍ አውሮፕላን በመገኘት ሸኝተዋቸዋል፡፡

ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

ወይዘሪት #ብርቱካን_ሚደቅሳ በነገው ዕለት የሀገሪቱ የምርጫ ቦርድ ሀላፊ ሆነው ሊሾሙ መሆኑ ተሰምቷል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ በሚያደርገው ስብሰባ ወሪት ብርቱካንን የምርጫ ቦርዱ ሀላፊ እንዲሆኑ በጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር #ዐብይ_አህመድ መንግስት የሚቀርብለትን ሹመት ድምፅ ይሰጥበታል።

ወይዘሪት ብርቱካን ከሰባት አመታት ስደት በኋላ መንግስት ባደረገላቸው ጥሪ በቅርቡ ወደሀገር ቤት መመለሳቸው ይታወሳል።

ምንጭ፦ wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የጅማ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር #ዐብይ_አህመድ በተገኙበት ዛሬ Dec. 8/2018 ይመረቃል።

©Dan(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ ዩኒቨርሲቲ🔝ዛሬ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #ዐብይ_አህመድ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ተገኝተው 40,000 ተመልካች የሚይዘውን የጅማ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየምና ስፖርት አካዳሚ በይፋ #ይመርቃሉ

ቪድዮ፦ ቢንያም ግርማይ(TIKVAH-ETH)
ፎቶ፦ ናቶሊ(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikahethiopia
''ወንጀለኞቹ ማንም ይሁኑ ማን . . . አድነን ለሕግ ማቅረባችን አይቀሬ ነው'' ጠ/ሚ ዶ/ር #ዐብይ_አህመድ

@tsegabwolde @tikvahethiopia