TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
እንኳን በጉራ!
.
.
የሌለህን አለኝ ሳታውቅ አዋቂነኝ፣
እንዳከብርህ ብቻ ውሸት አትንገረኝ።
ከሌለህ ነውር አይደል ካለህ ለራስህ ነው፣
እኔ የማከብርህ #በሰውነትህ ነው።

እንኳን #በጉራ ደረት ተነፍቶ፣
አልቻለውም ሰው አንገቱን #ደፍቶ
ዝቅ እያሉ ነው ተናንሶ ኑሮ፣
ላካበደማ አይወን ዘንድሮ። (2)
ትልቅ #ፈጣሪ ነው ትልቅ ለዘላለም፣
የሰው ትልቅ የለም!
የእድሜ ሰረገላ የድሜ ሰረገላ
ሄዶም መቶ አይሞላም! (2)

እኔ ምን አውቃለው #ካወክ አሰተምረኝ፣
#ንቀቱን ተውና ይሄ ይሄ ነው በለኝ።
ያን ያንን ሳታረገ #ብትመፃድቅም
ሆዴን ልሙላ በዬ #ብሞት ላንተ አልሰገድም!
ወርቅ በሰው ልጅ የተወደደው፣
እራሱን አቃሎ ጭቃ መሰሎ ነው።
ከፍ ከፍ ያለው በባዶ ሜዳ፣
አጅሬ ገለባ ወድቆ ተጎዳ።
ወርቅ በሰው ልጅ የተወደደው፣
እራሱን አቃሎ ጭቃ መሰሎ ነው።
ከፍ ከፍ ያለው አጅሬ ገለባ እዩት ሲጎዳ!
ትልቅ ፈጣሪ ነው ትልቅ ለዘላለም፣
አሃ አሃ የሰው ትልቅ የለም!
የእድሜ ሰረገላ የድሜ ሰረገላ
ሄዶም መቶ አይሞላም።

እንኳን በጉራ ደረት ተነፍቶ
አልቻለውም ሰው አንገቱን ደፍቶ
ዝቅ እያሉ ነው ተናንሶ ኑሮ
ላካበደማ አይሆን ዘድሮ። (2)
ትልቅ ፈጣሪ ነው ትልቅ ለዘላለም፣
አሃ አሃ... የሰው ትልቅ የለም!
የእድሜ ሰረገላ፣
ሄዶም መቶ አይሞላ።
የእደሜ ሰረገላ፣
ሄዶም መቶ አይሞላ፣
ትልቅ ፈጣሪ ነው ትልቅ ለዘላለም
አሃ አሃ ....የሰው ትልቅ የለም።

©ድምጻዊ - አብዱ ኪያር

#ቲክቫህኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia