TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዶክተር አብይ ዛሬ የሰሩት ስራ⬆️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የነበሩትን የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ከሸኙ በኋላ የብሔራዊ የክብር ዘብ አባል የደንብ ልብስ #ሲያስተካክሉ ታይተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሌሎች የአገሪቱ ላመሥልጣኖች ጋር ሆነው ወደ መኪናቸው እየተመለሱ ሳለ በድንገት ከቀይ ምንጣፍ ወጥተው የአንድ የክብር ዘበኛ አባል የደንብ ልብስ አለባበስን ሲያስተካክሉ አብረዋቸው የነበሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች #ሲደመሙ ተስተውለዋል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከትናንት በስቲያ ቤተ መንግስት በመሄድ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጥያቄ ያቀረቡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት #ይቅርታ ጠየቁ።

የሰራዊት አባላቱ ጥያቄውን ያቀረቡበት መንገድ ህግና ስርዓትን ያልተከተለ በመሆኑ መንግስትና ህዝብን ይቅርታ ጠይቀዋል።

አባላቱ ባለፉት ሁለት ቀናት ከኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ሞቱማ መቃሳ እና ከኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ሰአረ መኮንን ጋር ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅት ጥያቄያቸውን ለበላይ አካል መቅረብ ሲገባቸው ቤተ መንግስት ድረስ በመሄድ ማቅረባቸው ህግን ያልተከተለ መሆኑን ገልጸዋል።

ምንጭ፦ ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቴዎድሮስ ካሳሁን የሙዚቃ ኮንሳርት ጥቅምት 24 በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማሳሰብያ‼️

የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የከፍተኛ ትምህርት ምደባ ካካሄደ በኋላ ቅይይር የማይሰራ መሆኑ እያታወቀ ከዩንቨርሲቲ ዩንቨርሲቲ ቅይይር ማድረግ ለምትፈልጉ ተማሪዎች ዝውውር ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን የሚል ሀሰተኛ መረጃ የኤጀንሲውን የፌስ ቡክ ገጽ አስመስለው በመክፈት እየለቀቁ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም ኤጀንሲው ማንኛውንም ዓይነት ከዩኒቨርስቲ ዩኒቨርስቲ የማዘዋወር ስራ የማይሠራ መሆኑን እየገለጽን ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች ከሐሰተኛ መረጃዎች እራሳችሁን እንድትጠብቁ መልዕክት እናስተላልፋለን፡፡

ምንጭ፦ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተዎች ኤጀንሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በአጋሮ ከተማ እስካሁን የአንድ ሰው ህይወት እንዳለፈ የከተማው ነዋሪዎች ገልፀውልኛል። ከተማይቱ ውስጥ እንቅስቃሴ የለም። መንግስት ችግሩን እንዲፈታና ውጥረቱን እንዲያረግብ ነዋሪዎች ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር ዐብይ⬆️ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በሞተር የሚሰሩ 36 ዊልቸሮችን ለአካል ጉዳተኞች ለገሱ።

ፎቶ፦ አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
240,346 ብር!

ተጠናቋል‼️የማርያም የህክምና ወጪን በተመለከተ አሁን ያለውን የገንዘብ መጠን እንደሚከተለው አሳውቃለሁ፦

🔹240,346 ብር
🔹ታሳቢ ተደርጎ እንቅስቃሴ ሲደረግ የነበረው 180,000 ብር

የታዳጊዋ ህክምና እንዲያሳካ ወደ ሙሉ ጤንነቷዋ ተመልሳ የሀገር ተስፋና የኛ ሀኪም እንድትሆን እንመኛለን።

🙏የተሰበሰበው ገንዘብ አጠቃላይ የህክምና ወጪዋን ከመሸፈን አልፎ ለመድሃኒት ግዢ እና ለሌሎች ከጤናዋ ጋር ለተገናኙ ገዳዮች ይውላል።

ክብር ለናተ!! ክብር በየከተማው ላላችሁት ወጣቶች!! ጓደኞቿ!! በተለያየ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ያላችሁ ተማሪዎች እና መምህራን!

እኔ ምንም ቃላት የለኝም!
ለሁላችሁም ፈጣሪ ረጅም እድሜና ጤና ይስጣችሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተጨማሪ‼️

"የጥቁር አንበሳ የዘንድሮ ተመራቂ ሀኪሞች #ሀኪም_2018 ባደረጉት መዋጮ #30,000 ብር ተሰብስቦ ለእህታችን ተማሪ ማሪያም ተስፋዬ በተከፈተው የሂሳብ ደብተር ቁጥር አስገብተናል። እህታችንን ፈጣሪ ሙሉ በሙሉ ድና ወደ ትምህርቷ ተመልሳና ወገኖቿን በሞያዋ ስትረዳ ለማየት እንዲያበቃን እንመኛለን። #Hakim_2018_Black_Lion!!!"
.
.

እኛም ለማርያም ህክምና አለን ያሉ የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የጤና #ተማሪዎች 3,515 ብር ድጋፍ አድርገዋል። የቀረውን ነገ እናስገባልን ብለውኛል።
.
.
በሌላ በኩል...

ቀደም ብለው የማርየም ጓደኛ የሆኑ ወጣቶች በሀዋሳ እና በሻሸመኔ ከተማ ለማርያም ማሳከሚያ የሚሆን ገንዘብ የማሰባሰብ ስራ እየሰሩ ነበር ስራቸው እስከ እሁድ ድረስ እንደሚቀጥል ገልፀዋል። በመሆኑም በሀዋሳ እና ሻሸመኔ ያለው ነዋሪ ይህን እንዲረዳቸው ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia @tsegabwolde
#update ኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት⬇️

ጥቂት የሠራዊት አባላት ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ሊያነጋግሩን ይገባል በሚል ወደ ቤተ መንግስት የሄዱበት መንገድ ለሠራዊቱ የተሰጡ ክልከላዎችን የተላለፈ መሆኑ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ገለጸ፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ጠቅላይ መምሪያ፣ የምዕራብ ዕዝ፣ የሰሜን ዕዝ፣ የደቡብ ምስራቅ ዕዝ እና የማዕከል ግብረሀይል ጠቅላይ መምሪያዎች ድርጊቱን በማውገዝ መግለጫ ለኢቲቪ ዜና ልከዋል፡፡

በመግለጫቸው እንዳሉትም የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የአገራችን ህዝባች በልማትና በዴሞክራሲ ግንባታ ሂደት በሚያደርጉት ርብርብ ውስጥ የህዝባችን ሰላም የሚያውክና የአገራችንን ሉዓላዊነት የሚደፍር አደጋ ሲያጋጥም በፈፀምነው ጅግንነት እና ህዝባዊነት መንግስትና
ህዝብ የሰጡንን የአገርና የህዝብ ደህንነት የመጠበቅ ግዳጃችንን በአግባቡ ስንወጣ ቆይተናል፡፡

የአገራችንና የህዝባችንን ክብር በጐረቤት አገሮች በአህጉር እና በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍ እንዲል ያደረገና የተደነቀ፣ አካባቢያዊና አለምአቀፉዊ ግዳጃችንን በብቃት መወጣት ችለናል፡፡

ሠራዊታችንን ህገ መንግስቱን በማክበርና በማስከበር በህግ የበላይነት ማመንና በህግ ማዕቀፍ ብቻ መስራት፣ የሲቪል ባለስልጣናትን ማክበር፣ህዝብን ማስከበር እና በአጠቃላይ ኘሮፎሽናሊዝም፣ ህዝባዊነት፣ ጀግንነት፣ ውጤታማነት የሠራዊታችን ልዩ መገለጫዎች ናቸው ብለን እናምናለን፡፡

በመሆኑም ረቡዕ መስከረም 30 ቀን 2011 ዓ.ም ጥቂት የሠራዊት አባላት ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ሊያነጋግሩን ይገባል በሚል ወደ ቤተ መንግስት የሄዱበት መንገድ በኢፌዲሪ ህገ መንግስት ለሠራዊቱ የተሰጡ ክልከላዎችን የተላለፈ በመሆኑ ፍፁም ኢ-ህገመንግስታዊ ስለሆነ በፅኑ #እናወግዘዋለን፡፡

ድርጊቱም የሠራዊታችንን ባህሪ እና የተቋሙን አሠራር ያልተከተለና የማይገልፅ የጥቂት አባላት የተሳሳተ እንቅስቃሴ እንጂ እኛን #የማይወክል መሆኑኑ እንገፃለን፡፡

አሁንም ህገ መንግስቱን በማክበርና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለማፍረስ የሚንቀሳቀሱ የውጭና የውስጥ ሃይልን በመመከት የአገራችንን እና የህዝባችን ሉዓላዊነት የማስጠበቅ ግዳጃችን ላይ ፍፁም የማንዘናጋ መሆኑንም እንገፃለን፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሰላም ሚኒስቴር⬇️

ለመጀመሪያ ጊዜ የሚቋቋመው የ’ሰላም ሚኒስቴር’ ተቋም በአገር ውስጥ ሰላም እና የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን የሚሰራ መሆኑን ጠ/ሚኒስቴር ጽ/ቤት ገለጸ፡፡

የጠ/ሚኒስቴር ጽ/ቤት ሚኒስቴር ልዩ ሃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ እንደገለጹት አዲስ የሚቋቋመው የሰላም ሚኒስቴር በሕዝቡ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ በጋራ መገንባት እንዲቻል ትኩረት ይሰጣል።

በፖሊሲ ደረጃ ሰላምን በዋና አጀንዳነት የሚመራ ተቋም ያስፈልጋል ተብሎ በመታመኑ እንዲቋቋም መወሰኑንም አቶ ፍጹም ለኢዚአ ገልጸዋል።

የ”ሰላም ሚኒስቴር” ሰላም ላይ ያተኮሩ የተለያዩ ተግባራትን በማቀናጀት የሚመራ እንደሚሆንም ነው የተናገሩት።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ “የሰላም ሚኒስቴር” የተባለ አዲስ ተቋም እንዲቋቋም በረቂቅ አዋጁ ላይ ማካተቱ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ኤዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
University Reg.⬇️

"Hi tsegish, i have confirmed that the education minister have just given the date to all universities but some universities are providing special cases for education minister and now these universities are also trying to have a different registration dates like gambella universities too!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH-ከዩኒቨርሲቲዎች የሚመጡላትን የቅበላ ቀናት የሚያቀርብ ይሆናል። በመሆኑም ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ትክክለኛ ገፃችሁን እና ድረ ገፃችሁን ጎብኙ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia