TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UPDATE የቴድሮስ ካሳሁን የሙዚቃ ኮንሰርተን በተመለከተ ከአዘጋጆቹ መረጃ ለማግኘት ያደረኩት ጥረት አልተሳካም። ለምን ለህዝቡ መረጃ የመቀበያ ስልክ እንዳስቀመጡ እና ስልካቸውን እንደማያነሱ ግራ ያጋባል። ኮንሰርቱ በ3 ይካሄዳል ተብሎ የሚወራውን ወሬም ሊያስተባብል ብቅ ያለም የለም። እስካሁን ግን ኮንሰርቱ ነገ ስለመደረጉ የሚገልፅ ምንም ፍንጭ አልተገኘም። አዘጋጆቹ ይህን መልዕክት ካያችሁት ምላሽ እንድትሰጡበት በትህትና እንጠይቃለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ድጋፉ የቀጠለ ሲሆን ከ3 የTIKAH-ETH ቤተሰብ አባላት 5,270 ብር ድጋፍ ተደርጓል።
.
.
በዚህ አካሄድ አጠቃላይ የህክምና ወጪው ዛሬ ማታ ወይም ነገ ጥዋት ማሟላት ይቻላል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
164,800 ብር እስካሁን የደረሰ ሲሆን በሰዓታት ውስጥ 180,000 ብር እንደሚደርስ እና የማርያም የህክምና ወጪ እንደሚሸፈን እምነታችን ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአፍሪካ ህብረት⬇️

ኢትዮጵያ ወደ አገሪቱ ለሚገቡ አፍሪካውያን ተጓዦች የቪዛ ፖሊሲዋን #ለማቅለል መወሰኗን የአፍሪካ ህብረት አወደሰ፡፡

የህብረቱ ሊቀመንበር #ሙሳ_ፋኪ ማህመት ኢትዮጵያ ቪዛን አስመልክቶ ለምትወስደው እርምጃ እውቅና በመስጠት የቪዛ ስርዓታቸውን ያስተካከሉ ሌሎች የአፍሪካ አገራትንም አመስግነዋል፡፡

ሊቀመንበሩ አፍሪካውያን በአህጉራቸው ውስጥ እንደልባቸው የሚዘዋወሩበት ጊዜ እሩቅ እንደማይሆን ገልፀው ሌሎች የአፍሪካ አገራትም የቪዛ ስርዓታቸውን እንዲያሻሽሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የሁለቱ ምክር ቤቶችን ስራ መጀመር አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር ከያዝነው አመት ጀምሮ የየትኛውንም የአፍሪካ አገር ፓስፖርት ለያዘ ግለሰብ ኦን አራይቫል ቪዛ የሚያገኝበት ሁኔታ እንደሚመቻች መግለፃቸው ይታወቃል፡፡

እኤአ 2018 ጥር ላይ የተፈረመውን ስምምነት እስካሁን 32 የአፍሪካ ህብረት አባል አገራት የፈረሙት ሲሆን ቀሪ አገራትም እንዲፈርሙ ህብረቱ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

ምንጭ፡- ሺንዋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
AASTU⬆️የነባር እና የአዲስ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት

🔹አዲስ ተማሪዎች፡ ጥቅምት 10,11 ፣ 2011 ዓ.ም

🔹ነባር ተማሪዎች ፡ ጥቅምት 7,8,9 ፣ 2011 ዓ.ም

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚ ጁሴፔ⬆️

ጠቅላይ ሚኒስትር #ጁሴፔ_ኮንቴ መኪና በመገጣጠም የሚታወቀውን የአምቼ ኩባንያን ጎብኝተዋል።

ኩባንያው 70 በመቶ በጣሊያን መንግስት 30 በመቶ ደግሞ በኢትዮጵያ መንግስት ድርሻነት የተቋቋመ ነው፡፡

የጣሊያኑ ጠ/ሚኒስትር የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ #ኤርትራ አቅንተዋል፡፡

ጠ/ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ በጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየው በቦሌ አየር ማረፊያ ሽኝት ተደርጎላቸዋል፡፡

ፎቶ፦ ጠቅላይሚንስትር ፅ/ቤት
ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ምክትል ጠ/ሚ ደመቀ⬇️

በ2011 ዓመት የትምህርት ዘመን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ለማስፈን የተቀናጀ ጥረት መደረግ እንድሚያስፈልግ  ምክትል  ጠቅላይ ሚኒስትር  አቶ #ደመቀ_መኮንን ገለፁ።

በዛሬው ዕለት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት #ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው።

የዘንድሮውን  የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመማር ማስተማር ሂደት ሰላማዊ እና የተረጋጋ ለማድረግ ሁሉም ተዋናይ የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ  ነው ምክትል  ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስታወቁት።

ከተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ከማህበረሰብ የተውጣጡ 1500 ተሳታፊዎች በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት በሚካሄደው የውይይት መድረክ ላይ ታድመዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አጋሮ ከተማ የሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ከጥዋት ጀምሮ ከተማይቱ ውስጥ ውጥረት መኖሩን እየገለፁ ናቸው። ከሰሞኑ የከተማው ነዋሪ በአስተዳደሩ ላይ ያለውን ቅሬታ ሲያሰማ እንደነበር ጠቅሰዋል።

ዝርዝር መረጃ አደራጅቼ አቀርባለሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትኩረት ለአጋሮ‼️

በአጋሮ ያለውን ሁኔታ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ትኩረት እዲሰጠው ነዋሪዎች እየጠየቁ ናቸው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የአሠልጣኝ ስዩም አባተ የቀብር ስነ-ስርዓት በዛሬው ዕለት ከቀኑ 9:00 ሰዓት ሳሪስ በሚገኘው የፃድቁ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ (ሳሪስ አቦ) ቤተክርስቲያን ይፈፀማል።

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጥቁር አንበሳ ተማሪዎች⬆️

"በጥቁር አንበሳ የ4ኛ(C-1) ዓመት ህክምና ተማሪዎች በተቋቋመው Care Charity እና የተማሪ ተወካዮች አስተባባሪነት 13,330 ብር ተሰብስቦ ለእህታችን ተማሪ ማሪያም ተስፋዬ በተከፈተው የሂሳብ ደብተር ቁጥር አስገብተናል። እህታችንን ፈጣሪ ሙሉ በሙሉ ድና ወደ ትምህርቷ ተመልሳና ወገኖቿን በሞያዋ ስትረዳ ለማየት እንዲያበቃን እንመኛለን። #Care_Charity_Black_Lion"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ⬆️የሀዋሳ ከተማ ወጣቶች እና የቅርብ ጓደኞቿ ለማርያም ተስፋዬ ያሰባሰቡትን 31,822 ብር ገቢ አድርገዋል።

ወጣቶቻችን እድሜውን ከጤና ጋር አብዝቶ ይስጣችሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የታዳጊዋ የህክምና ተማሪ ማርያም ተስፋዬ የህክምና ወጪን በተመከት ያለውን አጠቃላይ ገንዘብ በደቂቃ ውስጥ አሳውቃላሁ።

ባለኝ መረጃ ሙሉ የህክምና ወጪዋን የሚሸፍን ገንዘብ ተገኝቷል!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia