TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል⬆️

በቤንሻንጉል ጉምዝ ካማሼ ዞን በተለይ በበሎይ ጅጋንፎይ ወረዳ በተባባሰ ግጭት ከ72 ሺህ ሰዎች በላይ ተፈናቅለው #ነቀምት እንደሚገኙ የምሥራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደርና ፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ #ታከለ_ቶሎሳ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።

በደንብ #የተደራጀና የታጠቀ ኃይል በተለይ ትላንት ከፍተኛ ጥቃት ከፍቶ በኦሮሚያ በኩል የሟቾች ቁጥር 23 መድረሱን ገልፀዋል።

የቤንሻንጉል ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #አበራ_ባይታ በበኩላቸው ሰዎች መፈናቀላቸውን ገልፀው "ቁጥሩ የተጋነነ ነው" ብለውታል። በቤንሻንጉል ጉምዝ በኩልም 31 ሰዎች ሞተዋል ይላሉ።

በከተማው ውስጥ ዘጠኝ ሰላማዊ ሰዎች #መገደላቸውን አረጋግጠዋል።

ከሁለቱ ክልል VOA ባገኘው አጠቃላይ መረጃ መጀመሪያ ላይ አራት ተገደሉ የተባሉ አመራሮችን ጨምሮ በአምስት ቀናት ውስጥ የ67 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች መኖራቸውና ብዙ መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውና ሁለቱም ክልሎች ተናግረዋል።

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሻሸመኔ
#ሀዋሳ
#ነቀምት
#አሰላ
#አዲስአበባ
#ሽሬ
#ደብረብርሃን
#ወላይታሶዶ
#አርባምንጭ
#ጅግጅጋ
#አዳማ
#ድሬዳዋ
#ባህርዳር
#መቐለ
#ሀረር
#ጎንደር

ከሌሎች በርካታ ከተሞች ከሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች የSAT ውጤት ያልጠበቁት እንደሆነ በመግለፅ ቅሬታቸው እያሰሙ ይገኛሉ። የሚመለከተው አካል ማብራሪያ እንዲሰጥበትም ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ነቀምት

ዛሬ ምሽት የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ጣቢያ በሰራው ዘገባ በምራዕብ ቀጠና የኢትዮ ቴሌኮም ኃላፊ አቶ ገመቺስ ታደሰ ግድያ ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የነቀምቴ ከተማ ፖሊስን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ ኃላፊው ከትናንት በስቲያ ዕሁድ አመሻሽ 1 ሠዓት ገደማ ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች መገደላቸውን ፖሊስ አስታወቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia