TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.91K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የ14 ዐመቷ ታዳጊ ህይወቷ አለፈ⬆️

አንዲት የ14 አመት ታዳጊ ከተደፍረች በኋላ በተደፋባት #አሲድ መሰል ንጥረ ነገር ሕይወቷ አለፈ።

#ጫልቱ_አብዲ የተባለችውና ከምስራቅ ሐረርጌ በደኖ ወደ ሐረር መጥታ የቤት ሰራተኛ የነበረችው ይህች ታዳጊ የተደፈረችውና ሕይወቷ ያለፈው #በአሰሪዋ እንደሆነም ተመልክቷል።

ስሙ ያልተጠቀሰው ይህ ግለሰብ ታዳጊዋን ከደፈራት በኋላ የአሲድ ጥቃት እንደፈጸመባትም ተመልክቷል።

ከጥቃቱም በኋላ በስቃይ ውስጥ እያለች በቤት ተደብቃ እንድትቀመጥ ማድረጉም ታውቋል። ታዳጊዋ ከመሞቷ በፊት ለፖሊስ በሰጠችው መግለጫ እንዳመለከተችው ሰውነቷ መሽተት ሲጀምር ወደ ሆስፒታል ሊወስዳት ተገዷል።

በአዲስ አበባ የካቲት 12 ሆስፒታል በሕክምና ላይ እያለች ሕይወቷ ላለፈው የ14 አመቷ ታዳጊ ጫልቱ አብዲ ትላንት በየካቲት 12 ሆስፒታል #የሻማ ማብራት ስነስርአት ተካሂዶላታል።

ታዳጊዋን #በመድፈርና በማቃጠል የተጠረጠረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር የዋለ ቢሆንም እስካሁን ግን ፍርድ ቤት አለመቅረቡ ታውቋል።

©ኢሳት
ፎቶ፦ ናቲ(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሁላችንም የTIKVAH-ETHIOPIA ቤተሰብ አባላት ለእህታችን #ጫልቱ ፍትህ በጋራ ልንቆም ይገባል። በሴቶች ላይ የሚደርስን ጥቃት በፍፁም ልንታገስ አይገባም።
.
.
ከዚህ በታች ያለውን ፅሁፍ በፌስቡክ ገፃቹ ላይ በመለጠፍ ተፅህኖ እንፍጠር!
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
#ፍትህ_ለጫልቱ!!
#JUSTICE_FOR_CHALTU!!

ሴት ሰው ናት!
ሴት ሀገር ናት!
ሴትን #መድፈር ሀገርን መድፈር ነው!

#ፍትህ_ለጫልቱ!!
#JUSTICE_FOR_CHALTU!!

📌በእህታች #ጫልቱ ላይ የደረሰው በደል ልባችንን የሰበረው እንዲሁም ለዚህች ምስኪን ኢትዮጵያዊት ፍትህ ይገባታል የምትሉ ይህንምልክት በመጫን በአንድ ላይ ድምፃችንን እናሰማ።

በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ በደሎችን አንታገስም!
#ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ወይዘሪት #ጫልቱ_ታከለ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ተይዛ በሻቡ ከተማ መታሰሯን የአይን እማኞች ተናገሩ። ጫሉት ከቤተሰቦቿ ቤት ነው በቁጥጥር ስር የዋለችው፤ ከሷ በተጨማሪ ቢያንስ 5 ሌሎች ሰዎች መታሰራቸው ተረጋግጧል። ወይዘሪት ጫልቱ በሽብርተኝነት ተጠርጥራ ለ8 አመታት በዕስር የከቆየች በኅላ ከወራት በፊት ነበር የተፈታችው።

ምንጭ፦ አዲስ ስታንዳርድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሆሮ ጉዱሩ~ወለጋ‼️

በኦሮሚያ ክልል በሆሩ ጉድሩ ወለጋ ዞን በሻምቡ ከተማ በርካታ ሰዎች #እየታሰሩ መሆኑን ነዋሪዎች ገለጹ። በትላትናው ዕለት በተደጋጋሚ ለእስራት የተዳረገችው #ጫልቱ_ታከለን ጨምሮ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን እና እስሩ ዛሬም መቀጠሉን ተናግረዋል።

በምዕራብ አሮሚያ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተከሰተውን ግጭት ለመከላከል የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ትላንት እንዳስታወቀው በሰዎች ሞት እና መፈናቀል የተጠረጠሩ 171 ግለሰቦች የሆሮ ጉድሩ ዞንን ጨምሮ በምዕራብ ኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በቁጥጥር ስር አውሏል።

የሻምቡ ከተማ ነዋሪ እንደገለጹት በከተማይቱ ከአንድ ሳምንት በላይ በእስር የቆዩ ሰዎች አሉ። በሆሮ ጉድሩ ፖሊስ መምሪያ ውስጥ ወደ 30 የሚጠጉ ሰዎች በእስር ላይ እንደሚገኙ እና ጃንሜዳ በተባለው የከተማይቱ ስፍራም ወጣቶች ተይዘው እንደሚታሰሩ ተናግረዋል። በቁጥጥር ስር ከዋሉት ሰዎች የተወሰኑቱ የታሰሩት “ለኦነግ ስንቅ ሰጥታችኋል” በሚል ምክንያት እንደሆነ መስማታቸውንም አክለዋል። የከተማይቱ ነዋሪዎች እታሰራለሁ በሚል ፍርሃት ውስጥ መሆናቸውን አስረድተዋል።

“እስካሁን ምንም ግጭት የለም ግን ፍርሃት አለ። ሰው እንደፈለገ መንቀሳቀስ አይችልም። ሁለት ሆነው አብሮ መቆም፣ መሄድ አይችልም። በየቦታው ፍተሻ ነው። አሁን ከተማ ውስጥ ያለው በጣም የሚያስፈራ ድባብ ነው” ሲሉ የከተማይቱ ነዋሪ በሻምቡ ያለውን ሁኔታ ገልጸውታል። “ከ12 ሰዓት በኋላ መንገድ ላይ የተገኘ ሁሉ ይደበደባል፤ ይታሰራል። በጣም አስፈሪ እና አስጊ ነው” ብለዋል።

በሻምቡ ትላንት በቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥ ከዚህ ቀደም ለሶስት ጊዜያት ለእስር የታደረገችው ጫልቱ ታከለ እንደምትገኝበት ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ አንድ የቤተሰብ አባል ለDW ተናግረዋል። ከእርሷ ጋር ሶስት የጎረቤት እና የሰፈር ሰዎች መታሰራቸውንም ገልጸዋል።

ጫልቱ ትላንት ጠዋት በኦሮሚያ አድማ በታኝ ፖሊሶች ተወስዳ ከሰዓታት በኋላ ብትመለስም በድጋሚ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ገደማ መብራት ኃይል በተሰኘው የከተማይቱ ክፍል ከሚገኝ መኖሪያ ቤቷ ተይዛ መታሰሯን አብራርተዋል። በቁጥጥር ስር ያዋሏት የክልሉ ፖሊሶች “ከኮማንድ ፖስት ነው የመጣነው” ከማለት ውጪ ለእስር ያበቃት ምክንያት ምን እንደሆነ አለመግለጻቸውንም አስረድተዋል።

ፖሊሶቹ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዳልያዙ እና በመከላከያ ሰራዊት አባላት ታጅባ ወደ ሆሩ ጉድሩ ፖሊስ መምሪያ እንድትወሰድ አድርገዋል ብለዋል። ስንቅ ለማቀበል ወደ ፖሊስ መምሪያው ያመሩት ቤተሰቦቿ ትላንት ማምሻውን እና ዛሬ ጠዋት እንዳነጋገሯት እኚሁ የቤተሰብ አባል ተናግረዋል።

ጫልቱ ከዚህ ቀደም በ1997 ዓ. ም. የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በነበረችበት ወቅት ተይዛ ለአንድ ዓመት ታስራ ተፈትታለች። በ2000 ዓ. ም. በኦነግ አባልነት ተጠርጥራ በድጋሚ ከተያዘች በኋላ 12 ዓመት ተፈርዶባታል። ስምንት ዓመት ከአንድ ወር ገደማ ታስራ በ2009 ዓ.ም. የተፈታችው ጫልቱ ብዙም ሳትቆይ እንደገና ወደ እስር ቤት እንድትመለስ ተደርጓል። ለሶስተኛ ጊዜ ለ11 ወራት በእስር የቆየችው ጫልቱ በየካቲት 2010 ዓ. ም. የፖለቲካ እስረኞች ከእስር ሲለቀቁ እርሷም የዕድሉ ተጠቃሚ ሆናለች።

ምንጭ:- የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የአነግ #አባል ስለሆነ የታሰረ #የለም" የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን
.
.
በፖለቲካ ምክንያት ታስረው ከነበሩና ኋላ ከተፈቱት መካከል የሆነችው #ጫልቱ_ታከለ ከሶስት ቀን በፊት በምዕራብ ወለጋ ሻምቡ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ተይዛ እስር ላይ ትገኛለች።

ጫልቱ ብቻ ሳትሆን የቤጊ ወረዳ አባ ገዳ ጌታቸው ተርፋን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ሰዎች እንደታሰሩ የጫልቱ እናት ወ/ሮ አስካለ አብዲ ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ማክሰኞ ማታ ቤት ውስጥ የመከላከያ ሃይል አባላት መጥተው በቁጥጥር ስር እንደዋለች ተናግረዋል።

