TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የአፍሪካ ህብረት⬇️

ኢትዮጵያ ወደ አገሪቱ ለሚገቡ አፍሪካውያን ተጓዦች የቪዛ ፖሊሲዋን #ለማቅለል መወሰኗን የአፍሪካ ህብረት አወደሰ፡፡

የህብረቱ ሊቀመንበር #ሙሳ_ፋኪ ማህመት ኢትዮጵያ ቪዛን አስመልክቶ ለምትወስደው እርምጃ እውቅና በመስጠት የቪዛ ስርዓታቸውን ያስተካከሉ ሌሎች የአፍሪካ አገራትንም አመስግነዋል፡፡

ሊቀመንበሩ አፍሪካውያን በአህጉራቸው ውስጥ እንደልባቸው የሚዘዋወሩበት ጊዜ እሩቅ እንደማይሆን ገልፀው ሌሎች የአፍሪካ አገራትም የቪዛ ስርዓታቸውን እንዲያሻሽሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የሁለቱ ምክር ቤቶችን ስራ መጀመር አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር ከያዝነው አመት ጀምሮ የየትኛውንም የአፍሪካ አገር ፓስፖርት ለያዘ ግለሰብ ኦን አራይቫል ቪዛ የሚያገኝበት ሁኔታ እንደሚመቻች መግለፃቸው ይታወቃል፡፡

እኤአ 2018 ጥር ላይ የተፈረመውን ስምምነት እስካሁን 32 የአፍሪካ ህብረት አባል አገራት የፈረሙት ሲሆን ቀሪ አገራትም እንዲፈርሙ ህብረቱ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

ምንጭ፡- ሺንዋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia