TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ🔝በአማራ ክልል #ደብረብርሃን ከተማ የተዘያዙት 52 ህገወጥ የጦር መሣሪያዎች ከላይ በፎቶው የምትመለከቷቸው ናቸው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሻሸመኔ
#ሀዋሳ
#ነቀምት
#አሰላ
#አዲስአበባ
#ሽሬ
#ደብረብርሃን
#ወላይታሶዶ
#አርባምንጭ
#ጅግጅጋ
#አዳማ
#ድሬዳዋ
#ባህርዳር
#መቐለ
#ሀረር
#ጎንደር

ከሌሎች በርካታ ከተሞች ከሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች የSAT ውጤት ያልጠበቁት እንደሆነ በመግለፅ ቅሬታቸው እያሰሙ ይገኛሉ። የሚመለከተው አካል ማብራሪያ እንዲሰጥበትም ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የTIKVAH-ETH #የStopHateSpeech ሀገር አቀፍ ዘመቻዎች/በዩኒቨርሲቲ ደረጃ/ና በየተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ውስጥ የተደረጉ ጉብኝቶችን ለመከታተል #የዩትዩብ ቻናላችንን ይጎብኙ!

#ሀረማያ #ጅማ #ወልቂጤ #ሀዋሳ #ወላይታ_ሶዶ #አርባምንጭ #መቐለ #ዋቻሞ #ወሎ #ደብረብርሃን #ወልዲያ

Watch ""የአንድ እናት ልጆች ነን" በመቐለ ዩኒቨርሲቲ #TIKVAH_ETHIOPIA" on YouTube
https://youtu.be/qjyt56okb3U
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው።

#ጎንደር_ዩኒቨርሲቲ

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 6 ሺህ 574 ተማሪዎችን ዛሬ እያስመረቀ ይገኛል፡፡

በ87 የመጀመሪያ እንዲሁም በ67 የድህረ ምረቃ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ነው የሚያስመርቀው፡፡

በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የውኃ መስኖ እና ኢነርጅ ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ተገኝተዋል፡፡

#ደብረታቦር_ዩኒቨርሲቲ

የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎቹን እያስመረቀ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው ለስምንተኛው ዙር ነው ተማሪዎቹን እያስመረቀ የሚገኘው።

#ቦንጋ_ዩኒቨርሲቲ

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ 2ኛ Batch ተማሪዎች በዛሬው ዕለት እያስመረቀ ይገኛል።

#ደብረብርሃን_ዩኒቨርሲቲ

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ13ኛ ዙር በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያስተማራቸውን በ2ኛ ዲግሪ 231 ተማሪዎችን እና በ3ኛ ዲግሪ አንድ ተማሪ እያስመረቀ ነው።

#ኮተቤ_ሜትርፓሊታን_ዩኒቨርሲቲ

የኮተቤ ሜትርፖሊታን በተለያየ የትምህርት ክፍሎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።

ዩንቨርሲቲው በዛሬው እለት ያስመረቃቸው በመጀመሪያና ሁለተኛ ድግሪ ወንድ 448 ሴት 135 በድምሩ 583 ተማሪዎች ናቸው።

#ቅድስተ_ማርያም_ዩኒቨርሲቲ

የቅድስተ ማርያም ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በድህረ ምረቃ ያሰለጠናቸውን 636 ተማሪዎችን በኦሮሞ ባህል ማዕከል አስመርቋል።

አጠቃላይ ከተመረቁት ውስጥ 322 ወንዶች 314 ደግሞ ሴቶች ናቸው።

#ሀራምቤ_ዩኒቨርሲቲ

ሀራምቤ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ ትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን 3683 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነዉ።

ዩኒቨርሲቲው ለ18ኛ ዙር ነው ተማሪዎችን እስመረቀ የሚገኘው።

ምንጭ፦ ኢፕድ፣ ዋልታ፣ አሚኮ፣ የዩኒቨርሲቲዎች ገፅ

@tikvahuniversity
#ደብረብርሃን

በደብረ ብርሃን ከተማ ከ1 ሺህ 500 በላይ ግለሰቦች በሕገ-ወጥ መንገድ በቤት ማኅበር ተደራጅተው እንደተገኙ የከተማው አስተዳደር አስታወቀ።

በደብረ ብርሃን ከተማ በተለምዶ 633ቱ የቤት ኅብረት ስራ ማኅበራት በሚል ከተደራጁና ዕውቅና ከተሰጣቸው ማህበራት ውስጥ ከ1 ሺህ 500 በላይ ግለሰቦች በህገወጥ መንገድ ተደራጅተው ተገኝተዋል።

ይህን የተገለፀው የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ም/ ከንቲባ አቶ ደስታ አንዳርጌ ከከተማና ከቀበሌ አመራሮች ጋር በማኅበራቱ አደረጃጀት ዙሪያ ውይይት ባካሄዱበት ወቅት ነው።

633ቱ ማህበራት ሲደራጁ 73 የተለያዩ ቦታዎቸ ክፍት የነበሩ ቢሆንም በ65ቱ ክፍት ቦታዎች 1 ሺህ 408 ሰዎች በህገወጥ መንገድ በመደራጀታቸው የከተማው ከንቲባ ኮሚቴ ማህበራቱ ሙሉ በሙሉ እዲሰረዙ መወሰኑ ተገልጿል።

በቀሪ 560 ማህበራት ውስጥ 110 ግለሰቦች በህገወጥ መንገድ ተደራጅተው ተገኝተዋል ያሉት ከንቲባው እነዚህ ግለሰቦች ማሕበራቱ ሳይፈርሱ ግለሰቦችን ብቻ እንዲወጡ መወሰኑን አስረድተዋል።

አሁንም መረጃ የማጣራት ስራው ቀጣይነት እዳለው የገለፁት ከንቲባው በዚህ ህገወጥ ድርጊት ውስጥ የተሳተፉ አካላትን በህግ ለመጠየቅ ይሰራል ብለዋል።

በውይይቱ ላይ በማኅበራት ከተደራጁ ግለሰቦች መካከል ፦
- በከተማዋ የማይኖሩ ፣
- መሸኛ ያላመጡ ፣
- ሐሰተኛ የጋብቻ ፍቺ የፈጸሙ ፣
- ሐሰተኛ መሸኛ ያመጡ እና ባልተሟላ መረጃ የተደራጁ መኖራቸው ተመልክቷል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በዚህ ህገ-ወጥ ድርጊት የተሳተፉ አካላት ፖለቲካዊ ፣ አስተዳደራዊ እና ህጋዊ ርምጃ ሊወሰድባቸው እንደሚገባ አስተያየት ሰጥተዋል።

መረጃው ከደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#DebreBirhan በደብረ ብርሃን ከተማ #ከነገ ጀምሮ የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች እና የደብረ ብርሃን ከተማ መታወቂያ ካላቸው ግለሰቦች ውጪ በከተማው ውስጥ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደማይቻል ከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ፡፡ አስተዳደሩ ይህን ውሳኔ ያሳለፈው ፥ " በከተማው በተለያዩ አካባቢዎች ሰርጎ ገቦች ገብተው አካባቢን የማጥናትና መረጃ የመስጠት ስራ እየሰሩ እንደሆነ ስለተደረሰበት ሰርጎ ገቦችን…
#ደብረብርሃን

" ... ድጋፍ ይዘው መምጣት የሚፈልጉ ክልከላው አይመለከታቸውም ፤ ይህንን አውቀው ወደ ከተማው መምጣት ይችላሉ " - አቶ ደስታ አንዳርጌ

በደብረ ብርሃን ከተማ የቀን እንቅስቃሴ ገደብ አስመልክቶ ተጨማሪ መልዕክት ከከተማው ከንቲባ ተላልፋል።

የደብረ ብርሃን ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ደስታ አንዳርጌ ፥ " የአሸባሪው ቡድን አባላት ከተፈናቃዮች ጋር ተመሳስለው ወደ ከተማው በመግባት የሀሰት ፕሮፓጋንዳ በመንዛትም ሆነ በሌሎች መንገዶች የከተማውን ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዳያውኩ እንዲሁም ለተፈናቃዮችም ሆነ ለከተማው ህዝብ ደህንነት ሲባል ከህዳር 16 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የቀን እንቅስቃሴ ማድረግ የሚችሉት የደብረብርሃን ከተማ መታወቂያ የያዙ ብቻ መሆን እንዳለባቸው የእንቅስቃሴ ገደብ ለመጣል ከተማ አስተዳደሩ ተገዷል " ሲሉ አስታውሰዋል።

ከንቲባው ፥ " የእንቅስቃሴ ገደቡ ዓላማ ሰርጎ ገቦችን ለመቆጣጠር ታሳቢ ያደረገ ነው እንጂ ጤናማ እንቅስቃሴዎችን ለማገድ ታስቦ አለመሆኑን ሁሉም ሰው በውል እንዲረዳው ያስፈልጋል " ብለዋል።

በመሆኑም ከቀያቸው ተፈናቅለው ደብረ ብርሃን ለመገኙ ወገኖች ከየትኛውም የሀገሪቱ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ድጋፍ ይዘው መምጣት የሚፈልጉ ሁሉ ክልከላው እንደማይመለከታቸው አውቀው ወደ ከተማው መምጣት እንደሚችሉ ከንቲባው አሳውቀዋል።

መረጃው የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
#ደብረብርሃን

በደብረ ብርሃን የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው ተብሏል።

የደብረ ብርሃን ከተማ ትራንስፖርት ልማት ጽ/ቤት ፤ በትራንስፖርት ዘርፍ እየተፈጠረ ያለውን ጫና ለመቅረፍ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ለማስጀመር ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አሳውቋል።

ጽ/ቤቱ በመንግስት ሠራተኛው ላይ የተፈጠረውን የኑሮ ውድነት ጫና ለማቃለል ሠራተኛው ለጊዜው #በነጻ_የትራንስፖረት_አገልግሎት እንዲጠቀም ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጿል።

የከተማ አውቶብስ አገልግሎት መጀመር በከተማ ታክሲ አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የሚፈጥረው ጫና የለም ተብሏል።

የከተማ አውቶብስ አገልግሎት እንዲጀመር ትራንስፖረት ጽህፈት ቤት ያቀረበውን ዕቅድ የደብረብርሃን ከተማ ከንቲባ ኮሚቴ እና ገንዘብ መምሪያው ተቀብለው ወደ ስራ እንዲገባ መፍቀዳቸው መገለፁን ከከተማው ኮሚኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ADAMA #BAHIRDAR ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራውን በባሕር ዳር እና በአዳማ ከተሞች ጀምሯል። ይህ የደንበኞች ሙከራ ከድሬዳዋ፣ ሐረር እና ሐረማያ በመቀጠል የሳፋሪኮምን ኔትወርክ ለመሞከር ባሕር ዳርን እና አዳማን 4ኛ እና 5ኛ የኢትዮጵያ ከተሞች አድርጓቸዋል። የሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ የአየር ሰዓት እና የስልክ ቀፎዎች ግዢ እንዲሁም የደንበኞች…
#Bishoftu #Mojo #Debrebrihan

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራውን በቢሾፍቱ፣ ሞጆ እና ደብረ ብርሃን ከተሞች መጀመሩን አሳውቋል።

ይህ የደንበኞች ሙከራ የሳፋሪኮምን ኔትወርክ እየሞከሩ ያሉትን ከተሞች ቁጥር #ስምንት የሚያደርሰው ሲሆን ባለፉት ሦስት ሳምንታት ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ሐረማያ፣ ባሕር ዳር እና አዳማ ላይ ሙከራው መጀመሩ ይታወቃል።

ደንበኞች የሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ የአየር ሰዓት እና የስልክ ቀፎዎች ግዢ እንዲሁም የደንበኞች ድጋፍ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ፦

#ቢሾፍቱ 📍

በቢሾፍቱ ሁለት የሳፋሪኮም መለያ የተለጠፈባቸው መደብሮች (ከኦዳ ነቤ ሆቴል ጎን እና ከመዘጋጃው ፊትለፊት)፤

#ሞጆ📍

በሞጆ አንድ መናኸሪያ አካባቢ የሚገኝ የሳፋሪኮም መለያ የተለጠፈበት መደብር፤

#ደብረብርሃን 📍

ከዘርዕ ያዕቆብ አደባባይ ወረድ ብሎ ባለው ኖክ ማደያ አካባቢ የሚገኝ የሳፋሪኮም መለያ የተለጠፈበት መደብር ደንበኞችን ለማገልገል ክፍት መሆኑን ገልጿል።

በቢሾፍቱ፣ በሞጆ እና በደብረ ብርሃን ከተሞች አገልግሎት በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሙከራ ኔትወርክ ደንበኞች ዳታ መጠቀም፣ ጥሪዎች እና የጽሁፍ መልዕክቶችን ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ጋር መለዋወጥ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ጥሪዎችን ማድረግ እንደሚችሉ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አሳውቆናል።

#SafaricomEthiopia

@tikvahethiopia
#ደብረብርሃን

ወደ ደብረ ብርሃን ከተማ መግቢያ ላይ በከባድ መሳሪያ የታገዘ የተኩስ ልውውጥ እየተካሄደ መሆኑን የደብረ ብርሃን ቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል።

አንድ የቤተሰባችን አባል ፤ በዚህ አይነት መንገድ ሰዎች ይጎዳሉ፣ ንፁሃን ይሞታሉ ፣ በአካባቢውም ተማሪዎች ይኖራሉና አስቸኳይ መፍትሄ ሊፈለግ ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ሌላኛው የደብረብርሃን ቤተሰባችን የሚመለከተው አካል ሁሉ ችግሮች አሁን ካሉበት ተባብሰው የሰዎችን ህይወት እንዳይቀጥፉ የሚቻላቸውን ሁሉ ማድረግ አለባቸው ፤ የአማራ ክልል አካባቢዎች ከዚህ በፊት በነበረው አስከፊ ጦርነት ብዙ ዋጋን የከፈሉ በመሆናቸው አሁንም ተጨማሪ የንፁሃን ሞት ፣ መፈናቀል ፣ ጉዳት እንዳይፈጠር በሰከነ መንገድ መፍትሄ መፈለግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ነሲሓ " ነሲሓ የበጎ አድራጎት እና የልማት ድርጅት " በደብረ ብርሃን የመጠለያ ካምፕ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ እያሰባሰበ እንደሚገኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል። ድጋፉ " ዘካተል ፊጥራችንን ለወገኖቻችን" በሚል መሪ ቃል የሚሰበሰብ መሆኑን አመልክቷል። የበጎ አደራጎት ድርጅቱ " ሙስሊሞች የምታወጡትን #ዘካተል_ፊጥር በደብረ ብርሃን ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ ይሆን ዘንድ በሚከተሉት አካውንቶች እያሰባሰበን…
#ደብረብርሃን

ነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት በደብረ ብርሃን መጠለያ ካምፕ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ ማድረጉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

ድርጅቱ ከማኅበረሰቡ ባሰባሰበው ድጋፍ 210 ኩንታል ፉርኖ ዱቄት ከፋብሪካ የገዛ ሲሆን፣ በአጠቃላይ ለ1800 አባወራ ድጋፍ ማድረግ መቻሉን አመልክቷል።

ነሲሓ የበጎ አድራጎትና ልማት ድርጅት ድጋፍ ለሰጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች ምስጋናውን አቅርቧል። ድርጅቱ ከቀናት በፊት በደብረ ብርሃን ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ ማቅረቡ ይታወቃል።

ከዚህ ቀደም በደብረ ብርሃን መጠለያ ካምፕ በርካታ ወገኖቻችን ተጠልለው እንደሚገኙ መግለፁ ይታወሳል፤ አሁንም ከድጋፍ አድራጊ ድርጅቶች የሚሰራው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ቢሆንም የሚመለከተው አካል ግን ዜጎች ወደ ቀደመ ህይወታቸው እንዲመለሱ ማድረግ አለበት።

@tikvahethiopia