TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወላይታ 🕊 ሲዳማ‼️

የወላይታ እና የሲዳማ ብሄሮች ዘመን ተሻጋሪ አንድነትና እብሮነት ቀጣይ አንዲሆን በትጋት አንደሚሰሩ የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት፣ የወላይታ እና የሲዳማ ዞኖች አስተዳደር፣ የኃይማኖት አባቶች፣የሀገር ሽማግሌዎችና የሶዶ ዩኒቨርሲቲ አመራር አካላት አስታወቁ፡፡

በማህበራዊ ሚዲያ በተለቀቁ #ሀሰተኛ መረጃዎች መነሻነት ላለፉት ጥቂት ቀናት ሶዶ ዩኒቨርስቲንና እና ሶዶ ግብርና፤ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅን በመልቀቅ ወደ ሀዋሳ እና አካባቢው ቤተሰብ ዘንድ የተመለሱ ተማሪዎች ዳግም ወደ ትምህርት ገበታቸው #ተመልሰዋል፡፡

ለተማሪዎቹ የወላይታ ዞን አስተዳደር፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የሶዶ ዩኒቨርሲቲ አመራር አካላት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት የሰላም ተምሳሌት የሆነውን #እርጥብ_ሳር አበርክተውላቸዋል፡፡

ከተማሪዎቹ አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያየት በማህበራዊ ሚዲያ የተለቀቁ የተዛቡ መረጃዎች በፈጠሩት ስጋት ወደ ትውልድ ቀዬአቸው መመለሳቸወን ተናግረው እውነተኛውን መረጃ በማግኘት ዳግም ወደ ትምህርት ገበታቸው መመለሳቸውን አመላክተዋል፡፡

ወደ ተምህርት ገበታቸው ዳግም እንዲመለሱ የክልልሉ መስተዳድር ምክር ቤት፣ የወላይታ ዞን አስተዳደር፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የሶዶ ዩኒቨርሲቲ አመራር አካላት አባታዊ ጥረት ማድረጋቸውን አብራርተው የወላይታ ዞን አስተዳደር፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የሶዶ ዩኒቨርሲቲ አመራር አካላት ባደረጉላቸው ደማቅ አቀባበል #መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚስተዋሉ ትንኮሳዎችና እንዲታረሙና አንዳንድ የግብአት መጓደሎች አንዲሟሉ ጠይቀዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች አንድነት የበልጥ አንዲጠናከር የህዝብ ለህዝብ ግኑኝት ሥራዎች ይበልጥ #ተጠናክረው እንዲሰሩ ጠይቀዋል፡፡

የክልሉ ፕሬዚዳንት ተወካይ አቶ ተመነ ተሰማ የሲዳማ እና የወላይታ ብሄሮችን የቆየ የአብሮነት እሴቶች #በመሸርሸር የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የቋመጡ ጸረ-ሰላም ኃይሎች በሚያነፍሱት ሀሰተኛ መረጃዎች ተማሪዎች ዳግም ሰለባ እንዳይሆኑ አሳስበዋል።

በሁለቱ ዞን ህዝቦች መካከል የእርቅ ኮንፈረንስ በቅርቡ አንዲካሄድ በክልሉ እና በሁለቱም ዞኖች በኩል የተጠናከረ ቅድመ-ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የወላይታ ዞን አስተዳደር፣ የኃይማኖት አባቶች፣የሀገር ሽማግሌዎችና የሶዶ ዩኒቨርሲቲ አመራር አካላት የሲዳማ እና የወላይታ ህዝቦች የቆየ መስተጋብር ያላቸው ህዝቦች መሆናቸውን ተናግረው አንድነቱ ዘላቂ እንዲሆን ህዝቡን በማሳተፍ ተግተው አንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡

በስነ-ስርዓቱ ላይ የወላይታ ዞን የንግድ ማህበረሰብ ለክልሉ መስተዳዳር ምክር ቤት ፣ ለሲዳማ ዞን አስተዳደር ተወካዮች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች የዘላቂ አንድነትና የአብሮነት ማሳያ ስጦታ አበርክተውላቸዋል፡፡

ምንጭ፦ ወላይታ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳች መምሪያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች‼️

በማዕበራዊ ሚዲያዎች በተለይም ደግሞ በፌስቡክ በሚሰራጩ #ሀሰተኛ መረጃዎች እንዳትደናገሩ። በዛሬው ዕለት የከተማው አስተዳደር ህጋዊ እውቅና የሰጠው ህዝባዊ #ሰልፍ_የለም

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀዋሳ መደበኛ የሆነ የዕለት ተዕለት እና ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ ናት። በማዕበራዊ ሚዲያዎች በሚሰራጩ #ሀሰተኛ መረጃዎች ነዋሪዎች ግር ልትሰኙ አይገባም።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ‼️

ነገ ለሚደረገው #ሰላማዊ_ሰልፍ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ ከዞን ፖሊስ፣ ከክልሉ ልዩ ሃይልና #ከፌደራል_ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ሰልፉ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች በቂ ጥበቃ ያደርጋል። ከሪፈራል አደባባይ ጠዋት አንድ ሰዓት የሚጀመረው ሰላማዊ ሰልፍ መዳረሻው ከቀኑ ስድስት ሰዓት ሃዋሳ አለም አቀፍ ስታዲየም ነው፡፡

ሰልፉ ወደ ብሉናይል የሚያወጣውን አስፓልት ይዞ ተስፋዬ ግዛው ህንጻ አደባባይ ሲደርስ ወደ ሃዋሳ አለም አቀፍ ስታዲየም እንደሚገባና ማጠቃለያውን እንደሚያደርግ ተናግሯል። በዚህ ምክንያት መንገዶቹ ለተሸከርካሪ #ዝግ ይሆናሉ እንዲሁም በበቂ የፀጥታ ሃይል ጥበቃ ይደረጋል፡፡ የከተማው ነዋሪ በሰልፉ ምክንያት #ስጋት ውስጥ እንዳይገባ በየክፍለ ከተማው #ውይይት መደረጉ ተገልጿል፤ ህዝቡም ለሰልፉ ሰላማዊነት #የበኩሉን እንዲወጣ ተጠይቋል፡፡

በተጨማሪ፦

የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ በማህበራዊ ሚዲያ ከሚሰራጩ #ሀሰተኛ_መረጃዎች ራሱን እንዲያርቅ ጥሪ ቀርቧል። ነዋሪው ምንም አይነት ሰላም የማደፍረስ እንቅስቃሴ ካየ ለፀጥታ ሀይሉ #ጥቆማ እንዲያደርስ ጥሪ ተላልፏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በጎንደር ህዝባዊ ተቃውሞ ተቀስቅሷል"

ዛሬ ይህን መረጃ በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲሰራጭ ተመልክተን ጎንደር የሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላትን ጠይቀናቸው "ነጭ ውሸት" ነው ወጣቱ ከመከላከያ ጋር አልተጋጨም፤ ህዝባዊ ተቃውሞ የሚያስብል አይደለም ብለውናል። ህዝቡም ከእንዲህ ያሉ #ግጭትን ከሚቀሰቅሱ እና ከሚያባብሱ #ሀሰተኛ መረጃዎች ራሱን እንዲያርቅም መክረዋል።

•Ethiopian Dj ~ የፌስቡክ ገፅ
•የተከታዮቹ ብዛት:1,928,218

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የጥላቻ_ንግግሮች: የማህበራዊ ትስስር ድረ ገፅ የሆነው ትዊተር የጥላቻ ንግግር የሚነዙ ተጠቃሚዎችን ከገጹ እንደሚያግድ አስታወቀ። በተለይም ከሀይማኖት ጋር በተያያዘ ሰብአዊነትን የሚያጎድፉ ይዘት ያላቸው መረጃዎችና እና ጽሁፎችን የሚለቁ አካላትን ሙሉ በሙሉ ከገጹ እንደሚያግድ ነው ያስታወቀው። ኩባንያው ይህንን ለማድረግ የሚረዳው አዲስ #ህግ ማውጣቱም ተነግሯል።

በአዲሱ የትዊተር ሀግ መሰረት ከዚህ በፊት በገጹ የተለቀቁ የጥላቻ ንግግሮችም ከገጹ እንዲነሱ እንደሚደረግ ታውቋል። ሆኖም ግን ግለሰቦቹ የጥላቻ ንግግሮቹን የለቀቁት ህጉ ከመውጣቱ በፊት በመሆኑ ከገጹ እንደማይታገዱ ተነግሯል።

ትዊተር ከዚህ ቀደምም የመተግበሪያውን ህግና ደንብ የሚተላለፉ የሃገር መሪዎችና ፖለቲከኞች የሚያሰራጩትን መልዕክት ሊደብቅ መሆኑን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

ትዊተር ይህን ውሳኔ ያሳለፈው የተለያዩ ተፅዕኖ ፈጣሪ ፖለቲከኞች የመተግበሪያውን ህግና ደንብ በመጣስ ተገቢ ያልሆኑ መረጃዎችን ለተከታዮቻቻው በማሰራጨታቸው እንደሆነም ነው በወቅቱ የተጠቀመው።

ከዚህ በተጨማሪም #ሀሰተኛ መረጃዎች እየተበራከቱ በመምጣታቸው ተከትሎ ችግሩን ከስሩ ለማድረቅ ትዊተር በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሀሰተኛ አካውንቶችን ማገዱም ይታወሳል።

ምንጭ፦ www.cnet.com---/#fbc/
🗞ቀን ሃምሌ 3/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጥንቃቄ #ETHIOPIA የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ማለፊያ ነጥብ/መቁረጫ ነጥብ/ ገና ይፋ አልተደረገም። ስለሆነም ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ሊሰራጩ ከሚችሉ #ሀሰተኛ መረጃዎች ከወዲሁ እንድትጠነቀቁ እንመክራለን።

🏷ይፋ ስለተደረገው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ጋር ተያይዞ ያልተሰሙ አዳዲስ መረጃዎች ካሉ ተከታትለን እናቀርባለን።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ጉባዔ ተቀምጧል፡፡ በዛሬው የጉባዔው ውሎ የመንግሥት ሃላፊዎች መገኘታቸው ተሰምቷል፡፡

Via #WAZEMA

•ከሰሞኑን ከሲኖዶሱ ጋር በተገናኘ በፌስቡክ ብዙ #ሀሰተኛ መረጃዎች እየተሰራጨ ስለሆነ TIKVAH-ETH በታማኝ ሚዲያዎች እና ከሚመለከታቸው አካላት ብቻ የሚሰማውን መረጃ ያጋራል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሚዲያ ጠፍተው የከረሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ ብቅ ብለዋል።

ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት የሰው ሰራሽ አካልና የአካል ድጋፍ ማደራጃ ድርጅትን መጎብኘታቸውን ገልፀዋል።

ዶክተር አብይ አህመድ በጤና ሚኒስቴር የሰው ሠራሽ አካልና የአካል ድጋፍ ማደራጃ ድርጅትን የጎበኙት ዛሬ ረፋድ ላይ ነው።

ድርጅቱ ሰው ሰራሽ አካል እና ለመንቀሳቀስ ድጋፍ የሚሆን እንደ ክራንች ያሉትን እና ሰው ሰራሽ አካላትን በማምረት ይታወቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሚዲያ ጠፍተው መክረማቸውን ተከትሎ ደህንነታቸውን በሚመለከት በማህበራዊ ሚዲያዎች የተለያዩ #ሀሰተኛ መረጃዎች ሲሰራጩ ነበር ፤ በዚህም ቢሯቸው የጠቅላይ ሚኒስትሩን ደህንነት በሚመለከት ትክክለኛ መረጃ ሰጥቶ እንደነበር ይታወሳል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#TiffanyHaddish

የ41 ዓመቷ አሜሪካዊት ተዋናይትና ኮሜዲያን ቲፋኒ ሀዲሽ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ስላለው ግጭት በሰጠቻቸው አስተያየቶች/በምታጋራው መልዕክቶ ምክንያት ከፍተኛ ተቃውሞ እየቀረበባት ነው።

የምታጋራው መልዕክቶች በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን አስቆጥቷል።

ቲፍኒ ሀዲሽ ፥ "በትግራይ ላይ የሚፈፀውን የንፁሃን ግድያ ፣ የሴቶች መደፈር፣ የህፃናት ሞት ክዳለች ፣ በትግራይ ጉዳይ ጦሯን ላሰማራቸው #ኤርትራ በተለይም አምባገነን ለሆነው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ድጋፍ ትሰጣለች" በሚል ነው ከፍተኛ ተቃውሞ እያስተናገደች የምትገኘው።

ቲፍኒ ሀዲሽ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በትግራይ ስላለው ሁኔታ በትዊተር ገጿ የተለያዩ መልዕክቶችን እያስተላለፈች ሲሆን ከነዚህ ውስጥ አንዱ ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ የሚሰራጩ #ሀሰተኛ መረጃዎች የሚመለከት ነው።

በተጨማሪ፥ በአንድ ሪትዊት ላይ የቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዜዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን "ጦርነቱ የህዝብ መሆኑን ህፃናትም የዚህ አካል ስለመሆናቸው" ተናግረውበታል የተባለውን የእሳቸውን ንግግር አጋርታለች።

ከተቃዋሚዎቹ በተቃራኒው ደግሞ የምታጋራቸውን መልዕክቶች ትክክል እንደሆኑ የሚገልፁ በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ታይተዋል።

ቲፍኒ ሀዲሽ በ1979 እ.አ.አ. በሎስ አንጀለስ የተወለደች ሲሆን አባቷ ፀሃዬ ረዳ ሀድሽ በወቅቱ የኢትዮጵያ አካል የነበረችውን ኤርትራን ጥለው የተሰደዱ ስደተኛ ነበሩ።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ቲፋኒ ሀዲሽ ከኤርትራና ከመሪዋ ኢሳያስ አፍወርቂ ጋር ጥሩ የሚባል ወዳጅነትንና ቅርርብ ስለመፍጠራቸው ይነገራል።

ለመጀመሪያ ጊዜ ኤርትራን የጎበኘችው እ.ኤ.አ. በ2018 ሲሆን በወቅቱ የአባቷን ህልፈት ተከትሎ በእሳቸውን የቀብር ስነስርዓት ላይ ለመገኘት ነበር።

@tikvahethiopia