በምን ምክንያት የታሰረች ይመስልዎታል ተብሎ ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄም የታሰረችበትን ምክንያት በትክክል ባያውቁም "ኦነግ ስለሆነች ይመስለኛል። ሌላ ጥፋት ያለባት አይመስለኝም። ለራሷም ስንት አመት ተሰቃይታ ነው የወጣችው" ብለዋል።

ጫልቱ ከአመታት በፊት የሃገርን ፖለቲካና የግዛት አንድነት በመንካት በሚል ተከሳ 12 አመት ተፈርዶባት 8 ዓመት ከ45 ቀን ታስራ በአመክሮ ወጥታለች።እንደገና በሽብር ተከሳ 11 ወር ከታሰረች በኋላ መንግስት ከወራት በፊት እስረኞችን ሲለቅ እሷም ክሷ ተቋርጦ ከእስር መውጣቷ የሚታወስ ነው።

ጫልቱ ወደ ትውልድ ቦታዋ ሻምቡ ከሄደች አንድ ወር እንዳስቆጠረች የሚናገሩት እናቷ በሻምቡ ባለው የኦነግ ፅህፈት ቤት ሊቀ መንበር ሆና ለአንድ ሳምንት ሰርታለች።
የኮማንድ ፖስቱን መምጣት ተከትሎ ቤቷ እንዳለችም ወ/ሮ አስካለ ጨምረው አስረድተዋል።

የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዴሬሳ በበኩላቸው ግለሰቦቹ የታሰሩት በወንጀል ተጠርጥረው እንጂ የኦነግ ወይም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ስለሆኑ አይደለም ብለዋል።

"የኦነግ አባል ስለሆነ የታሰረ የለም፤ የፖለቲካ ፓርቲ አባል መሆን ለአንድ ወንጀል ሽፋን መሆን አይችልም" ብለዋል።

እስካሁን ለምን ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡም ተጠይቀው " ያለኝ መረጃ በቅርቡ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ነው" ብለዋል።

ከባለፉት ጥቂት ወራት ጀምሮ በምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢ አለመረጋጋትና ግጭቶች የበረከቱ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ መከላከያ ሰራዊት በአካባቢው ተሰማርቷል።

በምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢ የተሰማሩ ታጣቂዎች በሰላማዊ መንገድ ሊታገሉ የመጡ ናቸው በሚል የክልሉ ፀጥታ ኃይል የሚደርሱ ግድያዎችና ዘረፋዎች ማስቆም አቅቶት እንደነበር የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታ ማዦር ብርሃኑ ጁላ የመከላከያ ሚኒስቴርን ግማሽ አመት የስራ ክንውን ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማክሰኞ እለት ባቀረቡበት ወቅት ተናግረዋል።

በአካባቢው ፖሊሶችን ጨምሮ ብዙ ሰዎች መገደላቸውንና ዝርፊያዎች እንደደረሱ የተናገሩት ጄኔራል ብርሃኑ "በውትድርና ዘመኔ በራስ ሕዝብ ላይ ጭካኔ የተሞላበት ዘግናኝ ጥቃት ተፈፅሞ ያየሁት በምዕራብ ወለጋ ነው" ብለዋል።

ምንም እንኳን የአካባቢውን ፀጥታ ማስከበር ሃላፊነት የክልሉ ኃይል ቢሆንም ነገሩ ከአቅም በላይ በመሆኑ የመከላከያ ሰራዊት በአካባቢው ተሰማርቶ የማረጋጋትና ወደ ሰላም የማምጣት ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ምንጭ፦ BBC አማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጫልቱ ታከለ ተፈታች‼️

ላለፉት ስድስት ቀናት እስር ላይ የቆየችው #ጫልቱ_ታከለ ተፈታች። ቤተሰቦቿ ለጀርመን ራድዮ እንደተናገሩት ጫልቱ ከእስር የተፈታችው ዛሬ ሰኞ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ገደማ ነው።

ጫልቱ በኦሮሚያ ክልል በሆሩ ጉድሩ ወለጋ ዞን በሻምቡ ከተማ ከሚገኘው የቤተሰቦቿ ቤት በጸጥታ ኃይሎች ተወስዳ የታሰረችው ባለፈው ማክሰኞ ነበር። በዕለቱ ከእርሷ ጋር ሶስት የጎረቤት እና የሰፈር ሰዎች መታሰራቸው ይታወሳል።

በምዕራብ አሮሚያ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተከሰተውን ግጭት ለመከላከል የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት በሰዎች ሞት እና መፈናቀል የተጠረጠሩ 171 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ባለፈው ሳምንት አስታውቆ ነበር። ሰዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሆሮ ጉዱሩን ጨምሮ በምዕራብ ኦሮሚያ ከሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች መሆኑ ተገልጿል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia