TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ምክትል ጠ/ሚ ደመቀ⬆️

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን ከረጅም ዓመታት የውጭ ሃገር ቆይታ በኋላ ወደ እናት ሃገሩ የተመለሰውን አርቲስት #ታማኝ_በየነን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

አርቲስት ታማኝ ከረጅም ዓመታት የውጭ ሃገር ቆይታ በኋላ ሲመለስ . . . "ወደ ምትወዳት እናት ሃገርህ እንኳን ደህና መጣህ" ብለውታል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ፡፡

በሃገሪቱ የተጀመረው ለውጥ ውሃ-ልኩን ጠብቆ ለህዝብና ለሃገር የሚተርፍ ቁም-ነገር እንደዜጋ ለማበርከት መልካም መንፈስ እና ቀና ድጋፍ መኖሩን አቶ ደመቀ አውስተዋል፡፡

ከዚህ በኋላ ስለ እናት ሃገር እና ህዝቦቿ በርቀት በመብከንከን ሳይሆን፤ የዜግነት ግዴታን ለመወጣት እና ግላዊ አበርክቶን ለማኖር ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ገልጸዋል፡፡

አርቲስት ታማኝ በበኩሉ መንግስት ያደረገለትን ደማቅ አቀባበል እጅግ እንዳስደሰተው በመግለጽ፤ በሃገሪቱ የተጀመረው #ለውጥ ቀጣይነቱ
እንዲረጋገጥ እና ፍሬ እንዲያፈራ #የበኩሉን እንደሚወጣ ተናግሯል፡፡

"ሃገሬ #በምትፈልገኝ ቦታ ሁሉ በተግባር ለመገኘት ዝግጁ ነኝ!" በማለት አርቲስት ታማኝ ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ በውይይቱ ላይ አረጋግጧል፡፡

©Office of Deputy Prime Minister
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ‼️

ነገ ለሚደረገው #ሰላማዊ_ሰልፍ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ ከዞን ፖሊስ፣ ከክልሉ ልዩ ሃይልና #ከፌደራል_ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ሰልፉ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች በቂ ጥበቃ ያደርጋል። ከሪፈራል አደባባይ ጠዋት አንድ ሰዓት የሚጀመረው ሰላማዊ ሰልፍ መዳረሻው ከቀኑ ስድስት ሰዓት ሃዋሳ አለም አቀፍ ስታዲየም ነው፡፡

ሰልፉ ወደ ብሉናይል የሚያወጣውን አስፓልት ይዞ ተስፋዬ ግዛው ህንጻ አደባባይ ሲደርስ ወደ ሃዋሳ አለም አቀፍ ስታዲየም እንደሚገባና ማጠቃለያውን እንደሚያደርግ ተናግሯል። በዚህ ምክንያት መንገዶቹ ለተሸከርካሪ #ዝግ ይሆናሉ እንዲሁም በበቂ የፀጥታ ሃይል ጥበቃ ይደረጋል፡፡ የከተማው ነዋሪ በሰልፉ ምክንያት #ስጋት ውስጥ እንዳይገባ በየክፍለ ከተማው #ውይይት መደረጉ ተገልጿል፤ ህዝቡም ለሰልፉ ሰላማዊነት #የበኩሉን እንዲወጣ ተጠይቋል፡፡

በተጨማሪ፦

የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ በማህበራዊ ሚዲያ ከሚሰራጩ #ሀሰተኛ_መረጃዎች ራሱን እንዲያርቅ ጥሪ ቀርቧል። ነዋሪው ምንም አይነት ሰላም የማደፍረስ እንቅስቃሴ ካየ ለፀጥታ ሀይሉ #ጥቆማ እንዲያደርስ ጥሪ ተላልፏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia