TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰበር ዜና📌 አቶ #ደመቀ_መኮንን የህዝቡንና የአባላትን ክብር በመጠበቅ የጉባኤውን ሀሳብ ተቀብለው በሀላፊነት #ለመቀጠል ተስማሙ፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን በክብር #ቢሰናበቱ ተብሎ የቀረበውን ሀሳብ ጉባኤው በመቃወሙ ነው ባሉበት እንዲቀጥሉ የተደረገው፡፡

ብአዴን ለማዕካዊ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ባይወዳደሩ ያላቸውን 12 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የቀረበውን መነሻ ተቀብሎ አጸደቀ፡፡

ለትምህርት የሚላኩ እና አሁን በትምህርት ላይ የሚገኙና የተሰናበቱ:-

• አቶ ዓለምነው መኮንን
• አቶ ለገሰ ቱሉ
• አቶ ጌታቸው ጀምበር
• አቶ ኢብራሂም ሙሀመድ
• አቶ ደሳለኝ አምባው እና
• ወይዘሮ ባንቺ ይርጋ መለሰን ባይወዳደሩ ብሎ መነሻ አቅርቧል፡፡

በክብር የተሰናበቱ፡-

• አቶ ከበደ ጫኔ
• አቶ መኮንን የለውምወሰን
• ወይዘሮ ፍሬህይወት አያሌው እና
• አቶ ጌታቸው አምባየን በክብር ቢሰናበቱ ብሎ አቅርቧል፡፡

በአምባሳደርነት እያገለገሉ ያሉ እና የተሰናበቱ፡-

• አቶ ካሳ ተክለብርሀንና
• ወይዘሮ ዘነቡ ታደሰን ከውድድሩ ውጭ ቢሆኑ ብሎ መነሻ አጸድቋል፡፡

ጉባኤው ዛሬ ጠዋት 1፡30 የተሰየመ ሲሆን 65 አባላት ያሉትን የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia